ኤርምያስ 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ በአንደበታቸው ሐሰት ለመናገር ዘወትር የተዘጋጁ ናቸው፤ ስለዚህም በምድሪቱ ላይ በእውነት ፈንታ ሐሰት ነግሦአል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ከአንዱ ኃጢአት ወደ ሌላው ኃጢአት ይተላለፋሉ፤ የእኔንም አምላክነት ዐውቀው አላከበሩኝም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሐሰትን ለመናገር፣ ምላሳቸውን እንደ ቀስት ገተሩ፤ በእውነት ሳይሆን፣ በሐሰት በምድሪቱ ገነኑ፤ ከክፋት ወደ ክፋት ሄዱ፤ እኔንም አላወቁኝም፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምላሳቸውን ለሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድርም በረቱ፤ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፥ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፥ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና እኔንም አላወቁምና፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ሕዝቡም እርስ በርሱ አንዱ ሌላውን ለመጨቈን ባልንጀራ በባልንጀራው ላይ ይነሣሣል፤ ወጣቱ ሽማግሌውን አያከብርም፤ ተንቆ ይኖር የነበረውም ሰው ክብር ባለው ሰው ላይ ይታበያል።
እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።
የሕዝቡ ክፋት ኲርንችቱንና እሾኹን እንደሚያቃጥል እሳት ነው፤ እንደ በረሓ እሳት ደኑን በሚያቃጥልበት ጊዜ ጢሱ ተትጐልጒሎ ሲወጣ ቀጥ ብሎ የቆመ ዐምድ ይመስላል።
ወንድሞችህና የቅርብ ዘመዶችህ ከድተውሃል፤ በአንተ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፤ ስለዚህ በፊትህ ስለ አንተ መልካም ነገር ቢናገሩም አትመናቸው።”
ከእንግዲህ ወዲህ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ ባልንጀራውንም ሆነ ወንድሙን የሚያስተምር ማንም አይኖርም፤ ከትልቁ ጀምሮ እስከ ትንሹ ሁሉም ያውቁኛል፤ በደላቸውን ይቅር እልላቸዋለሁ፤ ኃጢአታቸውንም አላስታውስባቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ እኔን የማያውቁ ሞኞች ሆነዋል፤ ማስተዋል ስለ ጐደላቸው እንደ ሕፃናት የሚታለሉ ናቸው፤ ክፉ ነገር ለመሥራት የተራቀቁ ብልኆች ናቸው፤ መልካም ነገር ማድረግ ግን ከቶ አይሆንላቸውም።”
ከዚህ በኋላ እኔ እንደዚህ አልኩ፥ “የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ሕግ ስላላወቁ፤ እነዚህ ድኾችና ማስተዋል የጐደላቸው ሰነፎች ናቸው፤ መንገዱንም አይከተሉም።
እንግዲህ በሥልጣን ላይ ወዳሉት ገዢዎች ሄጄ፥ ከእነርሱ ጋር እነጋገራለሁ፤ በእርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉ፤” ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀዋል፤ ለእርሱም መታዘዝ እምቢ ብለዋል።
ሁሉም ባልንጀራውን በማሞኘት ያሳስታል፤ እውነት የሚናገርም የለም፤ አንደበታቸው ውሸት መናገርን እንዲለማመድ አድርገውታል፤ ኃጢአት በመሥራት ሰውነታቸውን ያደክማሉ።
አንደበታቸው ዘወትር ተንኰል ስለሚናገር፥ እንደ አደገኛ ፍላጻ ነው፤ እያንዳንዱ ባልንጀራውን በፍቅር ቃል ያነጋግረዋል፤ ነገር ግን በስውር ወጥመድ ይዘረጋበታል።
ከዚያን በኋላ ሁለቱ ነገሥታት በልባቸው ተንኰል እንደ ያዙ አብረው ለመመገብ በአንድ ገበታ ይቀመጣሉ፤ አንዱ ሌላውን ለማታለል የሐሰት ቃላት ይለዋወጣሉ፤ ሆኖም የተወሰነው ጊዜ ገና ስለ ሆነ እንዳሰቡት አይከናወንላቸውም።
በዚህ በከሐዲና በኃጢአተኛ ትውልድ ፊት በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ እኔም የሰው ልጅ በአባቴ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር ስመጣ በእርሱ አፍርበታለሁ።”
እኔ በወንጌል ቃል አላፍርም፤ የወንጌል ቃል በመጀመሪያ አይሁድን፥ ቀጥሎም አሕዛብን፥ እንዲሁም የሚያምኑትን ሰዎች ሁሉ ማዳን የሚችል የእግዚአብሔር ኀይል ነው።
ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ፤ የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤
ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትም አትሥሩ፤ በእናንተ መካከል አንዳንዶች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉ። ይህንንም የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው።
ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ድፍረታችሁ ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳኛችሁ ምልክት ነው።
ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ በብርቱ ፈልጌ ነበር፤ አሁን ግን በማያዳግም ሁኔታ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አንድ ጊዜ ስለ ሰጠው እምነት በብርቱ እንድትጋደሉ ለመምከር ልጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።
ከዚህም የተነሣ እርስዋ በሠርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ አለቀሰች፤ አጥብቃም ስለ ነዘነዘችው የእንቆቅልሹን ፍች በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርስዋም ሄዳ ለፍልስጥኤማውያኑ ነገረቻቸው።