Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 9:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የሠራዊት አምላክ ተቈጥቶአል፤ የቅጣቱም ፍርድ በአገሪቱ በሞላ እንደ እሳት ይነዳል፤ ሕዝቡም እንደ ማገዶ ይሆናል፤ ወንድም ለወንድሙ አይራራም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ትጋያለች፤ ሕዝቡም እሳት ውስጥ እንደሚጨመር ማገዶ ይሆናል፤ ወንድሙንም ማዳን የሚችል ማንም የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በቀኝ በኩል ይጐርሳሉ፤ ነገር ግን ራባቸው አይታገሥም፤ በግራም በኩል ይበላሉ፤ ነገር ግን አይጠግቡም፤ እያንዳንዱም የገዛ ወገኑን ሥጋ ይበላል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ምድር ሁሉ ትቃ​ጠ​ላ​ለች፤ ሕዝ​ቡም እሳት እን​ደ​ሚ​በ​ላው እን​ጨት ሆኖ​አል፤ ሰውም ለወ​ን​ድሙ አይ​ራ​ራም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ተቃጥላለች፥ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፥ ሰውም ለወንድሙ አይራራም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 9:19
32 Referencias Cruzadas  

ገለባ በእሳት ብልጭታ እንደሚጋይ “ኀይለኞች ነን” የሚሉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ እንደ ቃጠሎ እሳት በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት የሚያቆም የለም።


ሀብታቸውን ዘርፈውና መዝብረው ሕዝቡን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንዲረግጡ በከሐዲውና ቊጣዬንም ባነሣሣው ሕዝብ ላይ አሦራውያንን አስነሥቼ እልካቸዋለሁ።”


እኔ የሠራዊት አምላክ ቊጣዬን በምገልጥበት ጊዜ ሰማይን አንቀጠቅጣለሁ፤ ምድርም ከስፍራዋ እንድትናወጥ አደርጋለሁ።


በቀስታቸውና በፍላጻቸው ወጣቶችን ይገድላሉ፤ ሕፃናትን እንኳ አይምሩም፤ ለልጆችም ርኅራኄ የላቸውም።


እነሆ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ የእግዚአብሔር ቊጣና መዓት የሚፈጸምበት ያ ቀን እጅግ አስፈሪ ነው፤ በዚያን ጊዜ በእርስዋ የሚኖረው ኃጢአተኛ ሕዝብ ስለሚደመሰስ ምድሪቱ ባድማ ትሆናለች።


ስለዚህም ርግማን ምድርን ያጠፋል፤ ሕዝቦችዋም በበደሉት በደል ተጠያቂዎች ይሆናሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይደመሰሳሉ፤ የሚተርፉትም ጥቂቶች ናቸው።


አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።


ሕዝቡም እርስ በርሱ አንዱ ሌላውን ለመጨቈን ባልንጀራ በባልንጀራው ላይ ይነሣሣል፤ ወጣቱ ሽማግሌውን አያከብርም፤ ተንቆ ይኖር የነበረውም ሰው ክብር ባለው ሰው ላይ ይታበያል።


በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ይፈራሉ፤ ከሐዲዎችም ይርበደበዳሉ፤ ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳትና ከዘለዓለማዊ ነበልባል ጋር ለመኖር የሚችል ማነው ይላሉ።


የኢየሩሳሌምን ርኲሰት ያጠራል፤ በፍርዱና በመንፈሱ ኀይል ደም አፍሳሽነትን ከመኻልዋ ያስወግዳል።


ስለዚህ የቊጣውን ግለትና አስፈሪውን ጦርነት በላያችን ላይ አወረደ፤ በዙሪያችን እሳት አቀጣጠለ፤ እኛ ግን ይህን ሁሉ አልተረዳነውም፤ አቃጠለን ልብም አላደረግነውም።


የእስራኤል ቅዱስ የሠራዊት አምላክ ያዘዘውን ሕግና ያስተማረውን ሥርዓት ስለ አቃለሉ ገለባና ድርቆሽ በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ የእነርሱም ሥር መሠረት በስብሶ ይጠፋል፤ አበባቸውም ደርቆ እንደ ትቢያ ይበናል።


በዚያን ቀን እንደ ባሕር ማዕበል እየተመሙ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ይመጡባቸዋል፤ እነሆ ወደ ምድር ቢመለከቱ በጨለማና በመከራ እንደ ተከበቡ ያያሉ፤ ከደመናውም የተነሣ ብርሃኑ ይጨልማል።


እነሆ፥ ጨለማ ምድርን፥ ድቅድቅ ጨለማም ሕዝብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ላይ ያበራል፤ ክብሩም በአንቺ ላይ ይገለጣል።


ከዚያ በኋላ ወደ ምድር ሲመለከቱ ሊያዩ የሚችሉት ጭንቀት ጨለማና ጭፍግግ ያለ አስፈሪ ሁኔታን ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ።


ጨለማን አምጥቶ በተራራዎች ከመሰናከላችሁ በፊት ተስፋ ያደረጋችኹትን ብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ወደ ጥልቅ ጭጋግ ከመለወጡ በፊት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ።


ለደቡብም ጫካ እኔ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ የሚለውን ስማ ብለህ ንገረው፤ ‘ተመልከት! እነሆ እኔ በውስጥህ እሳትን በማቀጣጠል ላይ ነኝ፤ ይህም እሳት ለምለሙንም ሆነ ደረቁን ሳይመርጥ ዛፎችን ሁሉ ያቃጥላል፤ እሳቱንም ሊያጠፋው የሚችል አይኖርም፤ ከደቡብ እስከ ሰሜን ይዛመታል፤ በመንገዱ ያገኘውን ሁሉ ያቃጥላል።


እንደገናም እግዚአብሔር ሌሎቹን ሰዎች እንዲህ ሲላቸው ሰማሁ፦ “በሉ እናንተም እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ ውስጥ በመዘዋወር ሁሉን ግደሉ፤ ለማንም በመራራት ምሕረት አታድርጉ።


ያ ቀን የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ የጧት ፀሐይ ወገግታ በተራሮች ላይ እንደሚያንሰራፋ፥ ታላቅና ኀያል የአንበጣ መንጋ በየቦታው ይንሰራፋል። ይህን የሚመስል ነገር ከዚህ በፊት አልታየም፤ ከእንግዲህ ወዲህም ምን ጊዜም ቢሆን አይታይም።


እነርሱ በፊታቸው የሚገኘውን ተክል ሁሉ እንደ እሳት ይበላሉ፤ እንደ ነበልባልም ያቃጥላሉ። ገና ያልደረሱበት፥ በፊታቸው ያለው ምድር፥ እንደ ዔደን የአትክልት ቦታ የለመለመ ነው፤ እነርሱ ያለፉበት ምድር ግን የወደመ በረሓ ይሆናል፤ ከእነርሱ የሚያመልጥ ምንም ነገር አይገኝም።


ምግብ እንድታጡ በማደርግበት ጊዜ እንጀራችሁን ዐሥር ሴቶች በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፤ ምግባችሁንም መጥነው ያቀርቡላችኋል፤ እናንተም በልታችሁ አትጠግቡም።


እናንተ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት የምትጠባበቁ ወዮላችሁ! ያ ቀን የጨለማ እንጂ የብርሃን ቀን ስላይደለ ለምን ያንን ቀን ትጠባበቃላችሁ?


የያዕቆብ ልጆች እንደ እሳት፥ የዮሴፍ ልጆች እንደ ነበልባል፥ የዔሳውም ልጆች እንደ ገለባ ይሆናሉ፤ እሳት ገለባን እንደሚያቃጥል የያዕቆብና የዮሴፍ ልጆች የዔሳውን ልጆች ያጠፋሉ። ይህንንም የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ከምድሪቱ ላይ ታማኝ ሰው ጠፍቶአል፤ አንድም ትክክለኛ ሰው የለም፤ ሁላቸውም ሰውን ለመግደል ያደባሉ፤ እርስ በርሳቸውም አንዱ ሌላውን ተከታትሎ ያጠምዳል።


በዚያን ዘመን ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃል፤ ሴት ልጅ በእናትዋ ላይ ምራትም በዐማትዋ ላይ በጠላትነት ይነሣሉ፤ የሰው ጠላቶቹ የገዛ ቤተ ሰዎቹ ይሆናሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔም ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖር ለማንም ሰው ርኅራኄ አላደርግም፤ እኔ ራሴ እያንዳንዱን ሰው ለጐረቤቱና ለንጉሡ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ምድሪቱን ያጠፋሉ፤ እኔም ከእነርሱ እጅ አልታደጋቸውም።”


ከዚህ በኋላ መንጋውን እንዲህ አልኩ፦ “እኔ ከእንግዲህ ወዲህ እረኛችሁ አልሆንም፤ የሚሞቱት ይሙቱ፤ የሚጠፉትም ይጥፉ፤ የተረፉትም እርስ በርሳቸው ተባልተው ይለቁ፤”


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።


ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ጨለማ ሆነ።


ታላቁና አስገራሚው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፥ ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ደም ትመስላለች።


መላእክትን እንኳ ኃጢአት በሠሩ ጊዜ እግዚአብሔር ሳይራራላቸው በጨለመ ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ሆነው የፍርድን ቀን እንዲጠባበቁ ወደ ገሃነም ጣላቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos