Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 44:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ደግ ነገር ሳይሆን ክፉ ነገር እንዲደርስባችሁ አደርጋለሁ፤ ከእናንተ አንድ እንኳ ሳይተርፍ ሁላችሁም በጦርነትና በረሀብ ትሞታላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ለመልካም ሳይሆን ለክፉ እተጋባቸዋለሁና፤ በግብጽ የሚኖሩ አይሁድ ፈጽሞ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ይደመሰሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እነሆ፥ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት በእነርሱ ላይ እመለከታለሁ፤ በግብጽም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እነሆ ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክ​ፋት እተ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ያሉት የይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ ያል​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እነሆ፥ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት እተጋባቸዋለሁ፥ በግብጽም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 44:27
16 Referencias Cruzadas  

ከጥፋት የተረፈውን ሕዝቤን ለጠላቶቹ ተላልፎ እንዲሰጥ እተወዋለሁ፤ እርሱም ይማረካል፤ ንብረቱም ይዘረፋል።


እነሆ መንቀልና ማፍረስ፥ ማጥፋትና መገለባበጥ፥ ማነጽና መትከል እንድትችል በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ።”


ይህች ከተማ እንድትጠፋ ወስኛለሁ፤ ፈጽሞም ምሕረት አላደርግላትም፤ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ እሰጣታለሁ፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እነርሱን ለመንቀልና ለማፍረስ፥ ለመገለባበጥና ለማጥፋት፥ ለመደምሰስም እከታተል የነበርኩትን ያኽል፥ እነርሱን እንደገና ለመትከልና ለማነጽም እከታተላለሁ።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ እንዲህ ብዬ እንድነግረው አዘዘኝ፦ “ልክ ከዚህ በፊት እንደ ተናገርኩት በዚህች ከተማ ላይ ብልጽግናን ሳይሆን ጥፋትን አመጣለሁ፤ በዚህችም ከተማ ሆነህ ይህ ሁሉ ሲፈጸም በዐይንህ ታያለህ፤


ያ የምትፈሩት ጦርነት ይደርስባችኋል፤ የምትፈሩትም ራብ ተከትሎአችሁ ይሄዳል፤ በዚያም በግብጽ ትሞታላችሁ።


በይሁዳ ከስደት ከተረፉት መካከል ወደ ግብጽ ወርደው በዚያ ለመኖር የወሰኑትን ሁሉ እንዲጠፉ አደርጋለሁ፤ ከትልቅ እስከ ትንሽ በጦርነት ወይም በረሀብ በግብጽ አገር ይሞታሉ። እነርሱም ለሕዝቦች አስደንጋጭ ይሆናሉ፤ ሕዝብም ሁሉ ይዘባበትባቸዋል፤ ስማቸውንም መራገሚያ ያደርጉታል።


ኢየሩሳሌምን በጦርነት፥ በራብና በቸነፈር እንደቀጣሁ፥ በግብጽ የሚኖሩትንም እቀጣለሁ፤


በይሁዳ ከስደት ተርፈው ወደ ግብጽ ወርደው ከሚኖሩት መካከል አንድ እንኳ የሚያመልጥ ወይም የሚተርፍ አይኖርም፤ እንደገና ይኖሩባት ዘንድ ወደሚናፍቋት ወደ ይሁዳ የሚመለስ ማንም አይኖርም፤ ከጥቂት ስደተኞች በቀር ተመልሶ የሚመጣ አይኖርም።”


ነገር ግን ለሰማይ ንግሥት የሚቃጠል መሥዋዕትና ለእርስዋም የወይን ጠጅ መባ ማቅረብን ካቋረጥንበት ጊዜ ጀምሮ ምንም ያተረፍነው ነገር የለም፤ ሕዝባችንም በጦርነትና በረሀብ አልቆአል።”


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የማደርገውን ነገር ልንገራችሁ፤ ይህ ሕዝብ ምግቡ መራራ መጠጡም የተመረዘ ውሃ እንዲሆንበት አደርጋለሁ።


እነርሱም ሆኑ የቀድሞ አባቶቻቸው በማያውቁአቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፤ እስከማጠፋቸውም ድረስ በሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።”


ከሕዝባችሁ አንድ ሦስተኛው እጅ በራብና በበሽታ ያልቃል፤ አንድ ሦስተኛው ከከተማው ውጪ በሰይፍ ይገደላል፤ ሌላው ሦስተኛ እጅ በአራቱ ማእዘን በነፋስ እንዲበተን አድርጌ በኋላ በሰይፍ አሳድደዋለሁ።


መጨረሻው መጥቶአል፤ መጨረሻው ደርሶአል፤ በእናንተ ላይ ተነሥቶአል፤ እነሆ፥ መጥቶአል።


አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ! አንተ በሥራህ ሁሉ እውነተኛ ነህ፤ እኛ ግን ስለ አልታዘዝንህ ይህን ሁሉ መከራ አመጣህብን።


እኔ ጌታ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኛው የእስራኤል መንግሥት እመለከታለሁ፤ እርስዋንም ከምድር ገጽ አጠፋለሁ፤ ሆኖም የያዕቆብን ዘር ሙሉ በሙሉ አልደመስስም። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos