ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።
ኤርምያስ 19:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የማደርገው ሕዝቡ እኔን ስለ ተዉና ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት በማቅረብ ይህን ስፍራ ስላረከሱ ነው፤ እነርሱም ሆኑ የቀድሞ አባቶቻቸው ከይሁዳ ነገሥታት ጭምር ስለ ነዚህ አማልክት የሚያውቁት ነገር የለም፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ንጹሖች ሰዎችን በመግደል ይህ ስፍራ በደም የተሞላ እንዲሆን አድርገውታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔን ትተውኝ፣ ይህን ስፍራ የባዕድ አማልክት ቦታ አድርገውታልና። እነርሱም ሆኑ አባቶቻቸው፣ የይሁዳ ነገሥታትም ለማያውቋቸው አማልክት ሠውተዋል፤ ይህንም ስፍራ በንጹሓን ደም ሞልተውታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትተውኛልና፥ ይህንም ስፍራ እንግዳ አድርገውታልና፥ እነርሱና አባቶቻቸውም የይሁዳም ነገሥታት ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት ዐጥነውበታልና፤ እነርሱም ይህን ስፍራ በንጹሓን ደም ሞልተውታልና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትተውኛልና፥ ይህንም ስፍራ እንግዳ አድርገውታልና፥ እነርሱና አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት ዐጥነዋልና፥ የይሁዳም ነገሥታት ይህን ስፍራ በንጹሓን ደም ሞልተዋልና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትተውኛልና፥ ይህንም ስፍራ እንግዳ አድርገውታልና፥ እነርሱና አባቶቻቸውም ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት ዐጥነዋልና የይሁዳም ነገሥታት ይህን ስፍራ በንጹህ ደም ሞልተዋልና፥ |
ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፥ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል።
ንጉሥ ኢዮስያስ በሒኖም ሸለቆ የነበረው “ቶፌት” ተብሎ የሚጠራው የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ “ሞሌክ” ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፤
በተለይም ምናሴ የንጹሓን ሰዎችን ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓን ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም።
እነርሱ ለከነዓን ጣዖቶች መሥዋዕት አድርገው ያቀረቡአቸውን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በመግደል ንጹሕ ደም አፍስሰዋል፤ ምድሪቱም በደም ረከሰች።
እነርሱ ወደ ክፉ ሥራ ይሮጣሉ፤ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ይቸኲላሉ፤ ሐሳባቸው የበደል ሐሳብ ነው፤ በሚያልፉበት ቦታ ሁሉ ማጥፋትና ማፈራረስ ልማዳቸው ነው፤
“እኔን እግዚአብሔርን ትታችሁ የተቀደሰ ተራራዬን በመርሳት ‘መልካም አጋጣሚ’ ለተባለ ጣዖትም ማእድ ታዘጋጃላችሁ፤ ‘ዕድል ፈንታ’ ለተባለ ጣዖትም ዋንጫችሁን በተደባለቀ የወይን ጠጅ ትሞላላችሁ።
የይሁዳ ሕዝብ ሆይ፥ በከተሞቻችሁ ልክ ብዙ አማልክት አሉአችሁ፤ በኢየሩሳሌምም መንገዶች ልክ አጸያፊ ለሆነው በዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ መሥዋዕት የምታቀርቡበት ብዙ መሠዊያዎችን ሠርታችኋል።
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል በላቸው፦ ‘የቀድሞ አባቶቻችሁ ከእኔ ተለይተው የሐሰት አማልክትን በማምለክ አገለገሉ፤ እኔን ተዉኝ፤ ሕጌንም አልፈጸሙም።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የእስራኤል ተስፋ ነህ፤ አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ፤ የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆንከውን አንተን እግዚአብሔርን ስለ ተዉ በትቢያ ላይ እንደ ተጻፈ ስም ይደመሰሳሉ።
እኔ የምነግርህንም ቃል እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የይሁዳ ነገሥታትና ሕዝብ! እንዲሁም በእነዚህ ቅጽር በሮች የምትገቡ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ!
ሕዝቤ ግን እኔን ረስተዋል፤ ከንቱ ለሆኑ ጣዖቶችም ዕጣን ያጥናሉ፤ እነርሱም ባልታወቀ መንገድ እንዲሄዱ አድርገዋቸዋል፤ ተሰናክለውም የቀድሞውን መንገድ ትተዋል።
ሕዝቤ ሁለት ኃጢአት ሠርተዋል፤ ይኸውም የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆንኩትን እኔን ትተውኛል፤ ውሃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጒድጓዶችን ለራሳቸው ቆፍረዋል።”
እነሆ የራስሽ ክፋት ይቀጣሻል፤ ክሕደትሽ ይፈርድብሻል፤ እኔን አምላክሽን እግዚአብሔርን መተውሽና ለእኔም የምታሳዪውን ክብር ማስቀረትሽ ምን ያኽል ከባድና መራራ በደል እንደ ሆነ ትረጂአለሽ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ጌታ የሠራዊት አምላክ ነኝ።”
ልብሶችሽ በንጹሖችና በድኾች ደም ተበክለዋል። “ነገር ግን ይህን ሁሉ አድርገሽ፥ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በእርግጥ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አይቈጣም!’ ትያለሽ፤ ነገር ግን ‘እኔ ኃጢአት አልሠራሁም’ ብለሽ በመካድሽ ምክንያት እኔ እግዚአብሔር እፈርድብሻለሁ።
“እኔ እግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድና እውነት የሆነውን ነገር እንድታደርጉ አዛችኋለሁ፤ አንዱ ሌላውን በመቀማት ግፍ እንዳይሠራ ጠብቁ፤ መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አታንገላቱ፤ በዚህም በተቀደሰ ስፍራ የንጹሕ ሰው ደም አታፍስሱበት።
ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ በጥንቃቄ ልታረጋግጡ ይገባል፤ ይኸውም እኔን ብትገድሉኝ፥ እናንተና የዚህ ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ሁሉ ንጹሕ ሰው በመግደላችሁ በደለኞች ሆናችሁ ትገኛላችሁ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ እንድሰጣችሁ ወደ እናንተ የላከኝ በእርግጥ ራሱ እግዚአብሔር ነው።”
ይህም የሆነበት ምክንያት በእነዚያ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሕዝብ ክፉ ሥራ በመሥራት ስላስቈጡኝ ነው፤ እነርሱ ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቀረቡ፤ እነርሱም ሆኑ እናንተ ወይም የቀድሞ አባቶቻችሁ ያላመለኩአቸውን አማልክት አመለኩ፤
ሕዝቡ ብዙ ጊዜ ዐምፀው እግዚአብሔርን ትተዋል፤ ስለዚህ ጠላቶቻቸው እንደ ዱር አንበሶች ወይም እንደ በረሓ ተኲላዎች አደጋ ይጥሉባቸዋል፤ እነዚያም ጠላቶች በከተሞቹ ላይ ሸምቀው ከዚያ የሚወጡትን ሰዎች ሁሉ እንደ ነብር ሆነው ይቦጫጭቁአቸዋል።
መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አትበዝብዙ፤ በዚህች ምድር የሚኖሩ ንጹሓን የሆኑ ሰዎችን በግፍ አትግደሉ፤ እንዳትጠፉም ለሐሰተኞች አማልክት አትስገዱ።
ከዚህም የተነሣ ትሰርቃላችሁ፤ ትገድላላችሁ፤ ታመነዝራላችሁ፤ ምላችሁም በሐሰት ትመሰክራላችሁ፤ ለባዓል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከዚህ በፊት የማታውቁአቸውን አማልክት ታመልካላችሁ።
የበኲር ልጆቻቸውን እስከ መሠዋት ድረስ ተቀባይነት የሌለውን መሥዋዕት በማቅረብ ራሳቸውን እንዲያረክሱ ተውኳቸው፤ ይህንንም ያደረግኹት እነርሱን መቀጣጫ የማደርጋቸው እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቁ ዘንድ ነው።
የሻፋንን ልጅ አዛንያን ጨምሮ ሰባ የእስራኤላውያን መሪዎች በዚያ ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጥና ይዞ ነበር፤ ከጥናውም መልካም መዓዛ ያለው የዕጣን ጢስ ይወጣ ነበር፤
ሠራዊቱም ቤተ መቅደሱንና አካባቢውን ያረክሳሉ፤ የዘወትር መሥዋዕትም እንዳይቀርብ ያደርጋሉ፤ አጸያፊ የሆነ ርኩስ ነገር በማቆም ጥፋትን ያመጣሉ።
“በቅርብም ሆነ በሩቅ ካሉት፥ ከአንዱ የምድር ዳርቻ በአካባቢህ ካሉ ከአሕዛብ አማልክት አንተ ወይም አባቶችህ የማታውቁትን አንዱን እናምልክ በማለት ሌላ እንኳ ቀርቶ የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ በምሥጢር ይገፋፋህ ይሆናል።
“ክፉ ነገር በማድረግ እግዚአብሔርን ስለ ተውክ በምታደርገው ነገር ሁሉ ፈጽመህ እስክትጠፋ ድረስ እርግማንን፥ ሁከትንና ውርደትን ያመጣብሃል።
“እግዚአብሔር አንተንና ንጉሥህን ከዚህ በፊት የቀድሞ አባቶችህም ሆኑ አንተ ወዳልነበራችሁበት ባዕድ አገር አፍልሶ ይወስዳችኋል፤ በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ባዕዳን አማልክትን ታመልካላችሁ።
“እግዚአብሔር በመላው ዓለም በሕዝቦች መካከል ከአንድ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ድረስ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ ሰግዳችሁላቸው የማታውቁትን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ባዕዳን አማልክት ታመልካለህ።
እስራኤላውያን ቀድሞ የማያውቁአቸውን ባዕዳን አማልክትን በመረጡ ጊዜ፥ በምድሪቱ ላይ ጦርነት ሆነ፤ ከአርባ ሺህ እስራኤላውያን ጋሻና ጦር የያዘ አንድ ሰው እንኳ አልነበረም!