ኤርምያስ 9:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የማደርገውን ነገር ልንገራችሁ፤ ይህ ሕዝብ ምግቡ መራራ መጠጡም የተመረዘ ውሃ እንዲሆንበት አደርጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ይህን ሕዝብ መራራ ምግብ አበላዋለሁ፤ የተመረዘንም ውሃ አጠጣዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይህን ሕዝብ መከራን አበላዋለሁ፤ የሐሞትንም ውኃ አጠጣዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣዋለሁ። |
እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤ በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤ እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል።
የሰዎች ኲራት ይጠፋል፤ እብሪት የሞላበት ትዕቢታቸውም ያከትማል፤ ጣዖቶች ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ብቻ በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
“እንግዲህ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም ነቢያት የምለው ይህ ነው፦ ‘በምድሪቱ ሁሉ ላይ የክሕደትን መንፈስ ስላሠራጩ፥ መራራ ቅጠል እንዲበሉና መርዝ እንዲጠጡ አደርጋቸዋለሁ።’ ”
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ይህን በቊጣዬ ወይን የተሞላ ጽዋ ከእጄ ውሰድ እኔ ወደምልክህ ሕዝቦች ሄደህ ከእርሱ እንዲጠጡ አድርግ።
የዔላም ሕዝብ ሕይወታቸውን ሊያጠፉ የሚፈልጉትን ጠላቶቻቸውን እንዲፈሩ አደርጋለሁ። በእነርሱም ላይ ለጥፋታቸው ምክንያት የሆነው ኀይለኛ ቊጣዬን አመጣባቸዋለሁ፤ እስኪያልቁ ድረስ በጦርነት እንዲሳደዱ አደርጋለሁ።
የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ዝም ብለን መቀመጣችን ለምንድን ነው? አምላካችን እግዚአብሔር ሞት ፈርዶብናል፤ እርሱን ስለ በደልን የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ አድርጎናል። ኑ! ወደተመሸጉ ከተሞች ሮጠን እዚያ እንሙት፤
ከሕዝባችሁ አንድ ሦስተኛው እጅ በራብና በበሽታ ያልቃል፤ አንድ ሦስተኛው ከከተማው ውጪ በሰይፍ ይገደላል፤ ሌላው ሦስተኛ እጅ በአራቱ ማእዘን በነፋስ እንዲበተን አድርጌ በኋላ በሰይፍ አሳድደዋለሁ።
ከበባው ከተፈጸመ በኋላ ከሦስቱ አንዱን እጅ የከተማውን ንድፍ በሠራህበት ጡብ መካከል አቃጥለው፤ ሁለተኛውን አንድ ሦስተኛ እጅ ቈራርጠህ የከተማው ንድፍ በተሠራበት ጡብ ዙሪያ አኑረው። ሦስተኛውን አንድ ሦስተኛ እጅ ደግሞ ለነፋስ በትነው፤ እኔም በሰይፍ አሳድደዋለሁ።
“እግዚአብሔር አንተንና ንጉሥህን ከዚህ በፊት የቀድሞ አባቶችህም ሆኑ አንተ ወዳልነበራችሁበት ባዕድ አገር አፍልሶ ይወስዳችኋል፤ በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ባዕዳን አማልክትን ታመልካላችሁ።
በዚህ ከቆማችሁት መካከል ማንም ወንድ ወይም ሴት፥ ቤተሰብ ወይም ነገድ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ፈቀቅ በማለት የሌሎችን ሕዝቦች አማልክት የሚከተል እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ በመካከላችሁ እንደዚህ ያለ መርዘኛና መራራ የሆነ ሥራ የሚሠራ አይኑር፤