Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 43:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በፊቴ የከ​በ​ር​ህና የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ ነህና፥ እኔም ወድ​ጄ​ሃ​ለ​ሁና ስለ​ዚህ ብዙ ሰዎ​ችን ለአ​ንተ ቤዛ፥ አለ​ቆ​ች​ንም ለራ​ስህ እሰ​ጣ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ለዐይኔ ብርቅና ክቡርም ስለ ሆንህ፣ እኔም ስለምወድድህ፣ ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ፥ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እናንተ በእኔ ፊት የተወደዳችሁ ናችሁ፤ ስለምወዳችሁ ሕይወታችሁን ለማዳን ሕዝቦችንና መንግሥታችን አሳልፌ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 43:4
23 Referencias Cruzadas  

እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሩቅ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በዘ​ለ​ዓ​ለም ፍቅር ወድ​ጄ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ በቸ​ር​ነት ሳብ​ሁህ።


ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቡሩ​ክም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ባ​ር​ኩ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤


እነሆ አይሁድ ሳይሆኑ ‘አይሁድ ነን’ ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።


እኔ በእ​ነ​ርሱ እኖ​ራ​ለሁ፤ አን​ተም በእኔ፤ በአ​ንድ ፍጹ​ማን ይሆኑ ዘንድ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸ​ኝና እንደ ወደ​ድ​ኸኝ እኔም እነ​ር​ሱን እንደ ወደ​ድ​ኋ​ቸው።


እና​ንተ ስለ ወደ​ዳ​ች​ሁኝ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ወጣሁ ስለ አመ​ና​ች​ሁ​ብኝ እርሱ ራሱ አብ ወድ​ዷ​ች​ኋ​ልና።


እስ​ራ​ኤል ሕፃን በነ​በረ ጊዜ ወደ​ድ​ሁት፤ ልጄ​ንም ከግ​ብፅ ጠራ​ሁት፤


እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።


እርሱ ብቻ​ውን ታላቅ ተአ​ም​ራ​ትን ያደ​ረገ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ርስ​ቱና ሕዝቡ ትሆን ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ሁሉ ትጠ​ብቅ ዘንድ፥ ዛሬ መር​ጦ​ሃ​ልና፤


ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፥ በም​ድ​ርም ላይ ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ሁሉ ይልቅ ለእ​ርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆ​ን​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ተን መር​ጦ​አ​ልና።


እኔን የወ​ደ​ድ​ህ​በት ፍቅር በእ​ነ​ርሱ ይኖር ዘንድ፥ እኔም በእ​ነ​ርሱ እኖር ዘንድ ስም​ህን ነገ​ር​ኋ​ቸው፤ ደግ​ሞም እነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤”


ወድጃችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እናንተ ግን፦ በምን ወደድኸን? ብላችኋል። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል እግዚአብሔር ያዕቆብንም ወደድሁ፥ ዔሳውንም ጠላሁ።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ክብ​ርን የም​ት​መ​ርጡ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን የማ​ትሹ እና​ንተ እን​ዴት ልታ​ምኑ ትች​ላ​ላ​ችሁ?


በመ​ል​እ​ክ​ተ​ኛም አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​አ​ክም አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ራሱ ያድ​ና​ቸ​ዋል እንጂ። እርሱ ይወ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና፥ ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ል​ምና እርሱ ተቤ​ዣ​ቸው፤ ተቀ​በ​ላ​ቸ​ውም፤ በዘ​መ​ና​ቸ​ውም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም አከ​በ​ራ​ቸው።


መካ​ኒ​ቱን በቤቱ የሚ​ያ​ኖ​ራት፥ ደስ የተ​ሰ​ኘ​ችም የል​ጆች እናት የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት።


አሁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከብ​ሬ​አ​ለ​ሁና፥ አም​ላ​ኬም ጕል​በት ሆኖ​ኛ​ልና ያዕ​ቆ​ብን ወደ እርሱ እን​ድ​መ​ልስ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ እርሱ እን​ድ​ሰ​በ​ስብ ባርያ እሆ​ነው ዘንድ ከማ​ኅ​ፀን ጀምሮ የፈ​ጠ​ረኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል።


አባ​ቶ​ች​ህን ወድ​ዶ​አ​ልና ከእ​ነ​ርሱ በኋላ ዘራ​ቸ​ውን መረጠ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ሆኖ በታ​ላቅ ኀይሉ ከግ​ብፅ አወ​ጣህ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios