ዘኍል 14:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ‘እግዚአብሔር ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩ የበዛ፣ ኀጢአትንና ዐመፃን ይቅር የሚል፣ በደለኛውን ግን ሳይቀጣ የማይተው፣ ስለ አባቶቻቸውም ኀጢአት ልጆችን እስከ ሦስትና አራት ትውልድ የሚቀጣ ነው።’ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ‘ጌታ ታጋሽና ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ በደልንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን በደል እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው።’ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ‘እግዚአብሔር በቶሎ አይቈጣም፤ ምሕረቱና ፍቅሩ የበዛ ነው፤ ኃጢአትንና ዐመፃን ይቅር ይላል፤ ነገር ግን እስከ ሦስት ከዚያም እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆችንና የልጅ ልጆችን ስለ ወላጆቻቸው ኃጢአት እቀጣለሁ’ እንዳልከው፥ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 እግዚአብሔር መዓቱ የራቀ ምሕረቱ የበዛ ጻድቅ፥ አበሳን፥ መተላለፍንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፥ ኀጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኀጢአት እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው። Ver Capítulo |