Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሚልክያስ 3:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፤ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ የግሌ ይሆናሉ፤ ወላጆች ለሚያገለግሉአቸው ልጆች ምሕረት እንደሚያደርጉላቸው እኔም ለእነርሱ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የገዛ ገንዘቤ ይሆናሉ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “አባት የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚታደግ ሁሉ እኔም እታደጋቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ እኔ በምሠራበት ቀን፥ ሰው የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሚልክያስ 3:17
40 Referencias Cruzadas  

አሁንም እነሆ፥ ለእኔ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔንም ብትጠብቁ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆን የተለያችሁ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤


አንተ እግዚአብሔር አምላክህ የራሱ ወገን አድርጎ የመረጠህ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ በምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች ሁሉ አንተ ለእርሱ የተለየህ ምርጥ ሕዝብ እንድትሆን አድርጎሃል።


እኔ አባታችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ፥ ይላል ሁሉን ቻይ አምላክ።”


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።


እግዚአብሔር ለአንድ ልጁ ሳይራራ ስለ እኛ አሳልፎ ከሰጠው እንዴት ከልጁ ጋር ሁሉን ነገር በነጻ አይሰጠንም?


የሠራዊት አምላክ ካህናቱን እንዲህ ይላቸዋል፦ “ልጅ አባቱን፥ አገልጋይም አሳዳሪ ጌታውን ያከብራል፤ እነሆ፥ እኔ አባታችሁ ከሆንኩ ለምን አታከብሩኝም? ጌታችሁም ከሆንኩ ለምን ክብር አትሰጡኝም? እናንተ የእኔን ስም ንቃችኋል፤ ነገር ግን ‘ስምህን የናቅነው እንዴት ነው?’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ።


እነሆ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤


እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፥ የእስራኤልንም ሕዝብ የግሉ አድርጎ መረጠ።


አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየህ ሕዝብ ነህ፤ በምድር ላይ ከሚኖሩ ከሌሎች ሕዝቦች መካከል ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ ትሆን ዘንድ ለራሱ መርጦሃል።


እርሱ በዋጋ ገዝቶአችኋል፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።


በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ በኩል ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ ‘እናንተ አባቴ የባረካችሁ! ኑ! ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ!


“እንደገናም በአጠገብሽ ሳልፍ ጊዜሽ የፍቅር ዕድሜ ነበር፤ የተራቈተውን ሰውነትሽንም በመጐናጸፊያዬ ሸፍኜ ቃል ገባሁልሽ፤ ከአንቺም ጋር እንደ ጋብቻ ያለ ቃል ኪዳን ገብቼ የእኔ የግሌ አደረግሁሽ፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


“እስራኤል ሆይ! እናንተ የተወደዳችሁ ልጆቼ ናችሁ፤ ከሁሉ አስበልጬ የምወዳችሁ አይደለምን? ምሕረት አደርግላችሁ ዘንድ ወደ እኔ ላቀርባችሁ እፈቅዳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ሌዋውያኑም በሕጉ መሠረት ራሳቸውን አንጽተው የሰንበት ቀን በቅድስና የተጠበቀች መሆንዋን ለማረጋገጥ የቅጽር በሮቹን እንዲቈጣጠሩ አዘዝኳቸው። እግዚአብሔር ሆይ! ስለዚህም ሁሉ እንድታስበኝና ስለ ጽኑ ፍቅርህም እንድትታደገኝ እለምንሃለሁ።


አለበለዚያ ግን ነፋስ ጠራርጎ እንደሚወስደው ገለባ ትሆናላችሁ፤ እንደ እሳት የሚነደው የእግዚአብሔር ቊጣ ይመጣባችኋል፤ ኀይለኛው የእግዚአብሔር የቊጣ ቀን ይመጣባችኋል።


ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።


የኢየሱስ ክርስቶስ የሆኑት ሰዎች ሥጋን ከፍትወቱና ከምኞቱ ጋር ሰቅለውታል።


ይህም የሚሆነው ለእያንዳንዱ በየተራው ነው፤ ክርስቶስ ከሞት የመነሣት የመጀመሪያው ምሳሌ ነው፤ በኋላም ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ የእርሱ የሆኑት ከሞት ይነሣሉ።


“አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እነዚህ አንተ የሰጠኸኝም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እወዳለሁ።


እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”


ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእርሱ ነኝ፤ በአሸንድዬ አበባዎች መካከል መንጋውን ያሰማራል።


እባክህ ኃጢአታቸውን ይቅር በል፤ ይቅር የማትላቸው ከሆነ ግን የሕዝብህ ስሞች ከተጻፉበት መዝገብ የእኔን ስም ደምስስ።”


በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በምድሪቱ ያለውን የተክልና የዛፍ ቅርንጫፍ ልምላሜ የተዋበና የተከበረ ያደርገዋል፤ ከእስራኤል ወገን ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ምድሪቱ በምታስገኘው ሰብል ደስታና ኲራት ይሰማቸዋል።


የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! የፈጠራችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የታደግኋችሁ ስለ ሆነ አትፍሩ፤ እናንተ የእኔ ናችሁ፤ በስማችሁም ጠርቼአችኋለሁ።


እነርሱም ለራሴ የሠራኋቸው ሕዝቦች ስለ ሆኑ እኔን ያመሰግናሉ።”


እኔ ይህን በማደርግበት ቀን ክፉዎች በእግራችሁ ጫማ ሥር እንደ ዐመድ ሆነው ይረገጣሉ።


የሚፈሩትን ሁሉ፥ ታላላቆችንም ሆነ ታናናሾችን ይባርካል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios