ኢሳይያስ 26:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ክንድህ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ ለሕዝብህ ያለህን ቅናት ይዩ፤ ይፈሩም፤ ለጠላቶችህም የተዘጋጀው እሳት ይብላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ ጌታ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩምም፥ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፥ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች። |
ነገር ግን እምቢ ብትል፥ በዓለም ላይ እኔን የመሰለ ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቅ ዘንድ አንተን ራስህን፥ መኳንንትህንና ሕዝብህን በመቅሠፍቴ ኀይል አሁኑኑ እቀጣለሁ።
ገለባ በእሳት ብልጭታ እንደሚጋይ “ኀይለኞች ነን” የሚሉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ እንደ ቃጠሎ እሳት በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት የሚያቆም የለም።
ስለዚህ ጌታ የሠራዊት አምላክ በግዙፉ ሠራዊቱ ላይ የሚያመነምን በሽታ ይልክበታል፤ በሰውነቱም ውስጥ እንደ እሳት የሚያቃጥል ትኲሳት ይልክበታል።
የእስራኤል ብርሃን እግዚአብሔር ራሱ እሳት ይሆንባቸዋል፤ የእስራኤልም ቅዱስ አምላክ ራሱ በአንዲት ቀን ኲርንችቱንና እሾኹን ሳያስቀር ሁሉን በልቶ እንደሚጨርስ የእሳት ነበልባል ይሆናል።
የእስራኤል ቅዱስ የሠራዊት አምላክ ያዘዘውን ሕግና ያስተማረውን ሥርዓት ስለ አቃለሉ ገለባና ድርቆሽ በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ የእነርሱም ሥር መሠረት በስብሶ ይጠፋል፤ አበባቸውም ደርቆ እንደ ትቢያ ይበናል።
የጨቋኞችሽ የልጅ ልጆች ወደ አንቺ ሲመጡ እጅ ይነሣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ በእግርሽ ሥር ይንበረከካሉ፤ እነርሱም አንቺን “የእስራኤል ቅዱስ የእግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ጽዮን” ብለው ይጠሩሻል።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ከተቀደሰውና ከክቡር መኖሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህ የት አሉ? መልካም ፈቃድህና ርኅራኄህስ የት አለ? እነርሱ ከእኛ ርቀዋል።
“ወጥተው ሲሄዱም በእኔ ላይ በማመፃቸው የተገደሉትን ሰዎች በድን ያያሉ፤ እነርሱን የሚበላቸው ትል አይሞትም፤ የሚያቃጥላቸውም እሳት አይጠፋም፤ እነርሱንም የሚያያቸው የሰው ዘር ሁሉ ይጸየፋቸዋል።”
ቃሉን የምታከብሩ እናንተ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ “ስለ ስሜ የሚጠሉአችሁና የሚያገሉአችሁ እንዲህ ይሉአችኋል፦ ‘እናንተ ስትደሰቱ እናይ ዘንድ እስቲ እግዚአብሔር ክብሩን ይግለጥ፤’ ኀፍረት ላይ የሚወድቁት ግን እነርሱ ራሳቸው ናቸው።
የሕዝቡ ክፋት ኲርንችቱንና እሾኹን እንደሚያቃጥል እሳት ነው፤ እንደ በረሓ እሳት ደኑን በሚያቃጥልበት ጊዜ ጢሱ ተትጐልጒሎ ሲወጣ ቀጥ ብሎ የቆመ ዐምድ ይመስላል።
የሠራዊት አምላክ ተቈጥቶአል፤ የቅጣቱም ፍርድ በአገሪቱ በሞላ እንደ እሳት ይነዳል፤ ሕዝቡም እንደ ማገዶ ይሆናል፤ ወንድም ለወንድሙ አይራራም።
ለንጉሣዊ ሥልጣኑ ወሰን የለውም፤ መንግሥቱም ዘለዓለማዊ ሰላም የሰፈነበት ይሆናል፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፥ እውነትና ፍትሕ የሰፈነበት መንግሥት በዳዊት ዙፋን ላይ ተመሥርቶ እንዲጸና ያደርገዋል፤ የሠራዊት አምላክ ቅናት ይህን ለማድረግ ወስኖአል።
ነገር ግን ከእናንተ ጥቂቶች ብቻ ከሞት ተርፈው ከግብጽ ወደ ይሁዳ ይመለሳሉ፤ በዚያን ጊዜ ወደ ግብጽ የወረዱ ስደተኞች የእኔ ወይስ የእናንተ የማንኛችን ቃል እውነት እንደ ሆነ ያረጋግጣሉ፤
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
ጠላቴም ይህን ሁሉ ያያል፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ይለኝ የነበረው ጠላቴ ኀፍረትን ይከናነባል፤ እኔ የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ በመንገድ ዳር እንዳለ ጭቃ ሲረገጥም እመለከታለሁ።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።
ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!
የእነዚህ ሰዎች ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸውም ተጨፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተዘግቶአል፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥ በዐይናቸው አይተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ወደ እኔ በተመለሱና እኔም በፈወስኩአቸው ነበር።’
ከሰማይ የሚገለጠውም በሚንበለበል እሳት ነው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይቀጣቸዋል።
መልሳችሁ ግን በገርነትና በአክብሮት ይሁን፤ የክርስቶስ በመሆናችሁ ባላችሁ መልካም ጠባይ ላይ ክፉ የሚናገሩ ሰዎች በክፉ ንግግራቸው እንዲያፍሩ መልካም ኅሊና ይኑራችሁ።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።
እንግዲህ፥ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉትን እነዚያን ከሰይጣን ማኅበር የሆኑትን ውሸታሞች መጥተው በእግርህ ሥር እንዲወድቁ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኩህም እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ።
ከዚህም በኋላ አካሄዱን ተመልከቱት፤ አቅጣጫው ወደ ቤትሼሜሽ ከተማ ያመራ እንደ ሆነ ይህን አሠቃቂ መቅሠፍት በእኛ ላይ የላከብን እግዚአብሔር መሆኑን ያመለክታል፤ ወደዚያ አቅጣጫ ባያመራ ግን መቅሠፍቱ የመጣብን በአጋጣሚ እንጂ እግዚአብሔር የላከብን አለመሆኑን እንገነዘባለን።”