Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 9:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ነገር ግን እምቢ ብትል፥ በዓለም ላይ እኔን የመሰለ ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቅ ዘንድ አንተን ራስህን፥ መኳንንትህንና ሕዝብህን በመቅሠፍቴ ኀይል አሁኑኑ እቀጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አለዚያ በአንተ በሹማምትህና በሕዝብህ ላይ የመቅሠፍቴን መዓት ሁሉ አሁን አወርድብሃለሁ፤ ይኸውም በምድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ ማንም እንደሌለ ታውቅ ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በዚህ ጊዜ መቅሠፍቴን ለልብህ በአገልጋዮችህ በሕዝብህም በምድር ሁሉ ላይ እልካለሁ ይህም እንደ እኔ ያለ እንደሌለ እንድታውቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በም​ድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እን​ደ​ሌለ ታውቅ ዘንድ በሰ​ው​ነ​ትህ፥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ላይ መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ሁሉ በዚህ ጊዜ እል​ካ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በምድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እንደሌለ ታውቅ ዘንድ በሰውነትህ በባሪያዎችህም በሕዝብህም ላይ መቅሠፍቴን ሁሉ አሁን እልካለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 9:14
27 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ እንደ አንተ ማንም የለም፤ በሰማነው መሠረት ከአንተ በቀር አምላክ የለም።


ጸሎታቸውን ስማ፤ በሕዝብህ በእስራኤል መካከል ልብን የሚያሸብር መራር ሐዘን ደርሶባቸው እጃቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ በመዘርጋት በሚጸልዩበት ጊዜ፥


እግዚአብሔር ሆይ ከቶ አንተን የሚመስል ማንም የለም፤ እንደ ሰማነው ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለም።


ጌታ ሆይ! ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል የለም፤ አንተ ያደረግኸውን ያደረገ ማንም የለም።


“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?


ንጉሡም “እንግዲያውስ ነገውኑ ጸልይልኝ” አለ። ሙሴም እንዲህ አለ፤ “እንዳልከው አደርጋለሁ፤ አንተም እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ሌላ አምላክ እንደሌለ በዚያን ጊዜ ታውቃለህ።


ስለዚህም አሮን በግብጽ ውሃ ሁሉ ላይ በትሩን ዘረጋ፤ ጓጒንቸሮችም ወጥተው ምድሪቱን አለበሱአት።


አንተንና ሕዝብህን በመቅሠፍት ለመምታት የኀይል ክንዴን አንሥቼ ቢሆን ኖሮ እስከ አሁን ከምድር በተወገዳችሁ ነበር።


“እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አንተ እኔን ባታውቀኝም እንኳ ብርታትን እሰጥሃለሁ።


እኔ ብቻ አምላክ መሆኔንና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ በቀድሞ ዘመን የተደረጉትን የጥንቱን ነገሮች አስታውሱ፤ እኔ አምላክ ነኝ፤ እኔንም የሚመስል ሌላ የለም።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተን የሚመስል ማንም የለም፤ አንተ ኀያል ነህ፤ ስምህም ታላቅና አስፈሪ ነው።


የመንግሥታት ሁሉ ንጉሥ ስለ ሆንክ አንተን የማይፈራ ማን ነው? በአሕዛብ ጠቢባንም ሆነ በንጉሦቻቸው መካከል አንተን የሚመስል ስለሌለ ክብር ይገባሃል።


ይህችን ከተማ የፍርስራሽ ክምር አደርጋታለሁ፤ በዚያ በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነግጣል፤ በደረሰባት ችግርም ይገረማል።


ከሕዝብ መካከል ተባረረ፤ አእምሮውም ተለውጦ እንደ እንስሳ ሆነ፤ እንደ በሬም ሣር እየበላ ከሜዳ አህዮች ጋር ሆኖ ለመኖር ተገደደ፤ መጠለያ አጥቶ ሰውነቱ በሰማይ ጠል ረሰረሰ፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትን ሁሉ ለፈለገው መስጠት እንደሚችል እስከሚረዳበት ጊዜ ድረስ ነበር።


“ይህም ሁሉ ከደረሰባችሁ በኋላ እንኳ የማትታዘዙኝ ከሆናችሁ፥ በእናንተ ላይ የማመጣውን ቅጣት ሰባት ጊዜ እጥፍ እንዲበዛ አደርገዋለሁ።


“እኔን በመቃወም ከቀጠላችሁና እኔን የማትሰሙኝ ከሆነ፥ እንደ ኃጢአታችሁ ብዛት ሰባት ጊዜ እጥፍ የሆነ መቅሠፍት አመጣባችኋለሁ።


በእናንተ ላይ በቊጣ እነሣለሁ፤ በእናንተ ላይ የማመጣውንም ቅጣት ካለፈው ሰባት ጊዜ የበለጠ እንዲሆን አደርጋለሁ።


ስለዚህ በኃጢአታችሁ ምክንያት እናንተን ለማጥፋትና ለመደምሰስ ተነሥቼአለሁ።


‘ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ወደ ፊት ከምታደርጋቸው ታላላቅና አስደናቂ ነገሮች ሁሉ ያሳየኸኝ የመጀመሪያውን ክፍል ብቻ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ አንተ የምታደርጋቸውን ታላላቅ ነገሮች የሚያደርግ ሌላ አምላክ በሰማይም ሆነ በምድር የለም።


አምላክ እርሱ ብቻ እንደ ሆነና ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ያረጋግጥላችሁ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አሳይቶአችኋል፤


ስለዚህ መቅሠፍቶችዋ ሁሉ በአንድ ቀን ይደርሱባታል፤ ሞትና ሐዘን ራብም ይደርሱባታል፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ በእርስዋ ላይ የሚፈርድባት ጌታ አምላክ ብርቱ ነው።”


እነሆ፥ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል የሚሰማውን ሁሉ አስጠነቅቃለሁ፤ ማንም በዚህ ቃል ላይ አንዳች ነገር ቢጨምር፥ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች እግዚአብሔር ይጨምርበታል።


ወዮልን! ከእነዚህ ኀያላን አማልክት እጅ ማን ያድነናል? እነርሱ ግብጻውያንን በበረሓ በተለያዩ መቅሠፍቶች የመቱ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos