Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 145:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ነው፤ ለቊጣ የዘገየና በዘለዓለማዊ ፍቅር የተሞላ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ፣ ለቍጣ የዘገየ፣ ታማኝነቱም የበዛ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታ ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቁጣ የራቀ፥ ጽኑ ፍቅሩም ብዙ ነው፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የወ​ደ​ቁ​ትን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕው​ሮ​ችን ጥበ​በ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቃ​ንን ይወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል፤

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 145:8
14 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩና ታማኝነቱ ዘለዓለማዊ ነው።


እግዚአብሔር መሐሪና ይቅር ባይ ነው። በቶሎ የማይቈጣና ለዘለዓለም ታማኝ ነው።


እግዚአብሔር ቸርና እውነተኛ ነው፤ አምላካችን መሐሪ ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን መሐሪና ርኅሩኅ ለቊጣ የዘገየህ፥ የተትረፈረፈ ፍቅርና ታማኝነት ያለህ አምላክ ነህ።


ጌታ ሆይ! አንተ ለእኛ ቸርና መሐሪ ነህ፤ ወደ አንተ ለሚጸልዩትም ሁሉ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን ታሳያቸዋለህ።


ጌታ አምላካችን ሆይ፥ ምንም እኛ በአንተ ላይ ብናምፅ አንተ መሐሪና ይቅር ባይ ነህ።


እንዲህም ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦ “እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህን እንደምታደርግ ገና በአገሬ ሳለሁ ተናግሬ አልነበረምን? ከፊትህ ኰብልዬ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ያቀድኩትም በዚህ ምክንያት ነበር፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ በዘለዓለማዊ ፍቅር የተመላህ፥ ቊጣህን መልሰህ ምሕረት የምታደርግ አምላክ መሆንህን ዐውቅ ነበር።


‘እግዚአብሔር በቶሎ አይቈጣም፤ ምሕረቱና ፍቅሩ የበዛ ነው፤ ኃጢአትንና ዐመፃን ይቅር ይላል፤ ነገር ግን እስከ ሦስት ከዚያም እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆችንና የልጅ ልጆችን ስለ ወላጆቻቸው ኃጢአት እቀጣለሁ’ እንዳልከው፥


ይህንንም ያደረገው በተወደደው ልጁ አማካይነት በነጻ የሰጠን ክቡር ጸጋ እንዲመሰገን ነው።


ጸጋውንም በጥበብና በዕውቀት ሁሉ አብዝቶ አፈሰሰልን።


ነገር ግን የእግዚአብሔር ምሕረቱ ብዙ ከመሆኑና ለእኛም ያለው ፍቅር ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos