Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 32:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “እርሱ ምሽጋችን ነው፤ ሥራዎቹም ፍጹሞች ናቸው፤ መንገዶቹም ሁሉ የቀኑ ናቸው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፥ እርሱም ቀጥተኛና እውነተኛ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 “እርሱ ዐለት፥ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፥ የታመነ አምላክ፥ ተንኮል የሌለበት፥ እርሱ ቀጥተኛና ጻድቅ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሥ​ራው እው​ነ​ተኛ ነው፤ መን​ገ​ዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ክፋ​ትም የለ​በ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቅና ቸር ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው፤ 2 መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ 2 የታመነ አምላክ፥ ክፋትም የሌለበት፥ 2 እርሱ እውነተኛና ቅን ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 32:4
66 Referencias Cruzadas  

ይህም የሚያረጋግጠው እግዚአብሔር ትክክለኛ መሆኑንና ጠባቂዬ በሆነው አምላክ ዘንድ እንከን ያለመኖሩን ነው።


ለዘለዓለሙም በእግዚአብሔር ታምናችሁ ኑሩ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም መጠጊያ አምባችን ነውና።


እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬና አዳኜ ነው፤ አምላኬ የምጠጋበት አለቴ ነው፤ እርሱ ጋሻዬና የመዳኔ ቀን፥ ጠንካራ መመኪያም ነው።


“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”


እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ፍቅሩና ታማኝነቱ ዘለዓለማዊ ነው።


መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።


ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹሞች ሁኑ።


ሁሉም አንድ ዐይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ የጠጡትም ይከተላቸው ከነበረው ከዚያ ከመንፈሳዊ አለት የመነጨ ነበር፤ ያም አለት ራሱ ክርስቶስ ነበር።


በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”


አንድ ሰው መመካት ካለበት በምድር ላይ ምሕረትን፥ ትክክለኛ ፍርድንና እውነትን የማስገኝ እኔ አምላክ መሆኔን በመረዳት ይመካ፤ እኔም ደስ የሚያሰኘኝ ይኸው ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


ነገር ግን የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያሳይ ከሆነ እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን ቢቀጣን ትክክለኛ ፈራጅ አይደለም ማለት ነውን? እዚህ ላይ የምናገረው እንደ ሰው አስተሳሰብ ነው።


ይህን በሚያደርጉ ሰዎች ላይ፥ እግዚአብሔር የሚገባቸውን እንደሚፈርድባቸው እናውቃለን።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በመካከላችን ኖረ፤ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ እንዳለው ያለውን ክብሩን አይተናል።


አምላክ ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ፤ አንተ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን አድርገሃል፤ ከጥንት ጀምሮ ያቀድከውን ሁሉ፥ ፍጹምነት ባለው አስተማማኝ ሁኔታ አከናውነሃል።


በቅዱስ መጽሐፍ “እነሆ! የተመረጠና ክቡር የሆነ የማእዘን ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም” የሚል ቃል ተጽፎ ይገኛል።


አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጥቶአል።


ዐይኖችህ እጅግ የጠሩ ስለ ሆኑ፥ ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ማየት አይስማማህም፤ ታዲያ እነዚህን ዐመፀኞችን እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታቸዋለህ? ክፉዎችስ ከእነርሱ ይበልጥ ደጋግ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠፉ ሲነሡ ስለምን ዝም ትላለህ?


ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “እነሆ፥ የጸና የመሠረት ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ እርሱም የተመሰከረለት፥ የከበረ የማእዘን ድንጋይ ነው፤ በእርሱም የሚያምን ሁሉ አይናወጥም።


ብሩህና ጥቊር ደመና ዙሪያውን ከበውታል፤ ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።


“አስተዋዮች የሆናችሁ ሰዎች አድምጡኝ! ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር፥ ስሕተትንም ማድረግ ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ!


ያስገኛቸውን አምላክ ተዉ፤ የፈጠራቸውንም እግዚአብሔር ረሱ።


“እስራኤላውያንም ወፈሩ፤ ዐመፁም። በጣም በልተው ወፈሩ፤ ሰቡ፤ የፈጠራቸውንም አምላክ ተዉ፤ መጠጊያ አዳኛቸውን አቃለሉ።


ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ሊያድንም ሊያጠፋም የሚችል እርሱ ብቻ ነው፤ ታዲያ፥ በሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?


እንግዲህ አንተ ንስሓ ባለመግባትህና እልኸኛ በመሆንህ የእግዚአብሔር ቊጣና ትክክለኛ ፍርድ በሚገለጥበት ቀን ቅጣትህ እንዲበዛ ታደርጋለህ።


“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ ይህን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ማድረግ ብቻም ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ሰዎች ያበረታታሉ።


ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጠ፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን እውነተኛ አምላክ ነህ፤ አንተ ሕያው አምላክ፥ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነህ፤ አንተ በምትቈጣበት ጊዜ ዓለም ይናወጣል፤ የአሕዛብ መንግሥታትም የአንተን ቊጣ ችለው አይቆሙም።


ከእነርሱ እያንዳንዱ ከነፋስ እንደሚከለሉበትና ከወጀብ እንደሚሰወሩበት መጠጊያ ይሆናል፤ በበረሓ እንደሚፈስሱ ጅረቶችና በምድረ በዳ እንደሚገኝ እንደ ትልቅ አለት መጠለያ ይሆናሉ።


ይህም ሁሉ ሆኖ እግዚአብሔር ምሕረት ሊያደርግላችሁ ተዘጋጅቶአል፤ እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ስለ ሆነ ሊራራላችሁ ወዶአል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።”


እግዚአብሔር የሠራው ነገር ሁሉ ዘለዓለማዊነት እንዳለው ዐውቃለሁ፤ በእርሱ ላይ የሚጨመርበት ወይም ከእርሱ የሚቀነስ ነገር የለም፤ እግዚአብሔር ይህን ያደረገው ሰዎች እርሱን እንዲፈሩት ነው።


እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ የፈጠረ ነው። እርሱ ዘወትር ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል፤


የገባኸውን ቃል ኪዳን ትፈጽምልኛለህ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ፍቅርህ ዘለዓለማዊ ነው፤ የእጅህን ሥራ ወደ ፍጻሜ ሳታደርስ አትተወው።


ፍትሕን የምትወድ ኀያል ንጉሥ ሆይ! ቅንነትን መሥርተሃል፤ በእስራኤል ዘንድ ፍትሕንና ጽድቅን ተግባራዊ አድርገሃል።


ለእስራኤል ሕዝብ የሰጠውን ፍቅርና ታማኝነት አስታውሶአል፤ በየስፍራው ያሉ ሕዝቦች ሁሉ የአምላካችንን ድል አድራጊነት አይተዋል።


የእውነት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ነፍሴን ለአንተ እሰጣለሁና አድነኝ።


የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤ ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል።


እግዚአብሔር ሕያው ነው! አምላኬ መጠጊያዬ ይመስገን! ያዳነኝም ኀያል አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።


እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ።


“ምንም እንኳ እግዚአብሔርን አላየውም ብትል ጉዳይህ በእርሱ ፊት ስለ ሆነ በትዕግሥት ልትጠብቀው ይገባል።


የእስራኤል አምላክ ይህን ተናግሮአል፤ የእስራኤል ጠባቂ እንዲህ ብሎኛል፤ “እግዚአብሔርን በመፍራትና በፍትሕ የሚያስተዳድር ንጉሥ፥


እግዚአብሔር ሕያው ነው! አምላኬ መጠጊያዬ ይመስገን! ያዳነኝም ኀያል አምላክ ከፍ ከፍ ይበል!


“እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለም፤ እንደ አንተ ያለ ማንም የለም፤ አምላካችንን የሚመስልም መጠጊያ ምሽግ የለም፤


እርሱ እናትና አባት ለሌላቸው ድኻ አደጎችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች በትክክል ይፈርዳል፤ እርሱ በእኛ ሕዝብ መካከል የሚኖሩትንም መጻተኞች ሁሉ ስለሚወድ ምግብና ልብስ ይሰጣቸዋል።


ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ በፍጹም የታመነ አምላክ መሆኑን አስታውሱ፤ እርሱ ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል፤ ለሚወዱትና ትእዛዞቹንም ለሚፈጽሙ ሁሉ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ያሳያል።


እግዚአብሔር በፊቱ ሲያልፍ እንዲህ ብሎ ዐወጀ፤ “እኔ እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሐሪ አምላክ ነኝ፤ እኔ ለቊጣ የዘገየሁ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅሬና ታማኝነቴ የበዛ ነው፤


እግዚአብሔር የፈጠረውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፥ እጅግ መልካም ነበረ። ቀኑ መሸ፤ ሌሊቱ ነጋ፤ ስድስተኛ ቀን ሆነ።


ፍትሕ ማጓደል ወይም ማድላት ወይም ጉቦ መቀበል በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ የሌሉ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን በመፍራት ትክክለኛ ፍርድ ስጡ።”


እግዚአብሔር ፍርድን ከቶ አያጣምምም፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ሁልጊዜ ትክክለኛውን ነገር ያደርጋል።


‘ይህን አድርግ’ ብሎ የሚያዘው፥ ወይም ‘ክፉ ሥራ ሠርተሃል’ ብሎ የሚወቅሰው ማነው?


እግዚአብሔር አምባቸው እንደ ሆነ ያስታውሳሉ፤ ልዑል እግዚአብሔርም አዳኛቸው እንደ ሆነ ያስባሉ።


እኛ አገልጋዮችህ ታላቁን ሥራህን እንድናይ ፍቀድልን። ልጆቻችንም የኀይልህን ክብር እንዲያዩ አድርጋቸው።


እስራኤል ሆይ እናንተ እንደ ጽኑ አለት መከላከያ ሆኖ የተቤዣችሁን እግዚአብሔርን ረስታችኋል፤ ስለዚህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ድንቅና ብርቅ የሆነ ተክል ብትተክሉና


እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! አንተ ከጥንት ጀምሮ የነበርክ ቅዱስ ነህ፤ አንተ ስለምትጠብቀን አንሞትም፥ እነርሱ ፍርድህን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መድበሃቸዋል፤ አምባችን ሆይ! እኛን እንዲቀጡ ለእነርሱ ሥልጣን ሰጥተሃቸዋል።


ጻድቁ እግዚአብሔር በርስዋ ውስጥ አለ፤ እርሱ ስሕተት አያደርግም፤ እርሱ በየቀኑ ፍርድን ይሰጣል፤ በየማለዳው ይህን ከማድረግ አይቈጠብም፤ ክፉ አድራጊ ሕዝብ ግን ኀፍረት የለውም።


እርሱም ለአንተ ታማኝ እንደ ሆነ ተመልክተህ፥ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳንን አደረግህ፤ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ኢያቡሳውያንና ጌርጌሳውያን የሚኖሩባትንም የከነዓንን ምድር ለዘሮቹ መኖሪያ ርስት አድርገህ ልትሰጠው ቃል ገባህለት፤ አንተ ታማኝ ስለ ሆንክ ቃል ኪዳንህን አጽንተህ ጠብቀሃል።


የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው፤ ሥራውም ሁሉ የታመነ ነው።


እግዚአብሔር በሚያደርገው ሁሉ እውነተኛ ነው፤ በሥራውም ሁሉ ታማኝ ነው።


ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “ሰባቱ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ቀና ብዬ ወደ ሰማይ ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤ ለዘለዓለማዊው አምላክ ክብርና ውዳሴ አቀረብኩ፤ “ግዛቱ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios