“የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ሁሉም ዕውቀት የላቸውም፤ እነርሱም፥ እንደሚያንቀላፉ፥ እንደሚጋደሙ፥ እንደሚያልሙና መጮኽ እንደማይችሉ ውሾች ናቸው።
ኤርምያስ 14:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ነቢያቱ በእኔ ስም ሐሰት ይናገራሉ፤ እኔ አላክኋቸውም፤ ትእዛዝም አልሰጠኋቸውም፤ አንድ ቃል እንኳ አልነገርኳቸውም፤ አየን የሚሉት ራእይ ሁሉ ከእኔ የተገኘ አይደለም፤ ትንቢታቸው ሁሉ የሐሰት ራእይ፥ መተት፥ ጣዖት አምልኮና ከሐሳባቸው ያፈለቁት ከንቱ ነገር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ እኔ አልላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውምም። የሐሰት ራእይ፣ ሟርት፣ ከንቱ ነገርንና የልባቸውን ሽንገላ ይተነብዩላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “ነቢያቱ በስሜ የውሸትን ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፥ አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፤ የውሸትን ራእይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውም፤ የሐሰቱን ራእይ፥ ምዋርትንም፥ ከንቱንም ነገር፥ በልባቸውም የፈጠሩትን ይተነብዩላችኋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ነቢያቱ ውሸት በስሜ ትንቢት ይናገራሉ፥ አላክኋቸውም፥ አላዘዝኋቸውም፥ አልተናገርኋቸውም፥ የውሸቱን ራእይ ምዋርትንም ከንቱንም ነገር የልባቸውንም ሽንገላ ይሰብኩላችኋል። |
“የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ሁሉም ዕውቀት የላቸውም፤ እነርሱም፥ እንደሚያንቀላፉ፥ እንደሚጋደሙ፥ እንደሚያልሙና መጮኽ እንደማይችሉ ውሾች ናቸው።
ፓሽሑር ሆይ! አንተም ራስህና ቤተሰብህ በሙሉ ተማርካችሁ ወደ ባቢሎን ትወሰዳላችሁ፤ በሐሰት ከተነበይክላቸው ከወዳጆችህ ሁሉ ጋር ሞተህ በዚያው ትቀበራለህ።’ ”
በሕዝቡም ሁሉ ፊት ሲናገር፦ “በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን የአገዛዝ ቀንበር ከሕዝቡ ጫንቃ ላይ አውርዶ እንደዚህ የሚሰባብረው መሆኑን እግዚአብሔር ተናግሮአል” አለ፤ ከዚያም በኋላ እኔ ከዚያ ተነሥቼ ሄድኩ።
“ሂድ! ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘እነሆ አንተ የእንጨቱን ቀንበር ለመስበር ችለሃል፤ እኔ ግን በእርሱ ፈንታ የብረት ቀንበር እተካለሁ፤
እኔም ይህንኑ ለሐናንያ እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ “ሐናንያ ሆይ! ስማ፤ አንተን እኮ እግዚአብሔር አላከህም፤ ይህንንም ሁሉ ሕዝብ ሐሰት በሆነ ነገር እንዲተማመን አድርገሃል።
“በእግዚአብሔር ስም የሐሰት ትንቢት ቃል ስለሚነግሩአችሁም ስለ ቆላያ ልጅ አክዓብና ስለ ማዕሤያ ልጅ ሴዴቅያስ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ ‘እነርሱን ዐይናችሁ እያየ በፊታችሁ በሞት ለሚቀጣቸው ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤
“እነሆ ተሰደው በባቢሎን ወደሚኖሩት ሁሉ ስለ ሽማዕያ የተነገረውን ይህን የትንቢት ቃል እንዲህ ብለህ ላክ፥ ‘ሽማዕያ እኔ ሳልከው የትንቢት ቃል በመናገር በውሸት እንድታምኑ አድርጓችኋል፤
ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?”
ስለዚህ እርሻቸውን ሁሉ ለሌሎች ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤ ሚስቶቻቸውንም ሌሎች ወንዶች እንዲቀሙአቸው አደርጋለሁ፤ ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች እያንዳንዱ ሰው በማታለል ጥቅምን ያግበሰብሳል፤ ነቢያትና ካህናት ሳይቀሩ ሕዝቡን ያታልላሉ፤
የእናንተ ነቢያት ሐሰተኛና አታላይ ራእይ አይተውላችኋል፤ ሐሰተኛና አሳሳች ትንቢት ተናገሩ እንጂ፥ ዕድል ፈንታችሁን ለመለወጥ በደላችሁን አላጋለጡም።
የቅጽር በሮች ከመሬት በታች ተቀበሩ፤ መወርወሪያዎቻቸውም ተሰባብረው ወደቁ፤ ንጉሡና መሳፍንቱ አሁን በአሕዛብ መካከል በስደት ላይ ናቸው፤ የኦሪት ሕግ ትምህርት ከእንግዲህ ወዲህ አይሰጥም፤ ነቢያትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አይገለጥላቸውም።
“የሰው ልጅ ሆይ! ከራሳቸው ሐሳብ አፍልቀው ትንቢት በሚናገሩ የእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፤ ይልቅስ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ ንገራቸው።”
ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ሐሰተኛ ራእይ አታዩም፤ የሟርተኝነትንም ሥራ አትሠሩም፤ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
የምታዩት ራእይ ሐሰት ነው፤ የምትናገሩትም የትንቢት ቃል ውሸት ነው፤ እናንተ ክፋትና ርኲሰት የሞላችሁ ናችሁ፤ ለመጨረሻ ጊዜ ቅጣት የምትቀበሉበት ቀን ቀርቦአል፤ በአንገታችሁ ላይ ሰይፍ ተቃጥቶአል።
የከተማይቱም ሹማምንት የሚፈርዱት በጉቦ ነው፤ ካህናቱ ያለ ዋጋ አያስተምሩም፤ ነቢያቱም ያለ ገንዘብ ትንቢት አይናገሩም፤ ይህም ሁሉ ሆኖ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይመጣብንም” በማለት በእግዚአብሔር ይመካሉ።
ጣዖቶች ዋጋቢስ ነገርን ይናገራሉ፤ ጠንቋዮችም ሐሰተኛ ራእይን ያያሉ፤ የማጭበርበሪያ ሕልምንም ይናገራሉ፤ ስለዚህ ሕዝቡ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች ይባዝናሉ፤ ማጽናናታቸው ከንቱ ነው፤ ከንቱ የማጽናናት ቃል ይሰጣሉ።
ማንም ነቢይ ነኝ ብሎ ቢነሣ የወለዱት አባቱና እናቱ በእግዚአብሔር ስም ሐሰትን ስለ ተናገርክ መሞት አለብህ ይሉታል፤ ትንቢትም ሲናገር ወላጆቹ ወግተው ይገድሉታል።
እንዲህም ዐይነቱ ትምህርት የሚመነጨው በግብዝነት፥ ሐሰትን ሲናገሩ በጋለ ብረት እንደ ተተኮሰ ያኽል ሆኖ የደነዘዘ ኅሊናቸው ከማይወቅሳቸው ሰዎች ነው።
ወዳጆች ሆይ! በዓለም ላይ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ስለ ተነሡ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ይልቅስ መንፈሶች የእግዚአብሔር መሆናቸውንና አለመሆናቸውን መርምሩ።