Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ገላትያ 4:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከልን፤ እርሱ ከሴት ተወለደ፤ ለሕግም ታዛዥ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የዘመኑ ሙላት በመጣ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነገር ግን ቀጠ​ሮው በደ​ረሰ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን ላከ፤ ከሴ​ትም ተወ​ለደ፤ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ፈጸመ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 4:4
44 Referencias Cruzadas  

በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በአንተ ዘርና በእርስዋ ዘር መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ። የእርስዋ ዘር የአንተን ራስ ይቀጠቅጣል፤ አንተም የእርስዋን ዘር ተረከዝ ትነክሳለህ።”


‘ሴሎ’ ተብሎ የሚጠራው፥ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለትና ለዘለዓለም የሚነግሠው እስኪመጣ ድረስ፥ በትረ መንግሥት (የገዢነት ሥልጣን) ከይሁዳ እጅ አይወጣም።


ወደ እኔ ቀርባችሁ ይህን ስሙ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ የተናገርኩት በምሥጢር አይደለም፤ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እኔ እዚያ ነበርኩ።” አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።


እንግዲህ እግዚአብሔር ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ‘ዐማኑኤል’ ብላ ትጠራዋለች፤


እናንተ እምነት የጐደላችሁ ሕዝብ፥ እስከ መቼ ታመነታላችሁ? እኔ እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገርን ፈጥሬአለሁ፤ ይኸውም ሴት ለወንድ ትከላከላለች። ልዩ የሆነ አዲስ ነገር ፈጥሬአለሁ።”


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ቅርንጫፉ በቦታው ስለሚስፋፋ ቅርንጫፍ የሚባል ስም ያለው ይህ ሰው ነው። ባለበት ስፍራ በቅሎ ገናና ይሆናል፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ እንደገና ይሠራል፤


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ በፊቴ መንገድን ያዘጋጅ ዘንድ መልእክተኛዬን እልካለሁ፤ የምትፈልጉት ጌታም በድንገት ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጣል፤ በእርሱ የምትደሰቱበት የቃል ኪዳን መልእክተኛም በእርግጥ ይመጣል።”


ስለ ኃጢአት ስርየትም የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል ታቀርባላችሁ፤ ይህም የኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት ነው።


“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙም ‘ዐማኑኤል’ ተብሎ ይጠራል።” ዐማኑኤል ማለትም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” ማለት ነው።


ኢየሱስ ግን “የጽድቅን ሥራ ሁሉ በዚህ መንገድ መፈጸም ስለሚገባን፥ አሁንስ ተው፤ እንዲሁ ይሁን” ሲል መለሰለት። ዮሐንስም በነገሩ ተስማምቶ ኢየሱስን አጠመቀው።


ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የኦሪትን ሕግና የነቢያትን ትምህርት ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ እኔ እንዲፈጸሙ ላደርጋቸው መጣሁ እንጂ ልሽራቸው አልመጣሁም።


ሲያስተምርም፦ “ዘመኑ ተፈጽሞአል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ! በወንጌልም እመኑ!” ይል ነበር።


እነሆ! ትፀንሺአለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።


መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል እግዚአብሔርም ኀይል በአንቺ ላይ ይሆናል፤ ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ሕፃን ቅዱስ ነው፤ የእግዚአብሔርም ልጅ ይባላል።


በዚያም የበኲር ልጅዋን ወለደች፤ በመታቀፊያ ጨርቅ ጠቀለለችው፤ በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ስላላገኙ በበረት በከብቶች መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛችው።


እንግዲህ ዳዊት ራሱ ጌታ ብሎ ከጠራው ታዲያ፥ መሲሕ ለዳዊት እንዴት ልጁ ሊሆን ይችላል?”


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በመካከላችን ኖረ፤ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ እንዳለው ያለውን ክብሩን አይተናል።


ታዲያ፥ አብ የቀደሰውንና ወደ ዓለም የላከውን ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስለ አለ ስለምን ‘በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ትናገራለህ’ ትሉታላችሁ?


“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ዓለምን እጅግ ስለ ወደደው አንድያ ልጁን ሰጠ።


እኔ ከሰማይ የወረድኩት የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ እንጂ የራሴን ፈቃድ ለማድረግ አይደለም።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆንማ እኔን በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ወደዚህ የመጣሁት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ የላከኝ እርሱ ነው እንጂ እኔ በራሴ ሥልጣን አልመጣሁም።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ጊዜና ዘመን እናንተ ልታውቁት አትችሉም።


ወንጌሉ የእግዚአብሔር ልጅ በሰብአዊነቱ በኩል፥ ከዳዊት ዘር መወለዱን የሚያበሥር ነው፤


ይህንንም ስናገር እግዚአብሔር ለቀደሙት አባቶች የሰጠው ተስፋ እንዲፈጸምና የእግዚአብሔርም እውነተኛነት እንዲታወቅ ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ ሆነ ማለቴ ነው።


ገና ደካሞች ሆነን ሳለ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች ሞተ።


ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።


እነርሱ በትውልዳቸው ከነገድ አባቶች የመጡ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የመጣው ከእነርሱ ዘር ነው፤ እርሱ ከሁሉ በላይ ነው፤ ለዘለዓለምም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን!


ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር በሥራ ላይ የሚያውለው ዕቅድ በሰማይና በምድር ያሉት ፍጥረቶች ሁሉ ተጠቃለው በአንዱ በክርስቶስ ሥልጣን ሥር እንዲሆኑ ነው።


እርሱ ያንን ይከሰንና ይቃወመን የነበረውን በሕግ ያለውን የዕዳ ጽሑፍ ደመሰሰው፤ በመስቀል ላይ ቸንክሮም ከእኛ አስወገደው።


ሰዎችን ሁሉ ከኃጢአት ለመዋጀት ራሱን ቤዛ አድርጎ የሰጠ እርሱ ነው፤ ይህም ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ የሚያስረዳ ምስክርነት ነው።


የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።


ስለዚህ እነዚህ ልጆች ሥጋና ደም ያላቸው ሰዎች እንደ መሆናቸው ኢየሱስም እንደ እነርሱ ሰው ሆነ፤ ይህን ያደረገውም በሞቱ አማካይነት በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስን ለማጥፋት ነው፤


እነዚህ ነገሮች የመታደስ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ በሥራ ላይ የዋሉ አፍአዊ ሥርዓቶች ናቸው፤ እነርሱ ስለ መብልና ስለ መጠጥ፥ ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶችም ብቻ የተደረጉ ናቸው።


አብ የዓለም አዳኝ አድርጎ ወልድን እንደ ላከው አይተናል፤ እንመሰክራለንም።


የእግዚአብሔርን መንፈስ ለይታችሁ የምታውቁት በዚህ ነው፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡን የሚያምን መንፈስ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos