ኤርምያስ 50:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለአሕዛብ ሁሉ በማወጅ ወሬውን ንገሩ! አርማ አንሥታችሁ ዜናውን አስታውቁ! ከቶ ምሥጢር አድርጋችሁ አታስቀሩ! እነሆ ባቢሎን ተያዘች፤ ቤል የተባለው ጣዖት እንዲያፍር ተደረገ፤ ‘ማርዱክ’ የተባለ ጣዖቷም ተሰባብሮአል፤ የባቢሎን ጣዖቶች አፍረዋል፤ አጸያፊ ምስሎችዋም ተሰባብረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፤ አስታውቁም፤ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ዐውጁ፤ አንዳች ሳታስቀሩ፣ እንዲህ በሉ፤ ‘ባቢሎን ትያዛለች፤ ቤል ይዋረዳል፤ ሜሮዳክ በሽብር ይሞላል፤ ጣዖቶቿ ይዋረዳሉ፤ አማልክቷም ይሸበራሉ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውጁም፥ ዓላማውንም አንሡ፤ አውጁ፥ ሳትደብቁም እንዲህ በሉ፦ ባቢሎን ተያዘች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ተሰባበረ፤ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ተሰባበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአሕዛብ ተናገሩ፤ አውሩም፤ ዓላማውንም አንሡ፥ አትደብቁ፦ ባቢሎን ተያዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮዳክ ፈራች፤ ምስሎችዋም አፈሩ፤ ጣዖታቷም ደነገጡ፤ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውሩም፥ ዓላማውንም አንሡ፥ አውሩ፥ አትደብቁ፦ ባቢሎን ተወሰደች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ደነገጠ፥ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ደነገጡ በሉ። |
በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ “እግዚአብሔርን አመስግኑ! ስሙንም አክብሩ! በሕዝቦች መካከል እርሱ ያደረገውን ተናገሩ! ስለ ገናናነቱም መስክሩ!
ጥንድ ጥንድ ሆነው በፈረስ የተቀመጡ ሰዎች እነሆ በድንገት ይመጣሉ፤ ዘብ ጠባቂውም “እነሆ ባቢሎን ወደቀች! የሚሰግዱላቸውም ጣዖቶች ሁሉ ተሰባብረው ወደቁ” የሚል ዜና ያስተላልፋል።
በዚያን ዘመን የባቢሎን ንጉሥ የባላዳን ልጅ መሮዳክ ባላዳን ንጉሥ ሕዝቅያስ ታሞ መዳኑን ሰማ፤ ስለዚህም ከገጸ በረከት ጋር ደብዳቤ ላከለት።
“ቤልና ኔቦ የተባሉት የሐሰት አማልክት ያጐነብሳሉ፤ ጣዖቶቻቸው በጭነት እንስሶች ላይ ተጭነዋል፤ የተጫኑት ምስሎች ለደካማ እንስሳ ከባዶች ናቸው።
እንግዲህ ከባቢሎን ወጥታችሁ ሽሹ፤ “እግዚአብሔር አገልጋዩን እስራኤልን አድኖአል” የሚለውን የምሥራች ቃል በደስታ አብሥሩ፤ በየስፍራውም እንዲታወቅ አድርጉ።
“እኔ የተናገርኩትን ሰምታችኋል፤ ይህም መፈጸሙን አይታችኋል፤ አስተውሉትና እውነተኛነቱን አረጋግጡ፤ ከአሁን ጀምሮ ቀድሞ ተሰውሮ የነበረ እናንተ ያላወቃችሁትን አዲስ ነገር ወደፊት አሳያችኋለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሆይ! አድምጡኝ፤ በሩቅ ጠረፎችም ቃሌን ዐውጁ፤ እኔ ሕዝቤን በትኜ ነበር፤ አሁን ግን እሰበስባቸዋለሁ፤ እረኛ መንጋውን እንደሚጠብቅም እጠብቃቸዋለሁ።
ለጽዮን መንገዱን አመልክቱአት! ሳትዘገዩ የደኅንነት ዋስትና ወደሚገኝበት ስፍራ ሽሹ! እግዚአብሔር ከሰሜን በኩል መቅሠፍትና ታላቅ ጥፋት ሊያመጣ ነው።
“የግብጽ ከተሞች በሆኑት በሚግዶል፥ በሜምፊስ በጣፍናስ ይህን ቃል ዐውጅ፤ ‘ራሳችሁን ለመከላከል ተዘጋጁ፤ በዙሪያችሁ ያለው ሁሉ በጦርነት ይጠፋል።
በባቢሎን ቅጥር ላይ አደጋ ጣሉ የሚል ምልክት አሳዩ! ጥበቃውን አጠናክሩ! ሰላዮችን መድቡ! ደፈጣ ተዋጊዎችንም አዘጋጁ፤ ይህንንም የምታደርጉት እግዚአብሔር በባቢሎን ሕዝብ ላይ ያቀደውንና የተናገረውን ተግባራዊ ስለሚያደርግ ነው።
“አደጋ ለመጣል የሚያስችል ምልክት ስጡ! ሕዝቦች ሁሉ መስማት እንዲችሉ እምቢልታ ንፉ! ባቢሎንን ይወጉ ዘንድ ሕዝቦችን አዘጋጁ! የአራራት፥ የሚኒና የአሽኬናዝ መንግሥታት አደጋ እንዲጥሉ ንገሩአቸው፤ የጦር አዛዥ የሚሆን ሰው ሹሙ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ፈረሶችን አምጡ።
የእርሱ ከተማ ከዳር እስከ ዳር የተያዘች መሆንዋን ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንዱ ሩዋጭ ለሌላው ሩዋጭ፥ አንዱ መልእክተኛ ለሌላው መልእክተኛ መልእክቱን ለማስተላለፍ ይሯሯጣሉ።
የባቢሎን ጣዖት የሆነውን ቤልን እቀጣለሁ፤ የተሰረቁ ዕቃዎቹንም ከእጁ አስጥላለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህም አሕዛብ አይሰግዱለትም።” “የባቢሎን ቅጽሮች ወድቀዋል፤
ስለዚህም የባቢሎንን ጣዖቶች የማስወግድበት ጊዜ ይመጣል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ኀፍረት ይደርሳል፤ የተገደሉባት ልጆችዋ ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።
እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው። በባቢሎን ጣዖቶች ላይ የምፈርድበትና በሀገሪቱም የሚገኙ ቊስለኞች የጭንቀት ድምፅ የሚያሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤
የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ኤዌል መሮዳክ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ኢኮንያንን ከእስር ፈታው።
እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምንና የቤተ መቅደሱንም ንዋያተ ቅድሳት በከፊል ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ ንጉሡም ንዋያተ ቅድሳቱን በባቢሎን ባሉት የጣዖት አማልክቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖረ።
ናቡከደነፆርም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ሲድራቅ፥ ሚሳቅና አብደናጎ! አማልክቴን አለማምለካችሁና ላቆምኩትም የወርቅ ምስል አለመስገዳችሁ እርግጥ ነውን?
በምድራቸው ያሉትን ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በማጥፋቱ እግዚአብሔር በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በባሕር ጠረፍና በደሴቶች የሚኖሩ መንግሥታት ሁሉ በያሉበት ለእርሱ ይሰግዳሉ።
ከፍ ባለ ድምፅም እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ ሆነች! የርኩሳን መናፍስት ማደሪያ ሆነች! የሚያጸይፉና የሚያስጠሉ ወፎች መጠለያ ሆነች!