ኤርምያስ 44:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በግብጽ ስለምትኖሩ እስራኤላውያን ሁሉ እኔ እግዚአብሔር በኀያሉ ስሜ በመማል የወሰንኩትን ስሙ፤ ከእናንተ ማንም ሰው ‘ሕያው ልዑል እግዚአብሔርን’ ብሎ በስሜ እንዲምል አልፈቅድም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽ የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘ከእንግዲህ ወዲህ በየትኛውም የግብጽ ክፍል የሚኖር ማንኛውም አይሁዳዊ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን!” ብሎ ስሜን እንዳይጠራ፣ እንዳይምልም በታላቁ ስሜ ምያለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ስሙ፤ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ‘ሕያው በሆነ ጌታ እግዚአብሔር እምላለሁ!’ ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፥ ይላል ጌታ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እናንተ በግብፅ ምድር የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ በታላቁ ስሜ ምያለሁ፥” ይላል እግዚእብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፥ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ተብሎ እንዳይጠራ፥ እነሆ፥ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እግዚአብሔር በኃይሉና በሥልጣኑ እንዲህ ሲል ማለ፦ “ከእንግዲህ ወዲያ እህልሽን ጠላቶችሽ እንዲበሉት አላደርግም፤ የደከምሽበትን አዲስ የወይን ጠጅሽንም ባዕዳን እንዲጠጡት አላደርግም።
ትእዛዜን የማትፈጽሙ ከሆነ ግን ይህ ቤተ መቅደስ ፈራርሶ እንደሚወድቅ በራሴ በመማል አረጋግጥላችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
“የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና በዙሪያው ያሉትን አማካሪዎቹን፥ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በዚህች ምድር የተረፉትንና ወደ ግብጽ የወረዱትን ሁሉ ግን ለምግብነት ደስ እንደማያሰኙና እጅግ እንደተበላሹት እንደእነዚያ የበለስ ፍሬዎች አደርጋቸዋለሁ።
በይሁዳ ከስደት ተርፈው ወደ ግብጽ ወርደው ከሚኖሩት መካከል አንድ እንኳ የሚያመልጥ ወይም የሚተርፍ አይኖርም፤ እንደገና ይኖሩባት ዘንድ ወደሚናፍቋት ወደ ይሁዳ የሚመለስ ማንም አይኖርም፤ ከጥቂት ስደተኞች በቀር ተመልሶ የሚመጣ አይኖርም።”
ከይሁዳ ተሰደው በግብጽ ስለሚኖሩት ሕዝብ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ የነገረኝን ሁሉ ለሕዝቡ ሁሉ በተለይም ለሴቶቹ እንዲህ በማለት ነገርኳቸው፦ “እናንተና ሚስቶቻችሁ ለሰማይ ንግሥት ስእለት ለመስጠት ቃል ገብታችኋል፤ ይኸውም እናንተ ለእርስዋ ዕጣን ልታጥኑላት፥ የወይን ጠጅም መባ ልታፈሱላት የገባችሁትን ቃል ኪዳን ፈጽማችኋል፤ እንግዲያውስ ቀጥሉ፤ የገባችሁትን ቃል ጠብቁ፤ መሐላችሁንም ፈጽሙ፤
“ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ የሚጠራው ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሕያው ነኝ፤ በተራሮች መካከል ታቦር፥ በባሕር አጠገብ ቀርሜሎስ ከፍ ብለው እንደሚታዩ እንደዚሁ በእናንተ ላይ ከፍ ብሎ የሚታይ፥ ኀይል ይመጣል።
የቦጽራ ከተማ አስፈሪ ምድረ በዳ ሆና እንደምትቀር እኔ በራሴ ምዬአለሁ፤ ሕዝብ ሁሉ መቀለጃ ያደርጋታል፤ ስሟንም እንደ ርግማን ይቈጥሩታል። በአቅራቢያዋ ያሉ መንደሮች ሁሉ ለዘለዓለም ፍርስራሾች ሆነው ይቀራሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
የሠራዊት አምላክ በባቢሎን ላይ ብዛቱ እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ሠራዊት እንደሚያመጣባት በስሙ ምሎአል፤ ያም ሠራዊት ድልን በመቀዳጀት ይደነፋል።
ከዚህም የተነሣ ትሰርቃላችሁ፤ ትገድላላችሁ፤ ታመነዝራላችሁ፤ ምላችሁም በሐሰት ትመሰክራላችሁ፤ ለባዓል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከዚህ በፊት የማታውቁአቸውን አማልክት ታመልካላችሁ።
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር ስለ እናንተ እንዲህ ይላል፦ “አሁንም ሆነ ወደፊት የማታዳምጡኝ ከሆነ እያንዳንዳችሁ ሄዳችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ! ቅዱስ ስሜን ግን ከእንግዲህ ወዲያ በጣዖቶቻችሁና በመባዎቻችሁ እንድታስነውሩት አልፈቅድም።
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እናንተ ብታመነዝሩም እንኳ የይሁዳ ሕዝብ በደለኛ እንዲሆን አታድርጉ፤ ወደ ጌልጌላ ወይም ወደ ቤትአዌን አትሂዱ፤ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁም አትማሉ።
ከሟቾቹ የአንዱ የቅርብ ዘመድ የሆነና ሥርዓተ ቀብሩን የሚፈጽም ሬሳውን ከቤት አውጥቶ ይወስዳል፤ በዚያን ጊዜ በቤት ውስጥ ያለውን አንድ ሰው ጠርቶ “ከአንተ ጋር የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ብሎ ይጠይቀዋል፤ ሰውየውም “ማንም የቀረ የለም!” ብሎ ይመልስለታል፤ ጠያቂውም “የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ስለማይገባን ዝም በል!” ይለዋል።
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር “የእስራኤልን ሕዝብ ትዕቢት ጠልቼአለሁ፤ የተዋቡ ቤተ መንግሥቶቻቸውን ተጸይፌአለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ከተማይቱንና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ ለጠላት አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል።
በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።