ታላቅ መሠዊያ የሚገኘው በገባዖን ስለ ነበር አንድ ቀን ሰሎሞን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ፤ ከዚህም በፊት በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦአል፤
ኤርምያስ 28:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚሁ ዘመን፥ ማለትም ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ በአምስተኛው ወር የገባዖን ሰው የሆነው የዐዙር ልጅ ሐናንያ በቤተ መቅደስ ተናገረኝ፤ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ እንደ ነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ዐምስተኛ ወር፣ የገባዖኑ ሰው የዓዙር ልጅ ነቢዩ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት፣ በካህናቱና በሕዝቡ ሁሉ ፊት እንዲህ አለኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ዓመት፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ፥ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር፥ ነቢዩ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በጌታ ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ፥ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ሐሰተኛው ነቢይ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዓመት፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ነቢዩ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ |
ታላቅ መሠዊያ የሚገኘው በገባዖን ስለ ነበር አንድ ቀን ሰሎሞን መሥዋዕት ለማቅረብ ወደዚያ ሄደ፤ ከዚህም በፊት በዚያ መሠዊያ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦአል፤
ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አንድ ዓመት ነበር፤ መኖርያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የነበረው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤
ሕልም ያለመ ነቢይ ቢኖር ሕልሙን ብቻ ይናገር፤ ቃሌን የሰማ ነቢይ ግን ያንኑ ቃል በታማኝነት ይናገር፤ ገለባ ከስንዴ ጋር ምን ግንኙነት አለው?
ለይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስም ይህንኑ ቃል እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ “ለባቢሎን ንጉሥ ብትገብር፥ እርሱንና ሕዝቡንም ብታገለግል በሕይወት መኖር ትችላለህ፤
በኢየሩሳሌም ወደሚኖረው ወደ ይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በመጡት መልእክተኞች በኩል ወደ ኤዶም፥ ሞአብ፥ ዐሞን፥ እንዲሁም ወደ ጢሮስና ሲዶና ነገሥታት መልእክት ላከ።
በሕዝቡም ሁሉ ፊት ሲናገር፦ “በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን የአገዛዝ ቀንበር ከሕዝቡ ጫንቃ ላይ አውርዶ እንደዚህ የሚሰባብረው መሆኑን እግዚአብሔር ተናግሮአል” አለ፤ ከዚያም በኋላ እኔ ከዚያ ተነሥቼ ሄድኩ።
እርሱም በቤተ መንግሥት ወደሚገኘው ባለሥልጣኖች ወደሚገኙበት ወደ ጸሐፊው ክፍል ሄደ፤ ጸሐፊው ኤሊሻማዕ፥ የሸማዕያ ልጅ ደላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ ሌሎችም ባለ ሥልጣኖች እዚያ ተቀምጠው ነበር።
ነገር ግን ከብንያም ቅጽር በር እንደ ደረስኩ የዘብ ጠባቂዎች አለቃ የሆነው ስሙ ዪሪያ ተብሎ የሚጠራ የሐናንያ የልጅ ልጅ የሆነው የሼሌምያ ልጅ “ከድተህ ወደ ባቢሎናውያን ልትሄድ ነው!” ብሎ አስቆመኝ።
የማሕሴያ የልጅ ልጅ የሆነው የኔሪያ ልጅ ሠራያ የንጉሥ ሴዴቅያስ የቅርብ አገልጋይ ነበር፤ ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ሠራያ ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን ወረደ፤ እኔም ኤርምያስ በዚያን ጊዜ መመሪያዎችን ሰጠሁት፤
ራእያቸው ሐሰት ነው፤ ሟርታቸውም ውሸት ነው፤ እግዚአብሔር ሳይልካቸው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ይላሉ፤ ይህም ሆኖ ቃላቸው ተፈጻሚነት እንደሚኖረው ይገምታሉ።
እግዚአብሔር አሞራውያንን ለእስራኤላውያን አሳልፎ በሰጠበት ቀን ኢያሱ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ፤ እርሱም በእስራኤል ፊት እንዲህ አለ፦ “ፀሐይ በገባዖን፥ ጨረቃም በኤሎን ሸለቆ ላይ ይቁሙ” አለ።