ዮሐንስ 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በመካከላችን ኖረ፤ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ እንዳለው ያለውን ክብሩን አይተናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ ልጅን ክብር አየን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በእኛም ዘንድ አደረ፤ ጸጋንና እውነትን የተመላውን፥ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ ያለውን ክብሩንም አየን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእኛም አደረ፤ ለአባቱ አንድ እንደ ሆነ ልጅ ክብር ያለ ክብሩን አየን፤ ጸጋንና እውነትን የተመላ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን። |
አገልጋዬ በደረቅ ምድር ላይ እንደሚወጣ ሥርና እንደ ቡቃያ አድጓል፤ እንመለከተው ዘንድ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤ እርሱን እንወደው ዘንድ ከመልኩ አንዳች እንኳ የሚስብ ደም ግባት የለውም።
በዚያም የበኲር ልጅዋን ወለደች፤ በመታቀፊያ ጨርቅ ጠቀለለችው፤ በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ስላላገኙ በበረት በከብቶች መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛችው።
በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና ጓደኞቹ በእንቅልፍ ተሸንፈው ተኝተው ነበር፤ በነቁ ጊዜ ግን የኢየሱስን ክብርና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሁለቱን ሰዎች አዩ።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ፊልጶስ ሆይ! ይህን ያኽል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ ታዲያ፥ አንተ ‘አብን አሳየን’ እንዴት ትላለህ?
“አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እነዚህ አንተ የሰጠኸኝም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እወዳለሁ።
ጲላጦስም “ታዲያ፥ አንተ ንጉሥ ነኻ?” አለው። ኢየሱስም “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንኩ አንተ ትላለህ፤ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ልመሰክር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማል” ሲል መለሰ።
ኢየሱስ ይህን የተአምራት ሁሉ መጀመሪያ የሆነውን ተአምር በገሊላ ምድር በቃና ከተማ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት ክብሩን ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
ከሰማይ የወረደው ሕይወትን የሚሰጥ እንጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እንጀራ የሚበላ ሁሉ ለዘለዓለም ይኖራል፤ ለዓለም ሕይወት እንዲሆን እኔ የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።”
እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት በማስነሣቱ ይህንኑ ተስፋ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞታል፤ ይህም በሁለተኛው መዝሙር፥ ‘አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤’ ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።
እነርሱ በትውልዳቸው ከነገድ አባቶች የመጡ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የመጣው ከእነርሱ ዘር ነው፤ እርሱ ከሁሉ በላይ ነው፤ ለዘለዓለምም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን!
ነገር ግን እርሱ “የእኔ ኀይል ፍጹም ሆኖ የሚገለጠው በአንተ ደካማነት ስለ ሆነ ጸጋዬ ይበቃሃል” አለኝ፤ ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ላይ እንዲሆን ከምን ጊዜውም ይልቅ በደካማነቴ ደስ እያለኝ ልመካ እወዳለሁ።
እኔ ከቅዱሳን ሁሉ የማንስ ብሆንም እንኳ ወሰን የሌለውን የክርስቶስን ባለጸግነት ለአሕዛብ እንዳበሥር በእግዚአብሔር ጸጋ ይህ ዕድል ተሰጠኝ።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።
እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ትክክል ነው። በኀያል ቃሉ ዓለምን ሁሉ ደግፎ ይዞአል፤ ሰዎችንም ከኃጢአት ካነጻ በኋላ በሰማይ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦአል።
እግዚአብሔር ከቶ ከመላእክት መካከል፥ “አንተ ልጄ ነህ፤ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤” ወይም “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ማንን ነው?
ሰዎችን ቅዱሳን የሚያደርጋቸውና በእርሱ ቅዱሳን የሆኑትም ሰዎች የአንድ አባት ልጆች ናቸው፤ በዚህ ምክንያት ኢየሱስ እነርሱን “ወንድሞቼ” ብሎ ለመጥራት አያፍርም።
እንዲሁም ክርስቶስ የካህናት አለቃ የመሆንን ክብር በገዛ ራሱ አልወሰደም፤ ነገር ግን እርሱ የካህናት አለቃ የመሆንን ክብር ያገኘው፥ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ካለው ከእግዚአብሔር ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡን የማያምኑ ብዙ አሳሳቾች በዓለም ተነሥተዋል። እንዲህ ያለው ሰው አታላይና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
እንዲህም የሚል ከፍተኛ ድምፅ ከዙፋኑ ሲወጣ ሰማሁ፤ “እነሆ! የእግዚአብሔር ማደሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱም ጋር ይኖራል፤ እነርሱም የእርሱ ሕዝብ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤