Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሆሴዕ 8:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “የእስራኤል ሕዝብ ለራሳቸው ታላላቅ ቤተ መንግሥቶች ሠርተዋል፤ እኔን ፈጣሪአቸውን ግን ረስተዋል፤ የይሁዳም ሕዝብ ብዙ የተመሸጉ ከተሞችን ሠርተዋል፤ ስለዚህ ከተሞቻቸውንና ምሽጎቻቸውን የሚያቃጥል እሳት እልክባቸዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እስራኤል ፈጣሪውን ረሳ፤ ቤተ መንግሥቶችንም ሠራ፤ ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አበዛ፤ እኔ ግን በከተሞቻቸው ላይ እሳትን እለቃለሁ፤ ምሽጎቻቸውንም ይበላል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፥ ቤተ መንግሥቶችን ሠርቶአል፤ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፤ እኔ ግን በእርሱ ከተሞች ላይ እሳት እልካለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ትበላለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እስ​ራ​ኤል ፈጣ​ሪ​ውን ረስ​ቶ​አል፤ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​ንም ሠር​ቶ​አል፤ ይሁ​ዳም የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች አብ​ዝ​ቶ​አል፤ እኔ ግን በከ​ተ​ሞች ላይ እሳ​ትን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትበ​ላ​ለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፥ መስገጃዎችንም ሠርቶአል፥ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፥ እኔ ግን በከተሞች ላይ እሳት እሰድዳለሁ፥ አዳራሾችንም ትበላለች።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 8:14
31 Referencias Cruzadas  

ያስገኛቸውን አምላክ ተዉ፤ የፈጠራቸውንም እግዚአብሔር ረሱ።


ነገር ግን ለእኔ መታዘዝና ሰንበትንም የተቀደሰ ቀን አድርገው ማክበር ይገባቸዋል፤ በዚህ ዕለት በኢየሩሳሌም የቅጽር በሮች ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው መግባት የለባቸውም፤ ትእዛዜን ባለመቀበል ይህን ቢያደርጉ ግን የኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች በእሳት እንዲጋዩ አደርጋለሁ፤ የኢየሩሳሌም ቤተ መንግሥቶችም በእሳት ይነዳሉ፤ እሳቱንም ሊያጠፋ የሚችል የለም።’ ”


ስለዚህ በይሁዳ ምድር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ያቃጥላል።”


ነገር ግን ወደ መልካሚቱ ምድር በገባችሁ ጊዜ እስክትጠግቡ በልታችሁ እጅግ ታበያችሁ፤ እኔንም ረሳችሁ።


እስራኤል ሆይ እናንተ እንደ ጽኑ አለት መከላከያ ሆኖ የተቤዣችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ስለዚህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ድንቅና ብርቅ የሆነ ተክል ብትተክሉና


ስለዚህ በጢሮስ ከተማ ቅጽር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ ምሽጎችዋንም ያቃጥላል።”


እኛ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጃቸውን መልካም ሥራዎች እንድንሠራ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንደገና የተፈጠርን የእግዚአብሔር ፍጡሮች ነን።


ስለዚህ በራባ ከተማ ቅጽር ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ ምሽጎችዋንም ያቃጥላል፤ ከዚህ በኋላ በጦርነቱ ቀን ጩኸትና ሁካታ ይበዛል፤ ጦርነቱም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይፈጥናል፤


ስለዚህ በቴማን ከተማ ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ የቦጽራንም ምሽጎች ያቃጥላል።”


በንጉሥ ሐዛኤል ቤተ መንግሥት ላይ እሳት እለቅበታለሁ፤ እሳቱም ንጉሥ ቤንሀዳድ የሠራቸውንም ምሽጎች ያቃጥላል።


“በዓል” ለሚባለው ጣዖት ለማጠንና ጌጣጌጥዋን አድርጋ ፍቅረኛዎችዋን በመከተል እኔን በመተዋ እቀጣታለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።


አባቶቻቸው በዓልን በማምለክ ስሜን እንደ ረሱ እነርሱም ሕልሞቻቸውን እርስ በርሳቸው በመነጋገር ሕዝቤ የእኔን ስም የሚረሳ ይመስላቸዋል።


ልምላሜ በሌለባቸው ኰረብቶች ራስ ላይ ድምፅ ይሰማል፤ ይህም ድምፅ፥ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር አምላካቸውን በመርሳት ኃጢአት ሲሠሩ ኖረው፥ አሁን በመጸጸት የሚያሰሙት የለቅሶና የልመና ድምፅ ነው።


ለመሆኑ ኰረዳ ጌጣጌጥዋን፥ ሙሽራም የሙሽርነት ልብስዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ሊቈጠሩ ለማይችሉ ለብዙ ዘመናት ረስተውኛል።


እነርሱም ለራሴ የሠራኋቸው ሕዝቦች ስለ ሆኑ እኔን ያመሰግናሉ።”


ስለዚህ የቊጣውን ግለትና አስፈሪውን ጦርነት በላያችን ላይ አወረደ፤ በዙሪያችን እሳት አቀጣጠለ፤ እኛ ግን ይህን ሁሉ አልተረዳነውም፤ አቃጠለን ልብም አላደረግነውም።


እግዚአብሔር እንደ ጀግና ወታደር ይወጣል፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ ጦርነትን ያውጃል፤ በጠላቶቹም ላይ ድልን ይጐናጸፋል።


የእጄ ሥራ የሆኑትን ልጆቻቸውን በመካከላቸው ባዩ ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የእስራኤልን ቅዱስ ያከብራሉ፤ በእስራኤልም አምላክ ፊት በፍርሃት ይቆማሉ።


በግብጽ ሳሉ ታላላቅ ተአምራትን በማድረግ ያዳናቸውን አምላክ ረሱ።


እንዲሁም በይሁዳ ተራራማ ስፍራዎች ላይ ከተሞችን፥ ደን በበዛባቸው ስፍራዎችም ላይ ምሽጎችንና ቅጽሮችን ሠርቶ ነበር።


በምዕራባዊ ኰረብቶች ግርጌና በሜዳዎች ላይ ብዙ የቀንድ ከብቶች ስለ ነበሩትም በገጠር የተመሸጉ መጠበቂያ ግንቦችን ሠራ፤ ብዙ ጒድጓዶችንም ማሰ፤ ግብርና ይወድ ስለ ነበረ በኰረብታማ አገሮችና በለሙ ቦታ የወይን ተክል ተካዮችና ገበሬዎች ነበሩት።


አክዓብ፥ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኃጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቊጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም፤


እንዲሁም ኢዮርብዓም በኮረብታዎች ላይ የማምለኪያ ስፍራዎችን አዘጋጅቶ የሌዊ ነገድ ካልሆኑ ቤተሰቦች መካከል ማንኛውንም ሰው ካህን አድርጎ ሾመ።


ሕዝቅያስ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም አደጋ በመጣል የተመሸጉትን የይሁዳን ከተሞች ያዘ፤


ኑ፤ ዝቅ ብለን እንስገድ! በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ!


የእስራኤል ሕዝብና በሰማርያ ከተማም የሚኖሩ ሁሉ ይህን ያደረገ እግዚአብሔር መሆኑን ያውቃሉ፤ ሆኖም፥ ትዕቢተኞችና እልኸኞች ሆነው እንዲህ ይላሉ፦


“ከጡብ የተሠሩ ግንቦች ፈርሰዋል፤ እኛ ግን እንደገና በጥርብ ድንጋይ እንገነባቸዋለን፤ ከሾላ ግንድ የተሠሩ ምሰሶዎች ተሰብረዋል፤ እኛ ግን በምርጥ የሊባኖስ ዛፍ እንተካቸዋለን።”


ሰብላችሁንና ምግባችሁን ሁሉ ጠራርገው ይበሉታል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን ሁሉ ይገድላሉ፤ የበጎችና የከብት መንጋችሁን ሁሉ ያርዳሉ፤ የወይን ተክሎቻችሁንና የበለስ ዛፎቻችሁን ሁሉ ያጠፋሉ፤ ሠራዊታቸውም የምትተማመኑባቸውን የተመሸጉ ከተሞቻችሁን ሁሉ ያወድማሉ።


አሁንም ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ስለ ረሳሽኝና ጀርባሽን ስላዞርሽብኝ፥ ስለ ሴሰኛነትሽና ስለ አመንዝራነትሽም መከራ ትቀበዪአለሽ።”


ሕዝቤ እኔን በሚገባ ካለማወቁ የተነሣ ጠፍቶአል፤ እናንተ እኔን ለማወቅ ስላልፈለጋችሁ እኔም ካህናት ሆናችሁ እንድታገለግሉኝ አልፈልጋችሁም፤ ሕጌንም ስላቃለላችሁና ስለ ረሳችሁ ልጆቻችሁ በእኔ ዘንድ የተረሱ ይሆናሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios