Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 26:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ለዘለዓለሙም በእግዚአብሔር ታምናችሁ ኑሩ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም መጠጊያ አምባችን ነውና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በእግዚአብሔር ለዘላለም ታመኑ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም ዐለት ነውና ለዘለዓለም በጌታ ታመኑ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም አንባ ነውና ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 26:4
32 Referencias Cruzadas  

ሰዎቹ በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ተነሥተው ተቆዓ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓማ አገር ሄዱ፤ ወደዚያ ለመሄድ ጒዞ በመጀመር ላይ ሳሉም ኢዮሣፍጥ እነርሱን “የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ተማመኑ፤ እርሱም ብርታትን ይሰጣችኋል፤ የእግዚአብሔር ነቢያት የሚነግሩአችሁንም እመኑ፤ ይሳካላችኋልም” አላቸው።


ከእርሱ ጋር ያለው ኀይል ሰብአዊ ኀይል ነው፤ ከእኛ ጋር ሆኖ የሚረዳንና የሚዋጋልን ግን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፤” ሕዝቡም ንጉሡ በተናገረው በዚህ ቃል ተበረታታ።


ባለኝ ኀይል ልታገለው እንዳልል፥ በኀይል እርሱን የሚቋቋም የለም፤ ተሟግቼ እረታዋለሁ እንዳልል፥ እርሱን ወደ ፍርድ ሸንጎ ሊያቀርበው የሚችል የለም።


በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሰዎች ከቶ እንደማይነቃነቅና እንደማይናወጥ እንደ ጽዮን ተራራ የጸኑ ናቸው።


እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬና አዳኜ ነው፤ አምላኬ የምጠጋበት አለቴ ነው፤ እርሱ ጋሻዬና የመዳኔ ቀን፥ ጠንካራ መመኪያም ነው።


እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤ ችግር በሚደርስብን ጊዜ ሁሉ ረዳታችን ነው።


ችግርህን ሁሉ ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ እርሱም በእንክብካቤ ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን ከቶ ለችግር አሳልፎ አይሰጣቸውም።


እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናግሮአል፤ ኀይል የእግዚአብሔር መሆኑን ሁለት ጊዜ ሰምቼአለሁ።


ሕዝቦች ሆይ! ዘወትር በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ መጠጊያችን ስለ ሆነ የልባችሁን ሐሳብ ሁሉ ለእርሱ አቅርቡ።


ተራ ሰዎች እንደ አየር ናቸው፤ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ተጨባጭነት እንደሌለው ምኞት ናቸው፤ ሁለቱ በሚዛን ላይ ቢቀመጡ ከነፋስ ሽውታ ይቀላሉ።


በኀይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፤ በዐይኑም መንግሥታትን አተኲሮ ያያል፤ ስለዚህ ዐመፀኞች በእርሱ ላይ ባይነሡ ይሻላቸዋል።


እግዚአብሔር ንጉሥ ነው፤ ግርማንና ኀይልን ተጐናጽፎአል፤ ምድርን በአንድ ስፍራ አጸናት፤ ከቶም አትናወጥም።


በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።


እስራኤል ሆይ እናንተ እንደ ጽኑ አለት መከላከያ ሆኖ የተቤዣችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ስለዚህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ድንቅና ብርቅ የሆነ ተክል ብትተክሉና


እናንተ ግን ደስ ይላችኋል፤ በተቀደሰ በዓል ምሽት እንደምትዘምሩት ትዘምራላችሁ፤ የእስራኤል አምባ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዋሽንት እየነፉ እንደሚዘምሩት ሰዎች ትደሰታላችሁ።


ከእነርሱ እያንዳንዱ ከነፋስ እንደሚከለሉበትና ከወጀብ እንደሚሰወሩበት መጠጊያ ይሆናል፤ በበረሓ እንደሚፈስሱ ጅረቶችና በምድረ በዳ እንደሚገኝ እንደ ትልቅ አለት መጠለያ ይሆናሉ።


እናንተ አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ አስቀድሜ አልነገርኳችሁምን? ወይስ አልገለጽኩላችሁምን? ለዚህም እናንተ ምስክሮቼ ናቸሁ፤ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ከእኔ ሌላ መጠጊያ አለት የለም፤ ማንም የለም።”


እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከእግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ዘለዓለማዊ ደኅንነት ትድናላችሁ፤ ለዘለዓለምም ኀፍረትና ውርደት ከቶ አይደርስባችሁም።


“ ‘ጽድቅና ኀይል የሚገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ ነው’ ብለው ስለ እኔ ይናገራሉ፤ የሚጠሉኝ ሁሉ ወደ እኔ መጥተው በዕፍረት ላይ ይወድቃሉ።


ከእናንተ መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራና ለአገልጋዩ ቃል የሚታዘዝ ማነው? ብርሃን የሌለው በጨለማ የሚመላለስ በእግዚአብሔር ይታመን፤ እምነቱንም በአምላኩ ላይ ይጣል።


ፈጥኜ በመምጣት አድናቸዋለሁ፤ በቅጽበት ድል የምነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ በኀይሌ ሕዝቦችን ሁሉ እገዛለሁ፤ በደሴቶች የሚኖሩ ሕዝቦች፥ እኔን በተስፋ ይጠባበቃሉ፤ ኀይሌንም ተስፋ ያደርጋሉ።


ከኤዶም ቦጽራ ቀይ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ የሚመጣው ይህ ማነው? በታላቅ ኀይሉ አስደናቂ ልብስ ለብሶ የሚራመደው ይህ ማነው? “ፍርድን የምሰጥ የማዳን ኀይል ያለኝ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


እኛ የምናገለግለው አምላክ ከዚህ ከሚነደው ከእሳት ነበልባልም ሆነ ከአንተ እጅ ሊያድነን ይችላል፤


ከዚህም በኋላ ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “የሲድራቅ፥ የሚሳቅና የአብደናጎ አምላክ የተመሰገነ ይሁን! እርሱ መልአኩን ልኮ እነዚህን አገልጋዮቹን አድኖአል፤ እነርሱ በአምላካቸው ተማምነው ለእርሱ ካልሆነ በቀር ለሌሎች አማልክት አንሰግድም በማለት የንጉሡን ትእዛዝ በማፍረስ ሕይወታቸውን በአደጋ ላይ ጥለውት ነበር።


ኢየሱስ ወደ እነርሱ ቀረበና እንዲህ አላቸው፤ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል፤


ከክፉ አድነን እንጂ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ [መንግሥት፥ ኀይልና ክብር ለዘለዓለም ያንተ ነው፤ አሜን።’]


“እስራኤላውያንም ወፈሩ፤ ዐመፁም። በጣም በልተው ወፈሩ፤ ሰቡ፤ የፈጠራቸውንም አምላክ ተዉ፤ መጠጊያ አዳኛቸውን አቃለሉ።


“እርሱ ምሽጋችን ነው፤ ሥራዎቹም ፍጹሞች ናቸው፤ መንገዶቹም ሁሉ የቀኑ ናቸው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፥ እርሱም ቀጥተኛና እውነተኛ ነው።


ዘለዓለማዊ አምላክ መጠጊያህ ዘለዓለማዊ ክንዶቹ ደጋፊዎች ናቸው፤ ጠላትን ከፊትህ ያባርራል፤ እንድትደመስሳቸውም ያደርጋል።


ኀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።


“እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለም፤ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አምላካችንን የሚመስልም መጠጊያ ምሽግ የለም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos