Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 23:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሕልም ያለመ ነቢይ ቢኖር ሕልሙን ብቻ ይናገር፤ ቃሌን የሰማ ነቢይ ግን ያንኑ ቃል በታማኝነት ይናገር፤ ገለባ ከስንዴ ጋር ምን ግንኙነት አለው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሕልመኛ ነቢይ ሕልሙን ያውራ፤ ቃሌ ያለው ግን በታማኝነት ይናገር፤ ገለባና እህል ምን አንድ አድርጓቸው!” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፤ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የሚ​ያ​ልም ነቢይ ሕል​ምን ይና​ገር፤ ቃሌም ያለ​በት ቃሌን በእ​ው​ነት ይና​ገር። ገለባ ከስ​ንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፥ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው?

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 23:28
15 Referencias Cruzadas  

ሚክያስ ግን “እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ እንደምናገር በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ!” ሲል መለሰለት።


አክዓብ ግን “አንተ በእግዚአብሔር ስም የትንቢትን ቃል ስትነግረኝ እውነቱን ግለጥ! ይህንንስ ስንት ጊዜ እነግርሃለሁ?” አለው።


ታማኝ ምስክር አይዋሽም፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን የሚናገረው ሐሰት ነው።


ሕዝቤ እስራኤል ሆይ! ስንዴ በአውድማ ላይ እንደሚወቃ እናንተም ተወቅታችሁ ነበር፤ አሁን ግን የሠራዊት ጌታ፥ የእስራኤል አምላክ፥ የሰማሁትን የምሥራች ቃል ገለጥሁላችሁ።


በስሜ ሐሰት የሚናገሩት ነቢያት የሚሉትን ሰማሁ፤ ‘ሕልም አልሜአለሁ፥ ሕልም ዐልሜአለሁ’ እያሉ ይጮኻሉ።


እኔም “መልካም ነው፤ ልክ እናንተ በጠየቃችሁት መሠረት ወደ እግዚአብሔር አምላካችሁ እጸልይላችኋለሁ፤ የሚገልጥልኝንም ሁሉ ከእናንተ ምንም ነገር ሳልሰውር እነግራችኋለሁ” ብዬ መለስኩላቸው።


እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ምድሪቱ ማንም ሊዘዋወርባት የማይችል ደረቅ በረሓና ጠፍ መሆንዋ ስለ ምንድን ነው? ይህንንስ የሚያስተውል ጥበበኛ ሰው ማን ነው? ለሌሎች ማስረዳት ይችል ዘንድ የገለጥክለትስ ማን ነው?”


እኔም እንዲህ አልኩ፦ “እናንተ ሴቶች፥ እግዚአብሔር የሚለውን አድምጡ፤ ቃሉንም ለመቀበል የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ እንዴት ማልቀስ እንደሚገባቸው ሴቶች ልጆቻችሁን አስተምሩ፤ ሙሾ የማውጣትንም ዘዴ ለወዳጆቻችሁ አስጠኑ።


ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ከአሳባቸው አፍልቀው ትንቢት ለሚናገሩና ራእይ ሳያዩ ‘ራእይ አይተናል’ ለሚሉ ለእነዚህ ለሞኞች ነቢያት ወዮላቸው!


“ለቤተሰቦቹ ምግባቸውን በጊዜው እንዲሰጣቸው፥ ጌታው በቤተሰቦቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ብልኅ አገልጋይ ማን ነው?


ጌታ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ታዲያ ቤተሰቦቹን በደንብ እንዲያስተዳድርለትና ለአገልጋዮቹም ምግባቸውን በተመደበው ጊዜ እንዲሰጣቸው ጌታው የሚሾመው ታማኝና ብልኅ መጋቢ ማን ነው?


ባለ ዐደራዎችም ታማኞች ሆነው መገኘት አለባቸው።


እኛ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ንግድ ዕቃ እንደሚቸረችሩት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላኩ ቅን መልእክተኞች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት እንናገራለን።


እኔን ለአገልግሎት በመሾም ታማኝ አድርጎ የቈጠረኝንና የሰጠኝን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰግናለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos