Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 10:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ጣዖቶች ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ መሆናቸውንና አንተ እግዚአብሔር ጣዖቶችን ሁሉ እንደምትደመስስ ንገራቸው” አልከኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “እናንተም፣ ‘እነዚህ ሰማያትንና ምድርን ያልፈጠሩ አማልክት ከምድር ላይ፣ ከሰማያትም በታች ይጠፋሉ’ ትሏቸዋላችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እናንተም፦ “ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ” ትሉአቸዋላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እና​ን​ተም፦ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ያል​ፈ​ጠሩ እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ከም​ድር ላይ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ፈጽ​መው ይጥፉ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እናንተም፦ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ ትሉአቸዋላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 10:11
14 Referencias Cruzadas  

ሌሎች ሕዝቦች የሚሰግዱላቸው አማልክት ጣዖቶች ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን የፈጠረ አምላክ ነው።


በዚያን ጊዜ የጣዖቶችን ስሞች ከምድሪቱ ላይ አስወግዳለሁ፤ ዳግመኛም የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤ የጣዖት ነቢያትንና ርኩሳን መናፍስትን አስወግዳለሁ።


በምድራቸው ያሉትን ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በማጥፋቱ እግዚአብሔር በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በባሕር ጠረፍና በደሴቶች የሚኖሩ መንግሥታት ሁሉ በያሉበት ለእርሱ ይሰግዳሉ።


እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አሳዳቸው፤ ከሰማያትም በታች ደምስሳቸው!”


እነዚህ አማልክት ዋጋቢሶችና የፌዝ ዕቃዎች ናቸው፤ እግዚአብሔር ለፍርድ በሚገለጥበት ጊዜ ይደመሰሳሉ።


እነዚህ አማልክት ዋጋ ቢሶችና የፌዝ ዕቃዎች ናቸው፤ እግዚአብሔር እነርሱን ለመቅጣት በሚገለጥበትም ጊዜ ይደመሰሳሉ።


ዘንዶውንም ይዞ ሺህ ዓመት አሰረው፤ ይህም ዘንዶ ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን የሚባለው የቀድሞው እባብ ነው፤


በተከታዩም ቀን ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ የምስሉ ሐውልት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እንደገና ወድቆ አዩት፤ በዚህ ጊዜ ራሱና ሁለት እጆቹ ተሰባብረው በመግቢያው መድረክ ላይ ወድቀው ሌላው አካሉ ብቻ ቀርቶ ነበር።


ትክክል ናቸው ብላችሁ የምታስቡአቸውን ሥራዎቻችሁን አጋልጣለሁ፤ ጣዖቶቻችሁም ሊረዱአችሁ አይችሉም።


በግብጽ የጣዖትን ቤተ መቅደሶች ያቃጥላል፤ ጣዖቶቹን ይማርካል፤ እረኛ ለምዱን እንደሚደርብ ግብጽን በግዛቱ ላይ ደርቦ ምንም ጒዳት ሳይደርስበት በድል አድራጊነት ይወጣል።


በግብጽ ውስጥ በሄሊዮፖሊስ ከተማ የሚገኙትን ከድንጋይ የተሠሩ ሐውልቶችን ይደመስሳል፤ የግብጻውያንን ጣዖቶችንና ቤተ መቅደሶችን ያቃጥላል።”


“ለአሕዛብ ሁሉ በማወጅ ወሬውን ንገሩ! አርማ አንሥታችሁ ዜናውን አስታውቁ! ከቶ ምሥጢር አድርጋችሁ አታስቀሩ! እነሆ ባቢሎን ተያዘች፤ ቤል የተባለው ጣዖት እንዲያፍር ተደረገ፤ ‘ማርዱክ’ የተባለ ጣዖቷም ተሰባብሮአል፤ የባቢሎን ጣዖቶች አፍረዋል፤ አጸያፊ ምስሎችዋም ተሰባብረዋል።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሜምፊስ ያሉትን ጣዖቶችና የሐሰት አማልክት ሁሉ አወድማለሁ፤ በግብጽ ምድር ላይ ገዢ ሆኖ የሚነሣ አይኖርም፤ በሕዝቡም ላይ ፍርሀትን አወርዳለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios