Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 46:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “የግብጽ ከተሞች በሆኑት በሚግዶል፥ በሜምፊስ በጣፍናስ ይህን ቃል ዐውጅ፤ ‘ራሳችሁን ለመከላከል ተዘጋጁ፤ በዙሪያችሁ ያለው ሁሉ በጦርነት ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ይህን በግብጽ ተናገር፤ በሚግዶልም አሰማ፤ በሜምፊስና በጣፍናስም እንዲህ ብለህ ዐውጅ፤ ‘በቦታችሁ ቁሙ፤ ተዘጋጁም፤ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰይፍ ይበላቸዋልና።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በግብጽ አውጁ፥ በሚግዶልም አሰሙ፥ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ እናንተም፦ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና ተነሥ ራስህንም አዘጋጅ በሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “በግ​ብፅ ተና​ገሩ፤ በሚ​ግ​ዶ​ልም አውሩ፤ በሜ​ም​ፎ​ስና በጣ​ፍ​ናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙ​ሪ​ያህ ያለ​ውን በል​ቶ​አ​ልና፦ ተነሥ ተዘ​ጋ​ጅም በሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በግብጽ ተናገሩ፥ በሚግዶልም አሰሙ፥ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፥ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 46:14
23 Referencias Cruzadas  

አበኔርም፥ ኢዮአብን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “ዘለዓለም ስንዋጋ እንኖራለንን? ፍጻሜውስ መራር መሆኑን አትገነዘብምን? ሰዎችህ እኛን ወንድሞቻቸውን ከማሳደድ እንዲገቱ ትእዛዝ የማትሰጣቸው እስከ መቼ ነው?”


“እስራኤላውያን ተመልሰው፥ በሚግዶልና በቀይ ባሕር መካከል ባለው ፒሃሒሮት ፊት ለፊት በባዓልጸፎን አጠገብ እንዲሰፍሩ ንገራቸው።


እምቢ ብትሉኝና ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ራሴ እግዚአብሔር ነኝ።”


የጾዓን ባለ ሥልጣኖች ሞኞች ሆኑ፤ የሜምፊስ መሪዎችም ተታለሉ፤ የሕዝብዋ ከፍተኛ አማካሪዎች ግብጽን አሳትዋት።


ከዚያ በኋላ አሦራውያን የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃሉ።


ለመሥዋዕት የቀረቡ የበግና የፍየል ጠቦቶች በሚሠዉበት ጊዜ ደማቸውና ስባቸው ሰይፉን እንደሚሸፍን የእርሱም ሰይፍ በኤዶማውያን ደምና ስብ ይሸፈናል፤ እግዚአብሔር ይህን መሥዋዕት በቦጽራ ከተማ፥ ይህንንም ታላቅ ዕርድ በኤዶም ምድር ያቀርባል።


በረሓማ ከሆነው ከባዶ ተራራ አጥፊዎች ይመጣሉ፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ሀገሪቱን ከዳር እስከ ዳር ስለሚያጠፋ አንድም ሰው አይድንም።


የሜምፊስና የጣፊናስ ሰዎች፥ መኻል አናትሽን ይላጩሻል።


ከቶ የምትታረሙ ስላልሆናችሁ፥ እኔ እናንተን መቅጣቴ ከንቱ ነው፤ እንደ ተቈጣ አንበሳ ሆናችሁ ነቢያቶቻችሁን በሰይፍ ገደላችሁ።


በሰሜን ግብጽ ውስጥ ሚግዶል፥ ጣፍናስና ሜምፊስ ተብለው በሚጠሩት ከተሞችና በአገሪቱም ደቡባዊ ክፍል ተበታትነው ስለሚኖሩት እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤


ይህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የመረጠው ቀን ነው፤ እርሱ ዛሬ የበቀል እርምጃ ይወስዳል፤ ጠላቶቹንም ይቀጣል። የእርሱም ሰይፍ ብዙዎችን ይበላል፤ በደማቸውም ይለወሳል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኙ ምርኮኞቹን መሥዋዕት ያደርጋቸዋል።


የግብጽ ሕዝብ ሆይ! ተማርካችሁ የምትሄዱ ስለ ሆነ ዕቃችሁን አዘጋጁ፤ ሜምፊስ ፈራርሳ ሰው የማይኖርባት በረሓ ትሆናለች፤


“የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ ስለ ዐሞናውያንና ስለ ስድባቸው እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውን እንዲህ ብለህ አስታውቃቸው፤ ‘አጥፊ ሰይፍ ተዘጋጅቶአል፤ ለመግደልና ለማውደም እንደ መብረቅም ለማብለጭለጭ ተወልውሎአል!’


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሜምፊስ ያሉትን ጣዖቶችና የሐሰት አማልክት ሁሉ አወድማለሁ፤ በግብጽ ምድር ላይ ገዢ ሆኖ የሚነሣ አይኖርም፤ በሕዝቡም ላይ ፍርሀትን አወርዳለሁ።


እነሆ ከጥፋት ለማምለጥ ሲሸሹ ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፤ ሜምፊስ ትቀብራቸዋለች፤ ያከማቹት የብር ሀብት ሁሉ ሳማ ለብሶ ይቀራል፤ መኖሪያቸውም እሾኽ ይበቅልበታል።


ነነዌ ሆይ! በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ ይላል የሠራዊት አምላክ፤ ሠረገሎችሽንም አቃጥላለሁ፤ ደቦሎችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል፤ በምድር ላይ በአንቺ ተጠቂ የሚሆን እንዳይኖር አደርጋለሁ፤ የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።


ከተገደሉትና ከተማረኩት ከጠላት መሪዎችም ራስ ደም ፍላጻዎቼን አሰክራለሁ፤ ሰይፌ የጠላትን ሥጋ ይቈራርጣል።’


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos