Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 3:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18-23 በዚያን ቀን ጌታ የኢየሩሳሌምን ሴቶች ጌጣጌጥ ማለት የእግራቸውን አልቦ፥ የጠጒራቸውን መሸፈኛ የአንገታቸውን ጌጣጌጥ፥ የጆሮአቸውን ጒትቻ፥ አምባራቸውን፥ የፊታቸውን መሸፈኛ፥ የጠጒራቸውን መሸፈኛ፥ በክንዳቸው ላይ የሚያደርጉትን ጌጥ፥ በወገባቸው ላይ የሚያስሩትን መቀነት፥ የሽቶ ጠርሙሳቸውን፥ ጥንቈላ የተጻፈበትን አሸንክታብ፥ የጣታቸውንና የአፍንጫቸውን ቀለበት፥ ለዓመት በዓል የሚሆነውን የክት ልብስ፥ መጐናጸፊያቸውንና ካባቸውን፥ የእጅ ቦርሳቸውን፥ መስታዋታቸውን፥ ከሐር የተሠራ የውስጥ ልብሳቸውን፥ ራስ ማሰሪያቸውንና ዐይነ ርግባቸውን ሁሉ ያስወግዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በዚያም ቀን ጌታ የክብር ጌጣቸውን ይነጥቃቸዋል፤ የእግር አንባሩን፣ የጠጕር ጌጡን፣ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን የዐንገት ጌጥ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በዚያም ቀን ጌታ የክብር ጌጣቸውን ይነጥቃቸዋል፤ የእግር አንባሩን፤ የጠጉር ጌጡን፤ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን የዐንገት ጌጥ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ግር አል​ቦ​ውን ክብር፥ መር​በ​ቡ​ንም፥ ጨረቃ የሚ​መ​ስ​ለ​ው​ንም ጌጥ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በዚያም ቀን ጌታ የእግር አልቦውን ክብር፥ መርበብንም፥ ጨረቃ የሚመስለውንም ጌጥ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 3:18
7 Referencias Cruzadas  

እኔ በእነርሱ ራስ ላይ የቡሃና የቈረቈር በሽታ አመጣለሁ፤ የውስጥ ገላቸውም ይጋለጣል።”


ልብሶችሽን ሁሉ ይገፉሻል፤ ጌጣጌጦችሽንም ሁሉ ይወስዳሉ።


“ወንዶችን ከሩቅ አገር ጋብዘው እንዲያመጡላቸው ደጋግመው መልእክተኞችን ላኩ፤ የፈለጓቸውም ወንዶች መጡላቸው፤ ሁለቱ እኅትማማቾች ገላቸውን ታጠቡ፤ ዐይናቸውን ተኳሉ፤ ጌጣጌጦቻቸውንም አደረጉ፤


የእናንተ ውበት ጠጒርን በመሠራት፥ በወርቅ በማጌጥና፥ የከበረ ልብስ በመልበስ በውጪ በሚታየው ጌጥ አይሁን።


ከዚህ በኋላ ዜባሕና ጻልሙናዕ ጌዴዎንን “በል እንግዲህ አንተው ራስህ ግደለን፤ የሰው ኀይሉ እንደ ሰውነቱ ነው” አሉት፤ ስለዚህ ጌዴዎን እነርሱን ገድሎ በግመሎቻቸው አንገት ላይ የነበረውን ጌጣጌጥ በሙሉ ወሰደ።


ጌዴዎን የተቀበለው የጆሮ ጒትቻ ኻያ ኪሎ ያኽል የሚመዝን ሆነ፤ ይህም ሌላውን ጌጣጌጥ፥ የአንገት ሐብልና የምድያማውያን ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ፥ እንዲሁም በግመሎቻቸው አንገት ዙሪያ ያለውን ጌጥ ሳይጨምር ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos