ኢሳይያስ 43:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በእኔ ፊት የተወደዳችሁ ናችሁ፤ ስለምወዳችሁ ሕይወታችሁን ለማዳን ሕዝቦችንና መንግሥታችን አሳልፌ እሰጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዐይኔ ብርቅና ክቡርም ስለ ሆንህ፣ እኔም ስለምወድድህ፣ ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ፥ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊቴ የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ብዙ ሰዎችን ለአንተ ቤዛ፥ አለቆችንም ለራስህ እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ። |
ገና በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ እግዚአብሔር መርጦኛል፤ የተበታተኑትን የያዕቆብን ልጆች እስራኤላውያንን ለመሰብሰብ አገልጋዩ አድርጎኛል። እኔ በእግዚአብሔር ዘንድ የተከበርኩ ነኝ፤ አምላኬም ኀይል ሆኖልኛል።
በችግራቸው ጊዜ ሁሉ ያዳናቸው በመልእክተኛ ወይም በመልአክ አማካይነት ሳይሆን እርሱ በመካከላቸው በመገኘት ነው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ታደጋቸው፤ እርሱም በቀድሞ ዘመናት ሁሉ አንሥቶ ልጁን እንደሚሸከም ሰው ተንከባከባቸው።
እኔ ለእነርሱ ከሩቅ ተገለጥኩላቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ እነሆ እናንተን ለዘለዓለም ወደድኳችሁ፤ ዘለዓለማዊ ቸርነቴም ለእናንተ የጸና ይሆናል።
እግዚአብሔር ሕዝቡን “እኔ እናንተን ወድጄአችኋለሁ” ይላል። እናንተ ግን “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልሳል፥ “ዔሳውና ያዕቆብ ወንድማማቾች ነበሩ፤ እኔ ግን ያዕቆብን ወደድኩ።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፤ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ የግሌ ይሆናሉ፤ ወላጆች ለሚያገለግሉአቸው ልጆች ምሕረት እንደሚያደርጉላቸው እኔም ለእነርሱ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ።
እኔ የምለምነው እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ እንደ ሆንክ እነርሱም በፍጹም አንድ እንዲሆኑ ነው፤ እንዲሁም እኔን እንደ ላክኸኝና እኔን በወደድከኝ መጠን እነርሱንም እንደ ወደድካቸው ዓለም እንዲያውቅ ነው።
አንተ እኔን የወደድክበት ፍቅር በእነርሱ ላይ እንዲሆንና እኔም በእነርሱ እንድሆን እነርሱ አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ ደግሞም እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ።”
አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየህ ሕዝብ ነህ፤ በምድር ላይ ከሚኖሩ ከሌሎች ሕዝቦች መካከል ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ ትሆን ዘንድ ለራሱ መርጦሃል።
ስለዚህም እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት እነሆ፥ ዛሬ ለእርሱ የተለየህ ውድ ሕዝብ አድርጎ ተቀብሎሃል፤ ትእዛዞቹንም ሁሉ እንድትፈጽም ያዝሃል፤
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
እንግዲህ፥ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉትን እነዚያን ከሰይጣን ማኅበር የሆኑትን ውሸታሞች መጥተው በእግርህ ሥር እንዲወድቁ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኩህም እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ።