Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 75:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር የተቀመመ ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ በእጁ ይዞአል፤ በቊጣው ሲያፈስሰው ክፉዎች ሁሉ ይጠጡታል፤ እስከ መጨረሻው ጠብታ ድረስ ይጨልጡታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በእግዚአብሔር እጅ ጽዋ አለ፤ በሚገባ የተቀመመና ዐረፋ የሚወጣው የወይን ጠጅ ሞልቶበታል፤ ይህን ከውስጡ ወደ ውጭ ገለበጠው፤ የምድር ዐመፀኞችም አተላውን ሳይቀር ይጨልጡታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህንን ያዋርዳል ያንንም ያከብራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ፍር​ድን ከሰ​ማይ ታሰ​ማ​ለህ። ምድር ፈራች፥ ዝምም አለች፥

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 75:8
15 Referencias Cruzadas  

ኃጢአተኞች ራሳቸው በሠሩት በደል ቅጣታቸውን ይቀበሉ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ቊጣውን ያውርድባቸው፤


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ይህን በቊጣዬ ወይን የተሞላ ጽዋ ከእጄ ውሰድ እኔ ወደምልክህ ሕዝቦች ሄደህ ከእርሱ እንዲጠጡ አድርግ።


በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል፤ የሚጋረፍ ነፋስም የእነርሱ ዕድል ፈንታ ነው።


ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የአሕዛብ ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔር ታላቂቱን ባቢሎንን አስታወሰ፤ የብርቱ ቊጣው ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ እንድትጠጣም አደረጋት።


ስለዚህ ጽዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ወሰድኩና እግዚአብሔር ወደ ላከኝ ሕዝቦች ሁሉ ሄጄ እንዲጠጡት አደረግሁ፤


የወይን ጠጅ በመጠጣት ጀግኖች፥ የሚያሰክረውንም መጠጥ ለማደባለቅ ደፋሮች ለሆኑ ወዮላቸው!


በሕዝብህ ላይ የችግር ቀን አመጣህ፤ እንድንንገዳገድ ያደረገንን የወይን ጠጅንም ሰጠኸን።


የሕዝቡን አቤቱታ የሚመለከተው አምላካችሁ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እንደ ሰከረ ሰው የሚያንገዳግደውን የመከራ ጽዋ ከእጃችሁ ወስጄአለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ኀይለኛ ቊጣዬን ከትልቁ ዋንጫ አትጠጡም።


ይህ ሁሉ ነገር የሚደርሰው ብዙ የወይን ጠጅ በመጠጣትና ድብልቅ የሆኑ ጠንካራ መጠጦችን በመለማመድ ጊዜውን በሚያባክን ሰው ላይ ነው።


አንቺ ከእግዚአብሔር እጅ የሚያንገዳግደውን የቊጣውን ጽዋ በትልቅ ዋንጫ ጨልጠሽ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ! ንቂ፤ ተነሥተሽም ቁሚ!


የእግዚአብሔር ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ወደ እነርሱ ያዘነብላሉ፤ የሚነግሩአቸውንም ሁሉ ይቀበላሉ።


እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ ያዋርዳል፤ ከፍ፥ ከፍም ያደርጋል።


ምንም ሳታስቀሪ ጨልጠሽ ትጠጪዋለሽ፤ ጽዋውንም ሰባብረሽ በስባሪው በሐዘን ጡቶችሽን ትቈራርጪአለሽ። እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios