ሴቶቹ የቊንጅና እንክብካቤ እየተደረገላቸው የሚቆዩት እስከ አንድ ዓመት ነበር፤ ይኸውም የሰውነታቸው ቅርጽ እንዲስተካከል ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በከርቤና በዘይት፥ እንደገናም ለቀሪዎቹ ስድስት ወራት ባልሳም በተባለ ጣፋጭ ሽቶ ይታሻሉ፤ ከዚያም በኋላ እያንዳንድዋ ልጃገረድ በየተራ ወደ ንጉሥ አርጤክስስ ዘንድ እንድትገባ ይደረጋል።
ኢሳይያስ 3:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በሽቶ ፈንታ ግማት፥ በጥሩ መታጠቂያ ፈንታ ገመድ፥ በጐፈሬ ፈንታ ቡሃነት፥ በመጐናጸፊያ ፈንታ ማቅ፥ በውበትም ፈንታ ጠባሳ መሆን ይመጣባቸዋል! አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሽቱ ፈንታ ግማት፣ በሻሽ ፈንታ ገመድ፣ አምሮ በተሠራ ጠጕር ፈንታ ቡሓነት፣ ባማረ ልብስ ፈንታ ማቅ፣ በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሽቶ ፈንታ ግማት፤ በሻሽ ፈንታ ገመድ፤ አምሮ በተሠራ ጠጉር ፈንታ ቡሀነት፤ ባማረ ልብስ ፈንታ ማቅ፤ በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ይሆናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁንብሽ፤ በወርቅ መታጠቂያሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸላሽም ፋንታ ቡሃነት ይውጣብሽ፤ በሐር መጐናጸፊያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፥ በሽቱ ፋንታ ግማት፥ በመታጠቂያውም ፋንታ ገመድ፥ ጠጕርንም በመንቀስ ፋንታ ቡሀነት፥ በመጎናጸፊያ ፋንታ ማቅ፥ በውበትም ፋንታ ጠባሳ ይሆናል። |
ሴቶቹ የቊንጅና እንክብካቤ እየተደረገላቸው የሚቆዩት እስከ አንድ ዓመት ነበር፤ ይኸውም የሰውነታቸው ቅርጽ እንዲስተካከል ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በከርቤና በዘይት፥ እንደገናም ለቀሪዎቹ ስድስት ወራት ባልሳም በተባለ ጣፋጭ ሽቶ ይታሻሉ፤ ከዚያም በኋላ እያንዳንድዋ ልጃገረድ በየተራ ወደ ንጉሥ አርጤክስስ ዘንድ እንድትገባ ይደረጋል።
የጺቦን ሕዝብም በቤተ ጣዖታቸው ለማልቀስ ወደ ኰረብታ ይወጣሉ፤ የሞአብ ሕዝብ ስለ ነቦና ስለ ሜዳባ ከተሞቻቸው በከባድ ሐዘን ያለቅሳሉ፤ ከሐዘናቸውም የተነሣ ጠጒራቸውንና ጢማቸውን ተላጭተዋል።
ብዙ ዘይትና ሽቶ ተቀብታችሁ ሞሌክ ወደ ተባለው ጣዖት ሄዳችሁ፤ የምታመልኳቸውን ጣዖቶች ለመፈለግ መልእክተኞቻችሁን ወደ ሩቅ ቦታ ወደ ሙታን ዓለም እንኳ ሳይቀር ላካችሁ።
የሞአብ ሕዝብ በሰገነቶች ላይና በመንገዶች ላይ ሆነው ያለቅሳሉ፤ ወንዶች ጢማቸውን ይቈረጣሉ፤ ሕዝቡም ራሳቸውን ይላጫሉ፤ እጆቻቸውን ይበጣሉ፤ ማቅም ይለብሳሉ።
የዐይ ከተማ ስለ ፈረሰች አልቅሱ! በራባ ከተማ አካባቢ መንደሮች የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ጮክ ብላችሁ አልቅሱ! ሚልኮም የተባለው ጣዖት ከካህናቱና ከረዳቶቹ ጋር ተማርኮ የሄደ ስለ ሆነ ማቅ ለብሳችሁ በቅጥሮችዋ መካከል ወዲያና ወዲህ እያላችሁ አልቅሱ!
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “ሊያጠፋችሁ የመጣው ጠላት በድንገት አደጋ ሊጥልባችሁ ስለ ሆነ፥ ማቅ ለብሳችሁ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ አንድ ልጁ እንደ ሞተበት ሰው ምርር ብላችሁ አልቅሱ፤
የኢየሩሳሌም ከተማ ሽማግሌዎች ጸጥ ብለው በምድር ላይ ተቀመጡ፤ እነርሱ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው ማቅ ለበሱ፤ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፉ።
የሚከተለውን አመጣባችኋለሁ፦ ታላቅ ድንጋጤን፥ ክሳትን፥ ዐይንን የሚያፈዝና ሰውነትን የሚያመነምን የንዳድ በሽታ አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁ የሚበሉት ስለ ሆነ ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።
የዓመት በዓል ደስታችሁን ወደ ሐዘን፥ ዘፈናችሁንም ወደ ለቅሶ እለውጠዋለሁ፤ አንድ ብቻ የሆነ ልጃቸው ሞቶባቸው እንደሚያለቅሱ ወላጆች ጠጒራችሁን ተላጭታችሁ ማቅ እንድትለብሱ አደርጋለሁ፤ የዚያ ቀን ፍጻሜ የመረረ ይሆናል።
እናንተ የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ልጆቻችሁ ተማርከው ስለሚወሰዱ፥ ስለ ነዚህ ስለምትወዱአቸው ልጆቻችሁ ሐዘን ጠጒራችሁን ተላጩ፤ ራሳችሁም እንደ ጥንብ አንሣ ራስ መላጣ ይሁን።
እግዚአብሔር በሚያመነምን በሽታ፥ በትኲሳት፥ በቊስል፥ በኀይለኛ ሙቀትና በድርቅ እስክትጠፋም ድረስ ይመታሃል። ሰብልህንም ለማጥፋት ዋግና አረማሞ ይልክብሃል።
ሰዎች በታላቅ ግለት ተቃጠሉ፤ በእነዚህ መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ንስሓ አልገቡም፤ እርሱንም አላከበሩም።