Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -


ሚልክያስ 4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም


የፍርድ ቀን

1 የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።

2 ለእናንተ ስሜን ለምታከብሩ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላችኋል፤ ፈውስንም ይሰጣችኋል። ከጒረኖ እንደ ተለቀቀ ጥጃ ትቦርቃላችሁ።

3 እኔ ይህን በማደርግበት ቀን ክፉዎች በእግራችሁ ጫማ ሥር እንደ ዐመድ ሆነው ይረገጣሉ።

4 “የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይመሩበት ዘንድ በሲና ተራራ ላይ ለአገልጋዬ ለሙሴ የሰጠሁትን ሕግና ትእዛዝ አስታውሱ።

5 “ታላቁና አስፈሪው የእኔ የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት እነሆ፥ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።

6 እኔ መጥቼ ምድሪቱን እንዳልረግም እርሱ የወላጆችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ ወላጆች ይመልሳል።”

© The Bible Society of Ethiopia, 2005

© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997

Bible Society of Ethiopia
Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos