ኤርምያስ 17:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ሀብትን የሚሰበስብ፥ ያልጣለችውን ዕንቊላል ታቅፋ እንደምትፈለፍል ቆቅ ነው፤ በዕድሜው አጋማሽ የሰበሰበውን ሃብት ሁሉ ያጣል። በመጨረሻም ሞኝነቱ ግልጥ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብትን በግፍ የሚያከማች ሰው፣ ያልፈለፈለችውን ጫጩት እንደምትታቀፍ ቆቅ ነው፤ በዕድሜው አጋማሽ ትቶት ይሄዳል፤ በመጨረሻም ሞኝነቱ ይረጋገጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያልወለደችውን እንደምታቅፍ ቆቅ፥ ባለጠግነትንም በቅን ባልሆነ መንገድ የሚሰበስብ ሰው እንዲሁ ነውና፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፥ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቆቅ ጮኸች፤ ያልወለደችውንም ዐቀፈች፤ በዐመፅ ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰውም እንደዚሁ ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፤ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያልወለደችውን እንደምታቅፍ ቆቅ፥ እንዲሁ በቅን ሳይሆን ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰው ነው፥ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፥ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል። |
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።
ስለዚህ እርሻቸውን ሁሉ ለሌሎች ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤ ሚስቶቻቸውንም ሌሎች ወንዶች እንዲቀሙአቸው አደርጋለሁ፤ ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች እያንዳንዱ ሰው በማታለል ጥቅምን ያግበሰብሳል፤ ነቢያትና ካህናት ሳይቀሩ ሕዝቡን ያታልላሉ፤
በሕዝቤ መካከል ያሉትን ሴቶች ከመልካም ቤት ንብረታቸው አፈናቅላችሁ አሳደዳችሁ፤ ልጆቻቸውንም ከእኔ በረከትና ክብር ዘወትር እንዲለዩ አደረጋችሁ።
እጆቻቸው ክፉ ነገርን ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ባለ ሥልጣኑና ዳኛው ጉቦ ይጠይቃሉ፤ ኀይለኛ ፍላጎቱን በግዴታ ተግባራዊ ያስደርጋል፤ በዚህም ዐይነት ሁሉም ፍርድን ያጣምማሉ።
በዚያን ቀን በአሕዛብ የአምልኮ ሥርዓት በቤተ መቅደሱ መድረክ ላይ እየዘለሉ የሚያመልኩትንና የጌታቸውን ቤት በዓመፅና በማታለል በተገኙ ዕቃዎች የሚሞሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።”
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ‘ይህን ርግማን እልካለሁ፤ ወደ እያንዳንዱ ሌባና በስሜ ምሎ በሐሰት ወደሚናገር ሰው ቤት ይገባል፤ በገባበትም ጊዜ በዚያ ቈይቶ ቤታቸውን ሁሉ ያፈራርሰዋል’ ይላል።”
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።
“ሰው ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዳይገባ፥ በሩን የምትዘጉ እናንተ ግብዞች፥ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ መግባት የሚፈልጉትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ!” [
ኃጢአት ከማድረግ የማይቈጠብ ቅንዝረኛ ዐይን አላቸው፤ የኃጢአት መሥራት ፍላጎታቸው መቼም አይረካም፤ በእምነት ጸንተው ያልቆሙትን ሰዎች ያታልላሉ፤ ለገንዘብ ይስገበገባሉ። የተረገሙ ሰዎች ናቸው።
እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ፍርድ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!