Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 55:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሸክምህን በጌታ ላይ ጣል፥ እርሱም ይደግፍሃል፥ ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 55:23
19 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፤ ክፉዎች ግን ያለ ዕድሜያቸው በሞት ይቀጫሉ።


ሐሰት የሚናገሩትን ሁሉ ታጠፋለህ፤ ነፍሰ ገዳዮችንና አታላዮችን ትጸየፋለህ።


ጊዜው ሳይደርስ ግንዱ እንደሚደርቅና ቅርንጫፎቹም እንደማይለመልሙ ዛፍ ይሆናል።


ችግር የደረሰብኝ በእርግጥ ለደኅንነቴ ነው፤ ከአደጋም ሁሉ ሕይወቴን ታድናለህ፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር ትላለህ።


ያለ ጊዜህም በሞት እንዳትቀጭ እጅግ ክፉ ወይም ሞኝ አትሁን።


በሚያዳልጥ ስፍራ ታኖራቸዋለህ፤ ወድቀው እንዲጠፉም ታደርጋቸዋለህ።


ሞትና መቃብር በቃን እንደማይሉ፥ የሰው ምኞትም እንደዚሁ ነው።


እግዚአብሔር በሲኦልና በጥፋት ቦታ ያለውን የሚያይ ከሆነ በልባችን ውስጥ ያለውንማ እንዴት አያይም?


እሾኽ በእሳት ላይ ተደርጎ ከመሞቁ በፊት ፈጥነህ ጠራርገህ አጥፋቸው።


አምላኬ ሆይ! በአንተ እታመናለሁ፤ ጠላቶቼ ድል እንዲቀዳጁ አድርገህ አታሳፍረኝ።


አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።


እርሱ በሕይወት ጠብቆናል፤ እንድንወድቅም አላደረገም።


በእውነት እርሱ ምንጊዜም ቢሆን አይናወጥም፤ ጻድቅ ሰው ለዘለዓለም ይታሰባል።


ጠባቂህ ዘወትር ንቁ ስለ ሆነ እንድትሰናከል አያደርግህም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios