Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 109:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር የቀድሞ አባቶቹን ኃጢአት ያስብበት፤ የእናቱንም ኃጢአት ይቅር አይበልላት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የአባቶቹ በደል በእግዚአብሔር ፊት ይታሰብ፤ የእናቱም ኀጢአት አይደምሰስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የአባቶቹ ጥፋት በጌታ ፊት ትታወስ፥ የእናቱም ኃጢአት አትደምሰስ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 109:14
15 Referencias Cruzadas  

በዳዊት ዘመነ መንግሥት ሦስት ዓመት ሙሉ ጽኑ ራብ ነበር፤ ዳዊትም ስለዚህ ጉዳይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጠየቀ ጊዜ እግዚአብሔር “ሳኦልና ቤተሰቡ ግድያ በመፈጸም በደል ሠርተዋል፤ ሳኦልም የገባዖንን ሰዎች ፈጅቶአል” ሲል መለሰለት።


ስለዚህም ቅጣቱ በኢዮአብና በቤተሰቡ ላይ ይውረድ! በዘመናት ሁሉ ከቤተሰቡ የአባለ ዘር ወይም የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው አይጥፋ! እንዲሁም አካለ ስንኩል የሆነ ሰው፥ በጦር ሜዳ የሚሞት ወይም የሚበላው አጥቶ የሚራብ ሰው አይታጣ!”


የንጉሥ አካዝያስ እናት ዐታልያ የልጅዋን መገደል እንደ ሰማች ወዲያውኑ የይሁዳ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጠች።


አካዝያስ የንጉሥ አክዓብ ዐማች ከመሆኑ የተነሣ ልክ እንደ አክዓብ ቤተሰብ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ።


ንጉሥ አካዝያስ የሆነውን ነገር ሁሉ በተመለከተ ጊዜ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ቤትሀጋን ከተማ ሸሽቶ ሄደ፤ ኢዩ ተከታትሎ እያሳደደው “እርሱንም ግደሉት!” ሲል ለወታደሮቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አካዝያስን ተከታትለው በዪብለዓም ከተማ አጠገብ በምትገኘው በጉር የአቀበት መንገድ ላይ በሠረገላው ሲበር መትተው አቈሰሉት፤ እርሱ ግን እንደምንም ጨክኖ መጊዶ ከተማ እስኪደርስ ተጓዘ፤ በዚያም ሞተ፤


ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር ምሕረት አታድርግላቸው፤ የፈረሰውን በመሥራታችን በስድብ አዋርደውናልና በደላቸውን አትርሳ።”


እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።


ዘለዓለማዊ ፍቅሬንም እስከ ብዙ ሺህ ትውልድ እጠብቃለሁ፤ በደልን መተላለፍንና ኃጢአትን ሁሉ ይቅር እላለሁ፤ ነገር ግን እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ ስለ ወላጆቻቸው ኃጢአት ከመቅጣት አልገታም።”


ይህም ሁሉ ሆኖ ኃጢአታችሁን ይቅር የምል አምላክ እኔ ነኝ፤ ይህንንም የማደርገው ስለ እናንተ ሳይሆን ስለ እኔነቴ ነው፤ ስለዚህ ኃጢአታችሁን አልቈጥርባችሁም።


አምላክ ሆይ! እነርሱ እኔን ለመግደል የሸረቡትን ሤራ ታውቀዋለህ፤ ስለዚህ ክፋታቸውን ይቅር አትበል፤ ኃጢአታቸውም እንዲሰረይላቸው አታድርግ፤ በፊትህ እንዲሸነፉና በብርቱ ቊጣህ እንዲወድቁ አድርግ።”


በጠላቶቻችሁ ምድር ከሞት ተርፋችሁ የምትቀሩት ጥቂቶቻችሁ፥ በራሳችሁና በቀድሞ አባቶቻችሁ ኃጢአት ምክንያት መንምናችሁ ትቀራላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos