Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 28:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “ሂድ! ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘እነሆ አንተ የእንጨቱን ቀንበር ለመስበር ችለሃል፤ እኔ ግን በእርሱ ፈንታ የብረት ቀንበር እተካለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ሄደህ ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ አንተ የዕንጨት ቀንበር ሰብረሃል፤ እኔ ግን በምትኩ የብረት ቀንበር እሠራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 “ሂድ፥ ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ አንተ የእንጨትን ቀንበር ሰብረሃል፥ ነገር ግን በእርሱ ፋንታ የብረትን ቀንበር ተክተሀል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ሂድ፥ ለሐ​ና​ንያ እን​ዲህ ብለህ ንገ​ረው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ የእ​ን​ጨ​ትን ቀን​በር ሰብ​ረ​ሃል፤ እኔ ግን በእ​ርሱ ፋንታ የብ​ረ​ትን ቀን​በር እሠ​ራ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሂድ፥ ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ የእንጨትን ቀንበር ሰብረሃል፥ እኔ ግን በእርሱ ፋንታ የብረትን ቀንበር እሠራለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 28:13
10 Referencias Cruzadas  

የእናንተ ነቢያት ሐሰተኛና አታላይ ራእይ አይተውላችኋል፤ ሐሰተኛና አሳሳች ትንቢት ተናገሩ እንጂ፥ ዕድል ፈንታችሁን ለመለወጥ በደላችሁን አላጋለጡም።


እርሱ ያልላካቸው መሆኑንና እነርሱ በስሙ የሚነግሩአችሁ ሁሉ ውሸት መሆኑን እግዚአብሔር ራሱ ነግሮአችኋል። ስለዚህ እርሱ ያሳድዳችኋል፤ እናንተና ይህን ውሸት የሚነግሩአችሁ ነቢያት ሁሉ ትጠፋላችሁ።”


ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት ለመያዝ፥ መኳንንቶቻቸውን በእግር ብረት ለማሰር፥


ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ለሚልካቸው ለጠላቶችህ አገልጋይ ትሆናለህ። በሁሉ ነገር በመቸገርም ትራባለህ፤ ትጠማለህ፤ ትታረዛለህ። ፈጽሞ እስክትጠፋ ድረስ እግዚአብሔር አንተን በጠላቶችህ እንደ ብረት በጠነከረ የአገዛዝ ቀንበር በብርቱ እንድትጨቈን ያደርጋል።


ከናስ የተሠሩትን በሮች ሰባበረ፤ የብረት መወርወሪያዎችንም ቈራረጠ።


“እኔ በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራራዎችን ዝቅ አድርጌ እደለድላለሁ፤ በነሐስ የተሠሩ በሮችንና የብረት መወርወሪያዎችን እሰብራለሁ።


“የጠፍር ማሰሪያና ማነቆ ያለው ቀንበር ከእንጨት ሠርተህ በጫንቃህ ላይ ተሸከም።


“በደሎቼ በጫንቃዬ ላይ ታስረዋል፤ እነርሱም በጣም ከባድ ስለ ሆኑ ኀይል አሳጡን፤ ልንቋቋማቸው ለማንችላቸው ጠላቶቻችን አሳልፎ ሰጠን።


የግብጽን ኀይል በመሰባበር የሚመኩበትን ብርታት በማስወግድበት ጊዜ ጣፍናስ በጨለማ ትጋረዳለች፤ ግብጽ በደመና ትሸፈናለች፤ የከተሞችዋ ኗሪዎችም ተማርከው ይወሰዳሉ።


አባቴ በእናንተ ላይ ከባድ የአገዛዝ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፤ እኔ ደግሞ ይኸው የአገዛዝ ቀንበር ይበልጥ እንዲከብድባችሁ አደርጋለሁ፤ ይኸውም አባቴ በአለንጋ ይገርፋችሁ ነበር፤ እኔ ግን እንደ ጊንጥ በሚናደፍ ጅራፍ በመግረፍ አሠቃያችኋለሁ።’ ”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios