Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ዮሐንስ 1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ለተመረጠችው እመቤትና ለልጆችዋ፤ ከእኔ ከሽማግሌው የተላከ መልእክት፤ እኔ በእውነት እወዳችኋለሁ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ይወዱአችኋል፤

2 ይህም እውነት በመካከላችን ያለና ወደ ፊትም ለዘለዓለም ከእኛ ጋር የሚኖር ነው።

3 የእግዚአብሔር አብና የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእውነትና በፍቅር ከእኛ ጋር ይሁን።


ስለ እውነትና ስለ ፍቅር

4 ከልጆችሽ አንዳንዶቹ አብ ባዘዘን መሠረት በእውነት ጸንተው በማግኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል።

5 እመቤት ሆይ፥ አሁንም ዐደራሽን፥ ይህ የምጽፍልሽ አዲስ ትእዛዝ አይምሰልሽ፤ አሁን የምጽፍልሽ “እርስ በርሳችን እንዋደድ” የሚለውን ከመጀመሪያ አንሥቶ በእኛ ዘንድ የነበረውን ትእዛዝ ነው።

6 እውነተኛ ፍቅር ማለት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መፈጸም ነው። ይህም ትእዛዝ በመጀመሪያ እንደ ሰማችሁት “በፍቅር ኑሩ” የሚል ነው።

7 ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በሥጋ መገለጡን የማያምኑ ብዙ አሳሳቾች በዓለም ተነሥተዋል። እንዲህ ያለው ሰው አታላይና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።

8 እናንተ ግን ሙሉ ዋጋችሁን ለመቀበል ትጉ፤ የሠራችሁትም እንዳይጠፋባችሁ ተጠንቀቁ።

9 በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የማይኖርና ከእርሱም ርቆ የሚሄድ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የለም፤ በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የሚኖር ሰው ግን አብና ወልድ ከእርሱ ጋር አሉ።

10 ይህን ትምህርት ሳይዝ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምታም እንኳ አትስጡት።

11 ሰላምታም የሚሰጠው ሰው የክፉ ሥራው ተባባሪ ይሆናል።


የመጨረሻ ሰላምታ

12 ልጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ነበረኝ፤ ነገር ግን ሁሉንም በደብዳቤ ልገልጸው አልፈልግም፤ ይልቅስ ደስታችን ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ መጥቼ ቃል በቃል ላነጋግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።

13 የተመረጠችው የእኅትሽ ልጆች ሰላምታ ያቀርቡልሻል።

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos