እግዚአብሔርንም፥ “አዳኝ አምላካችን ሆይ! ከአሕዛብ መካከል መልሰህ ወደ አገራችን አግባን፤ በዚያን ጊዜ እናመሰግን ዘንድ፥ ቅዱስ ስምህንም እናከብር ዘንድ፥ እባክህ ታደገን!” በሉት።
ኢሳይያስ 17:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤል ሆይ እናንተ እንደ ጽኑ አለት መከላከያ ሆኖ የተቤዣችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ስለዚህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ድንቅና ብርቅ የሆነ ተክል ብትተክሉና አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዳኝ አምላክህን ረስተሃል፤ መሸሸጊያ ዐለትህንም አላስታወስህም፤ ስለዚህ ምርጥ ተክል ብትተክልም፣ እንግዳ ዘርንም ብትዘራ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዳኝ አምላክህን ረስተሃል፤ መሸሸጊያ ዐለትህንም አላሰብክም፤ ስለዚህ ያማረውን ተክል ብትተክልም እንግዳንም ዘር ብትዘራ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዳኝህ እግዚአብሔርን ትተኸዋልና፥ ረዳትህ እግዚአብሔርንም አላስብኸውም፤ ስለዚህ የሐሰትን ተክል ተክለሃል፤ የሐሣርንም ዘር ዘርተሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደኅንነትህን አምላክ ረስተሃል፥ የረድኤትህንም ጌታ አላሰብህም፥ ስለዚህ ያማረውን ተክል ተክለሃል፥ እንግዳንም ዘር ዘርተሃል። |
እግዚአብሔርንም፥ “አዳኝ አምላካችን ሆይ! ከአሕዛብ መካከል መልሰህ ወደ አገራችን አግባን፤ በዚያን ጊዜ እናመሰግን ዘንድ፥ ቅዱስ ስምህንም እናከብር ዘንድ፥ እባክህ ታደገን!” በሉት።
ጸሎታችንን ሰምተህ ድልን ታጐናጽፈናለህ፤ እኛንም ለማዳን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ፤ ሩቅ ከሆነው ባሕር ማዶ ያሉት ሳይቀሩ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይታመናሉ።
በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።
በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን አደጋ ባደረሱባቸው ጊዜ የሒዋውያንና የአሞራውያን ከተሞች ባድማ እንደ ሆኑት የእናንተም ጠንካራ ከተሞች ባድማዎች ይሆናሉ።
የወይን መከር ከመሰብሰቡ በፊት አበቦች ረግፈው የወይን ፍሬ በሚበስልበት ጊዜ የወይን ሐረግ ቅርንጫፎች በስለት ተቈርጠው እንደሚጣሉ እርሱ የዚያችን አገር ሕዝብ ያጠፋል።
ለድኾች፥ ለመጻተኞችና ለችግረኞች በችግራቸው ጊዜ መጠጊያ ሆነህላቸዋል፤ ከዐውሎ ነፋስ የሚድኑበት ተገንና ከፀሐይ ቃጠሎ የሚጠለሉበት ጥላ ሆነህላቸዋል፤ የጨካኞች ምት የክረምት ወጀብ ግድግዳን እንደሚገፋ ያለ ነው።
እናንተ ግን ደስ ይላችኋል፤ በተቀደሰ በዓል ምሽት እንደምትዘምሩት ትዘምራላችሁ፤ የእስራኤል አምባ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዋሽንት እየነፉ እንደሚዘምሩት ሰዎች ትደሰታላችሁ።
እናንተ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ አስቀድሜ አልነገርኳችሁምን? ወይስ አልገለጽኩላችሁምን? ለዚህም እናንተ ምስክሮቼ ናቸሁ፤ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ከእኔ ሌላ መጠጊያ አለት የለም፤ ማንም የለም።”
ምድርን የመሠረተና ሰማያትን የዘረጋ ፈጣሪአችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ሊያጠፉአችሁ ከተዘጋጁ ከጨቋኞቻችሁ ቊጣ የተነሣ፥ ዘወትር በፍርሃት ትኖራላችሁ። የእነርሱስ ቊጣ የት አለ?
እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ እንዲህ ብሎ ያውጃል፦ “አዳኝሽ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር ለሰዎች የሚከፍለው ዋጋና ሽልማት አለ ብላችሁ ለጽዮን ልጅ ንገሩአት።”
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የእስራኤል ተስፋ ነህ፤ አንተን የሚተዉ ሁሉ ያፍራሉ፤ የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆንከውን አንተን እግዚአብሔርን ስለ ተዉ በትቢያ ላይ እንደ ተጻፈ ስም ይደመሰሳሉ።
ልምላሜ በሌለባቸው ኰረብቶች ራስ ላይ ድምፅ ይሰማል፤ ይህም ድምፅ፥ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት ኃጢአት ሲሠሩ ኖረው፥ አሁን በመጸጸት የሚያሰሙት የለቅሶና የልመና ድምፅ ነው።
ከሕዝብሽ አንዳንዶቹ ገንዘብ ተቀብለው ሰው ይገድላሉ፤ አንዳንዶቹ ለገዛ ወገኖቻቸው ለእስራኤላውያን ሳይቀር በአራጣ ያበድራሉ፤ እነርሱንም በመበዝበዝ ያለ አግባብ ይበለጽጋሉ፤ እኔንም ፈጽሞ ረስተዋል፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
አሁንም ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ስለ ረሳሽኝና ጀርባሽን ስላዞርሽብኝ፥ ስለ ሴሰኛነትሽና ስለ አመንዝራነትሽም መከራ ትቀበዪአለሽ።”
ሕዝቤ እኔን በሚገባ ካለማወቁ የተነሣ ጠፍቶአል፤ እናንተ እኔን ለማወቅ ስላልፈለጋችሁ እኔም ካህናት ሆናችሁ እንድታገለግሉኝ አልፈልጋችሁም፤ ሕጌንም ስላቃለላችሁና ስለ ረሳችሁ ልጆቻችሁ በእኔ ዘንድ የተረሱ ይሆናሉ።
“የእስራኤል ሕዝብ ለራሳቸው ታላላቅ ቤተ መንግሥቶች ሠርተዋል፤ እኔን ፈጣሪአቸውን ግን ረስተዋል፤ የይሁዳም ሕዝብ ብዙ የተመሸጉ ከተሞችን ሠርተዋል፤ ስለዚህ ከተሞቻቸውንና ምሽጎቻቸውን የሚያቃጥል እሳት እልክባቸዋለሁ።”
የሚከተለውን አመጣባችኋለሁ፦ ታላቅ ድንጋጤን፥ ክሳትን፥ ዐይንን የሚያፈዝና ሰውነትን የሚያመነምን የንዳድ በሽታ አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁ የሚበሉት ስለ ሆነ ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።
ድኾችን ጨቊናችሁ፤ እህላቸውንም አስገብራችሁ፤ ከጥርብ ድንጋይ ቤቶች ሠርታችኋል፤ እናንተ ግን አትኖሩባቸውም፤ የሚያስደስት ወይን ተክላችኋል፤ ነገር ግን ከእርሱ የሚገኘውን የወይን ጠጅ እናንተ አትጠጡም።
ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ በዚያን ጊዜ ቤት ይሠራሉ፤ ነገር ግን አይኖሩበትም፤ ወይንም ይተክላሉ፤ ነገር ግን የወይኑን ጠጅ አይጠጡም።”
“ልጃገረድ ለማግባት ታጫለህ፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይደፍራታል፤ ቤት ትሠራለህ፤ ነገር ግን አትኖርበትም፤ ወይን ትተክላለህ፤ ነገር ግን በፍሬው አትጠቀምበትም።
“እርሱ ምሽጋችን ነው፤ ሥራዎቹም ፍጹሞች ናቸው፤ መንገዶቹም ሁሉ የቀኑ ናቸው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፥ እርሱም ቀጥተኛና እውነተኛ ነው።
እግዚአብሔር አምላክህን ብትረሳና ትሰግድላቸውና ታገለግላቸውም ዘንድ ወደ ባዕዳን አማልክት ፊትህን ብትመልስ፥ በእርግጥ የምትጠፋ መሆንህን ዛሬውኑ አስጠነቅቅሃለሁ።