አስቴር 2:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ሴቶቹ የቊንጅና እንክብካቤ እየተደረገላቸው የሚቆዩት እስከ አንድ ዓመት ነበር፤ ይኸውም የሰውነታቸው ቅርጽ እንዲስተካከል ለመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በከርቤና በዘይት፥ እንደገናም ለቀሪዎቹ ስድስት ወራት ባልሳም በተባለ ጣፋጭ ሽቶ ይታሻሉ፤ ከዚያም በኋላ እያንዳንድዋ ልጃገረድ በየተራ ወደ ንጉሥ አርጤክስስ ዘንድ እንድትገባ ይደረጋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 አንዲት ልጃገረድ ወደ ንጉሥ ጠረክሲስ ዘንድ ለመግባት ተራዋ ከመድረሱ በፊት ስድስት ወር በከርቤ ዘይት፣ ስድስት ወር ደግሞ ልዩ ልዩ ሽቱ በመቀባትና በተለያዩ የፊት ቀለሞች በመዋብ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ወር መቈየት ነበረባት፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 የመንጻታቸውም ወራት ስድስት ወር ያህል በከርቤ ዘይት፥ ስድስት ወርም በጣፋጭ ሽቱና በልዩ ልዩም በሚያነጻ ነገር ይፈጸም ነበርና እንደ ሴቶች ወግ አሥራ ሁለት ወር እንዲሁ ከተደረገላት በኋላ ወደ ንጉሡ ወደ አርጤክስስ ለመግባት የአንዳንዲቱ ቆንጆ ተራ በደረሰ ጊዜ፥ Ver Capítulo |