ኤርምያስ 15:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቆመው ቢማልዱ ለዚህ ሕዝብ ምሕረት አላደርግም፤ ስለዚህ ከፊቴ ወዲያ እንዲሄዱ አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቢቆሙ፣ ልቤ ለዚህ ሕዝብ አይራራምና ከፊቴ አስወጣቸው፤ ይሂዱ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንደዚህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም እንኳ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ ከፊቴ አስወጣቸው፤ ይሂዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ እነዚህን ሕዝቦች ከፊቴ አባርራቸው፤ ይውጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፦ ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አይዘነብልም፥ ከፊቴ ጣላቸው፥ ይውጡ። |
ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝቦቹን ለማጥፋት ዐቅዶ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የመረጠው ሙሴ በመካከል በመቆም፥ እንዳያጠፋቸውና ቊጣውንም እንዲመልስ እግዚአብሔርን ለመነ።
እየጾሙ ቢጸልዩ እንኳ አላዳምጣቸውም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ሆነ የእህል ቊርባን ቢያቀርቡልኝ እንኳ በእነርሱ ደስ አልሰኝም፤ ይልቁንም በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ እንዲያልቁ አደርጋለሁ።”
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ወደ እኔ በንስሓ ብትመለስ፥ እቀበልሃለሁ፤ እንደገናም አገልጋይ ትሆነኛለህ፤ ከንቱ ቃል መናገርህን ትተህ ቁም ነገር ያለውን መልእክት ብታስተላልፍ፥ እንደገና የእኔ ነቢይ ትሆናለህ፤ ሕዝቡ ወደ አንተ ይመጣሉ እንጂ አንተ ወደ እነርሱ አትሄድም።
ስለዚህ ከዚህች አገር አውጥቼ፥ እናንተም ሆናችሁ የቀድሞ አባቶቻችሁ ወደማያውቁት አገር እወረውራችኋለሁ፤ እዚያም ሐሰተኞች አማልክትን ቀንና ሌሊት ታመልካላችሁ፤ ፈጽሞ ምሕረት አላደርግላችሁም።’ ”
“ለቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፤ ስለ ማንም ሐዘንህን አትግለጥ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝቤን በሰላም አልባርክም፤ ዘላቂ ፍቅርና ምሕረትም አላሳያቸውም፤
ታዲያ የደግ ሥራ ዋጋው ክፉ ነገር ማድረግ ነውን? አንተ በእነርሱ ላይ እንዳትቈጣ እኔ በፊትህ ቆሜ ስለ እነርሱ እንደማለድኩህ አስብ፤ እነርሱ ግን እነሆ እኔ የምወድቅበትን ጒድጓድ ቈፈሩ።
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ንጉሥ ኢኮንያን ከተጣለ በኋላ ማንም እንደማይፈልገው ሰባራ ገንቦ መሆኑ ነውን? እርሱና ልጆቹ ተማርከው ወደማያውቁት አገር የተወሰዱት ለምንድን ነው?”
በጽዮን “ወዮልን ልንጠፋ ነው! ፈጽሞም ተዋረድን! ቤቶቻችን ስለ ፈራረሱ አገራችንን ለቀን መሄዳችን ነው” እየተባለ የሚያስተጋባውን የለቅሶ ጩኸት አድምጡ።
እነዚያ ሦስት ሰዎች ማለትም ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጥዋ ቢገኙ እንኳ በደግነታቸው ማትረፍ የሚችሉት የራሳቸውን ሕይወት ብቻ ነው፤ ይህን የተናገረ ጌታ እግዚአብሔር ነው።
በቊጣዬ አገሪቱን ከማጥፋቴ በፊት የቅጽር ግንብ የሚሠራ፥ ቅጽሮቹ በፈረሱበት በኩል በመቆም በእኔና በሕዝቡ መካከል ገብቶ ቊጣዬን የሚያበርድ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንንም አላገኘሁም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ገና በጌልገላ ሳሉ ክፉ ሥራቸው ተገለጠ፤ እኔም በዚያ የእነርሱን ሥራ መጥላት ጀመርኩ፤ ስለ ሠሩትም ክፉ ሥራ ከሰጠኋቸው ምድር አስወጣቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ለእነርሱ ፍቅር አላሳያቸውም፤ መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ሆነዋል።
ክርስቶስ የእውነተኛይቱ “መቅደስ” ምሳሌ ወደ ሆነችውና በሰው እጅ ወደተሠራችው ቅድስተ ቅዱሳን አልገባም፤ እርሱ አሁን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት ወደ ሰማይ ገባ።
ሳሙኤልንም እንዲህ አሉት፤ “እንዳንሞት እባክህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ ሌላውን ኃጢአት ሁሉ ከመሥራት አልፈን ንጉሥ እንዲያነግሥልን በመጠየቃችን በደለኞች መሆናችንን አሁን ተገንዝበናል።”
ሳሙኤልም ገና ጡት ያልተወ ትንሽ የበግ ጠቦት ዐርዶ በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለእግዚአብሔር አቀረበው፤ ከዚህም በኋላ ስለ እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰማለት፤