ዘፍጥረት 49:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሮቤል፥ ኀይልና የጐልማሳነት ብርታት በነበረኝ ጊዜ፥ የወለድኩህ የበኲር ልጄ ነህ። ከልጆቼ ሁሉ በክብርና በኀይል የምትበልጥ አንተ ነህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤ ኀይሌና የጕብዝናዬም መጀመሪያ፤ በክብር ትልቃለህ፤ በኀይልም ትበልጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሮቤል፥ አንተ በኩር ልጄና ኃይሌ፥ የጉብዝናዬም መጀመሪያ፥ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሮቤል እርሱ የበኵር ልጄና ኀይሌ፥ የልጆችም መጀመሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አንገቱንም አደነደነ። ጭንቅ ነገርንም አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሮቤል አንተ በኵር ልጄና ኃይሌ የጕብዝናዬም መጀመሪያ ነህ፤ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ። |
ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።
የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው፤ (ሮቤል የአባቱን አልጋ ደፍሮ በማርከሱ የብኲርናውን መብት ስላጣ፥ ያ መብት ለዮሴፍ ተሰጥቶ ነበር፤
ከማያፈቅራት ሚስቱ የተወለደ ቢሆንም እንኳ ለበኲር ልጁ የሚሰጠው ድርሻ ከሌሎቹ የነፍስ ወከፍ ድርሻ በእጥፍ ከፍ ያለ መሆን አለበት፤ ስለዚህም ያ ሰው ልጁ በመጀመሪያ በመወለዱ በኲር መሆኑን ተረድቶ የብኲርና ድርሻውን ሊሰጠው ይገባል።
“ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ፥ አሜን ከሆነው፥ ታማኝና እውነተኛ ምስክር ከሆነው፥ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ መገኛ ከሆነው የተነገረ ነው፤