Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ጴጥሮስ 2:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤

Ver Capítulo Copiar




1 ጴጥሮስ 2:9
50 Referencias Cruzadas  

በአንተ ከሚመኩት ወገኖችህ እንደ አንዱ ሆኜ፥ ሕዝቦችህ ሲበለጽጉ እንዳይና የወገኖችህንም ደስታ እንድካፈል አድርገኝ።


እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ብርሃንን ሰጥቶናል፤ ለምለም የሆኑ ቅርንጫፎችን ይዘን በዓል ለማክበር ወደ መሠዊያው እንሂድ።


እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፥ የእስራኤልንም ሕዝብ የግሉ አድርጎ መረጠ።


መጪው ትውልድ ያገለግለዋል፤ የወደፊት ትውልድም ስለ እግዚአብሔር ይነገረዋል።


እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለትና እግዚአብሔር የራሱ አድርጎ የመረጠው ሕዝብ የተባረከ ነው!


እነርሱ እንደሚናገሩት ለመናገር ባስብ ኖሮ ለሕዝብህ ታማኝ ባልሆንኩም ነበር፤


እምነቱን የጠበቀ እውነተኛ ሕዝብ እንዲገባ የከተማይቱን በሮች ክፈቱ፤


“ነገር ግን አንተ አገልጋዬ እስራኤል ሆይ! ሕዝቤ እንድትሆን የመረጥኩህ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ነህ።


“ዕውሮችን ሄደውበት በማያውቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤ ቀድሞ ባላወቁትም መንገድ እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸው የተጋረደውንም ጨለማ ወደ ብርሃንነት እለውጣለሁ፤ ወጣገባ የሆነውንም ስፍራ አስተካክላለሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እኔ የምፈጽማቸው ናቸው፤ አልተዋቸውምም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመረጥኳችሁ አገልጋዮቼ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ሆይ! አድምጡ።


እናንተ ግን “የእግዚአብሔር ካህናትና የአምላካችን አገልጋዮች” ተብላችሁ ትጠራላችሁ። በሕዝቦች ሀብት ትደሰታላችሁ፤ በብልጽግናቸውም ትከብራላችሁ።


ሕዝቡ “የተቀደሱና እግዚአብሔር የታደጋቸው ወገኖች” ተብለው ይጠራሉ፤ አንቺም ኢየሩሳሌም “የተፈለገችና ያልተተወች ከተማ” ተብለሽ ትጠሪአለሽ።


እኔም ከእነርሱ አንዳንዶቹን ካህናትና ሌዋውያን ሆነው እንዲያገለግሉ አደርጋቸዋለሁ።


በጨለማ ይኖር የነበረ ሕዝብ እነሆ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገር ውስጥ ለሚኖሩትም ሁሉ ብርሃን ወጣላቸው።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ የእኔ ይሆናሉ፤ እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ የግሌ ይሆናሉ፤ ወላጆች ለሚያገለግሉአቸው ልጆች ምሕረት እንደሚያደርጉላቸው እኔም ለእነርሱ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ።


በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ የሞት ጥላ በጣለበት ምድር ለሚኖሩትም ብርሃን ወጣላቸው።”


እንዲሁም ሰዎች መልካም ሥራችሁን አይተው የሰማይ አባታችሁን እንዲያመሰግኑት፥ የእናንተም ብርሃን በሰው ፊት ይብራ።”


እርሱ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ላሉት ሁሉ ያበራል፤ እርምጃችንንም ወደ ሰላም መንገድ ይመራል።”


እነርሱ በእውነት ቅዱሳን እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ ቅዱስ አደርጋለሁ።


መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።


ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’


አግሪጳም ጳውሎስን፥ “አንተ በዚህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ክርስቲያን ልታደርገኝ ነው እኮ” አለው።


እኛን የምሕረት ዕቃዎቹንም ከአይሁድ ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብም ጠርቶናል።


እንግዲህ ሰው የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነው፤ ይህም ቤተ መቅደስ እናንተ ናችሁ።


ይህ መንፈስ ለክብሩ ምስጋና እንዲሆን እግዚአብሔር የራሱ የሆኑትን በሙሉ እስኪዋጅ ድረስ ልናገኝ ላለው ርስታችን መያዣችን ነው።


ይህንንም ያደረገው በተወደደው ልጁ አማካይነት በነጻ የሰጠን ክቡር ጸጋ እንዲመሰገን ነው።


ለእርሱ በቤተ ክርስቲያንና በኢየሱስ ክርስቶስ በዘመናት ሁሉ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶችህ የነበረው ፍቅር እጅግ ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ፥ ዛሬም አንተን ከብዙ አሕዛብ መካከል መርጦአል፤ አንተም እስከ አሁን የእርሱ ምርጥ ሕዝብ ነህ።


አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየህ ሕዝብ ነህ፤ በምድር ላይ ከሚኖሩ ከሌሎች ሕዝቦች መካከል ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ ትሆን ዘንድ ለራሱ መርጦሃል።


በወንድሞቻቸው በእስራኤላውያን መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ በሰጣቸው ተስፋ መሠረት እግዚአብሔር ርስታቸው ነው።


እናንተ ግን እሳት እንደሚነድበት የብረት ምድጃ ከሆነችው ከግብጽ መንጥቆ እግዚአብሔር ያወጣችሁ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ለራሱ የተለያችሁ ወገኖቹ እንድትሆኑ ነው።


አንተ እግዚአብሔር አምላክህ የራሱ ወገን አድርጎ የመረጠህ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ በምድር ላይ ካሉት ሕዝቦች ሁሉ አንተ ለእርሱ የተለየህ ምርጥ ሕዝብ እንድትሆን አድርጎሃል።


ሽልማቴንም ለማግኘት በፊቴ ወዳለው ግብ እሮጣለሁ፤ ይህም ሽልማት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ወደ ላይ ጠርቶ የሚሰጠኝ ሕይወት ነው።


እርሱ ከጨለማ ኀይል አድኖ ወደ ተወደደው ልጁ መንግሥት እንድንገባ አድርጎናል።


እርሱ እኛ ስላደረግነው መልካም ሥራ ሳይሆን በራሱ ፈቃድና በጸጋው አዳነን፤ ለቅድስናም ጠራን፤ ይህንንም ጸጋ ከዘመናት በፊት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰጠን።


ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።


እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ በዐቀደው መሠረት ለተመረጣችሁት፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመታዘዝና በደሙ ተረጭታችሁ ለመንጻት በመንፈስ ቅዱስ ለተቀደሳችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።


ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።


የሚያስተምር፥ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚያስተምር ያስተምር፤ የሚያገለግልም እግዚአብሔር በሚሰጠው ኀይል ያገልግል፤ በዚህም ዐይነት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሁሉ ነገር ይመሰገናል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።


የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን እንድናገለግል ንጉሦችና ካህናት ላደረገን፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ኀይል ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።


የመጀመሪያው ትንሣኤ ተካፋይ የሆኑ የተመሰገኑና ቅዱሳን ናቸው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፤ እነርሱ የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።


ለአምላካችንም የካህናት መንግሥት እንዲሆኑ አድርገሃቸዋል፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ።”


እግዚአብሔር የእርሱ ሕዝብ ያደርጋችሁ ዘንድ ወዶአልና ስለ ታላቅ ስሙ እናንተን ሕዝቡን አይተውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos