Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 66:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “ወጥተው ሲሄዱም በእኔ ላይ በማመፃቸው የተገደሉትን ሰዎች በድን ያያሉ፤ እነርሱን የሚበላቸው ትል አይሞትም፤ የሚያቃጥላቸውም እሳት አይጠፋም፤ እነርሱንም የሚያያቸው የሰው ዘር ሁሉ ይጸየፋቸዋል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ የሚበሏቸው ትሎች አይሞቱም፤ የሚያቃጥላቸው እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ወጥ​ተ​ውም በእኔ ያመ​ፁ​ብ​ኝን ሰዎች ሬሳ​ቸ​ውን ያያሉ፤ ትላ​ቸው አይ​ሞ​ትም፤ እሳ​ታ​ቸ​ውም አይ​ጠ​ፋም፤ ለሥጋ ለባ​ሽም ሁሉ ምሳሌ ይሆ​ናሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፥ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፥ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 66:24
24 Referencias Cruzadas  

በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ የጦር ሜዳዎችንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋል፤ በምድር ላይ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ይደመስሳል።


ኃጢአተኞችንና ዐመፀኞችን ግን በአንድነት ሰባብሮ ይደመስሳል፤ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ሁሉ ይጠፋሉ።


ገለባ በእሳት ብልጭታ እንደሚጋይ “ኀይለኞች ነን” የሚሉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ እንደ ቃጠሎ እሳት በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት የሚያቆም የለም።


ቀድሞ ስለ ክብርህ በመሰንቆ ይዘመርልህ የነበረው ቆመ፤ አሁን አንተ በትዕቢትህ ወደ ሙታን ዓለም ወረድክ። ስለዚህ አልጋህ ምስጥ፥ ልብስህም የትል መንጋ ሆኖአል።’ ”


ምድር እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ በዐውሎ ነፋስ እንደ ተገፋ ጎጆም ትናወጣለች፤ እርስዋም የኃጢአትዋ ሸክም ስለሚጫናት ትወድቃለች፤ መነሣትም አትችልም።


አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።


ቀንና ሌሊት ትቃጠላለች፤ ጢስም ከእርስዋ መውጣቱን ለዘለዓለም አያቋርጥም፤ ምድሪቱም በዘመናት ሁሉ የማትጠቅም ባድማ ትሆናለች፤ ዳግመኛ በእርስዋ ውስጥ አልፎ የሚሄድ አይኖርም።


ሬሳቸው የትም ተጥሎ ይበሰብሳል እንጂ አይቀበርም፤ ተራራዎችም በደማቸው ይጥለቀለቃሉ።


“ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል እግዚአብሔር።


እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ በጣም ተቈጥቶአል፤ በኀያልነቱም ይቀጣቸዋል፤ ተራራዎች ይናወጣሉ፤ የሞቱ ሰዎችም አስከሬን እንደ ጥራጊ በየመንገዱ ዳር ይወድቃል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ አይበርድም፤ እንደገናም ሊቀጣቸው ተዘጋጅቶአል።


እነርሱ ብል እንደ በላው ልብስና ትል እንደበላው ሱፍ ይሆናሉ፤ የእኔ ታዳጊነት ግን ዘለዓለማዊ ነው፤ አዳኝነቴም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።”


እኔ ጌታ እግዚአብሔርም እናንተን ለሞት አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የእናንተም ስም በእኔ ተመራጮች ዘንድ መራገሚያ ይሆናል፤ ለአገልጋዮቼ ግን የተለየ ስም እሰጣቸዋለሁ።


እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፍ ይፈርዳል፤ እንዲሁም በሞት የሚቀጣቸው ብዙዎች ናቸው።


ሞተው ዐፈር የበላቸው ሁሉ ይነሣሉ፤ ከእነርሱም ከፊሎቹ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሲገቡ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት ይላካሉ።


ኢየሩሳሌምን ለመውጋት በሚነሣሡ ሕዝቦች ላይ እግዚአብሔር ቀሣፊ በሽታ ያመጣባቸዋል፤ በሕይወት እያሉ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዐይናቸው በዐይነስባቸው ውስጥ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።


እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos