Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 18:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ጲላጦስም “ታዲያ፥ አንተ ንጉሥ ነኻ?” አለው። ኢየሱስም “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንኩ አንተ ትላለህ፤ እኔ የተወለድኩትና ወደ ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ልመሰክር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማል” ሲል መለሰ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ጲላጦስም፣ “ታዲያ፣ ንጉሥ ነህ ማለት ነዋ!” አለው። ኢየሱስም፣ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ መናገርህ ትክክል ነው፤ የተወለድሁት፣ ወደዚህም ዓለም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመስከር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ይሰማኛል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ጲላጦስም “እንግዲያውስ ንጉሥ ነህን?” አለው። ኢየሱስም መልሶ “እኔ ንጉሥ እንደሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ተወልጃለሁ፤ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ጲላ​ጦ​ስም፥ “እን​ግ​ዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላ​ለህ፤ እኔ ስለ​ዚህ ተወ​ለ​ድሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ለእ​ው​ነት ልመ​ሰ​ክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእ​ው​ነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰ​ማ​ኛል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ጲላጦስም፦ “እንግዲያ ንጉሥ ነህን?” አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ትላለህ። እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 18:37
26 Referencias Cruzadas  

እነሆ እርሱን ለሕዝቦች ምስክር፥ መሪና አለቃ አድርጌዋለሁ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “አንተ እንዳልከው ነው፤ ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ታዩታላችሁ፤ እንዲሁም በሰማይ ደመና ሆኖ ሲመጣ ታዩታላችሁ እላችኋለሁ።”


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ወደ ገዢው ወደ ጲላጦስ ፊት ቀረበ፤ ገዢውም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ጠየቀው፤ ኢየሱስም “አንተ እንዳልከው ነው” ሲል መለሰ።


ኢየሱስም “አዎ፥ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ታያላችሁ! እንዲሁም በሰማይ ደመና ተመልሶ ሲመጣ ታያላችሁ” አለ።


ጲላጦስም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ኢየሱስም “አንተ እንዳልከው ነው፤” አለው።


ሁሉም በአንድነት “ታዲያ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህን?” ሲሉ ጠየቁት። እርሱም “አዎ፥ እናንተ እንዳላችሁት ነው” አላቸው።


ጲላጦስም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ኢየሱስን ጠየቀው። ኢየሱስም “አንተ እንዳልከው ነው” አለው።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በመካከላችን ኖረ፤ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ እንዳለው ያለውን ክብሩን አይተናል።


ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጠ፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።


እርሱ ያየውንና የሰማውን ይመሰክራል፤ ነገር ግን የእርሱን ምስክርነት የሚቀበል የለም።


የላከኝን ፈቃድ ማድረግ የሚፈልግ ቢኖር ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር የተገኘ ወይም እኔ ከራሴ የተናገርኩት መሆኑን ያውቃል።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ምንም እንኳ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ከየት እንደ መጣሁ፥ ወዴትም እንደምሄድ ስለማውቅ ምስክርነቴ እውነት ነው፤ እናንተ ግን ከየት እንደ መጣሁና ወዴት እንደምሄድ አታውቁም።


እኔ ግን እውነትን ስለምናገር አታምኑኝም፤


ለመሆኑ ከእናንተ ‘ኃጢአተኛ ነህ’ ብሎ የሚወቅሰኝ ማን ነው? እውነትን የምናገር ከሆንኩ ታዲያ፥ ለምን አታምኑኝም?


ከእግዚአብሔር የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማል፤ እንግዲህ እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል የማትሰሙት ከእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ ነው።”


ለሁሉ ነገር ሕይወት በሚሰጠው በእግዚአብሔርና በጴንጤናዊው ጲላጦስ ፊት በመልካም መታመን በመሰከረው በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አዝሃለሁ።


ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


ለእናንተ የምጽፍላችሁ እውነትን ስለማታውቁ አይደለም፤ እናንተስ እውነትን ታውቃላችሁ፤ በእውነትም ሐሰት እንደማይገኝ ታውቃላችሁ።


እኛ ወንድሞቻችንን ስለምንወድ ከሞት ወደ ሕይወት መሸጋገራችንን እናውቃለን። ፍቅር የሌለው ሰው በሞት ጥላ ውስጥ ይኖራል።


በዚህም እውነተኞች መሆናችንንና ወደ እግዚአብሔር ፊት ያለ ስጋት በመተማመን ለመቅረብ የምንችል መሆናችንን እናውቃለን።


እኛ የእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ሁሉ ይሰማናል፤ የእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም። እውነተኛን መንፈስና ሐሰተኛን መንፈስ ለይተን የምናውቀው በዚህ ነው።


የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።


ከዮሐንስ ለሰባቱ የእስያ አብያተ ክርስቲያን። ካለው፥ ከነበረውና፥ ከሚመጣው ከእግዚአብሔር፥ በዙፋኑ ፊት ካሉት ከሰባቱ መንፈሶች፥ እንዲሁም ከሞት በመነሣት በኲር ከሆነው የምድር ነገሥታት ገዢ፥ ታማኝ ምስክር ከሆነው፥ ከሚወደንና በደሙ ከኃጢአታችን ነጻ ካወጣን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።


“ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ፥ አሜን ከሆነው፥ ታማኝና እውነተኛ ምስክር ከሆነው፥ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ መገኛ ከሆነው የተነገረ ነው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos