እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፦ “የልጅ ልጆችህ በባዕድ አገር ስደተኞች እንደሚሆኑ ዕወቅ፤ እዚያም በባርነትና በጭቈና ለአራት መቶ ዓመት ያስጨንቁአቸዋል፤
ዘፀአት 1:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ በብርቱ ሥራ ይጨቊኑአቸው ዘንድ ጨካኞች የሆኑ አሠሪዎችን ሾሙባቸው፤ በዚህም ሁኔታ ዕቃ ማከማቻ የሆኑትን ፊቶምና ራምሴ የተባሉትን ከተሞች ለፈርዖን ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እያስጨነቁ የግዳጅ ሥራ የሚያሠሯቸውን አሠሪ አለቆች ሾሙባቸው። እስራኤላውያንም ፊቶምና ራምሴ የተባሉ ንብረት ማከማቻ ከተሞችን ለፈርዖን ሠሩለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብርቱ ሥራ እንዲያስጨንቁአቸው ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፊቶምንና ራዓምሴስን የማከማቻ ከተሞች አድርገው ሠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብርቱ ሥራም ያስጨንቋቸው ዘንድ የሠራተኞች አለቆችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፌቶምን፥ ራምሴንና የፀሐይ ከተማ የምትባል ዖንን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብርቱ ሥራም ያስጨንቁአቸው ዘንድ ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፊቶምንና ራምሴን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ። |
እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፦ “የልጅ ልጆችህ በባዕድ አገር ስደተኞች እንደሚሆኑ ዕወቅ፤ እዚያም በባርነትና በጭቈና ለአራት መቶ ዓመት ያስጨንቁአቸዋል፤
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱና ወንድሞቹ በግብጽ ምድር እንዲቀመጡ አደረገ፤ ፈርዖን ባዘዘው መሠረት በግብጽ ምድር ምርጥ የሆነውን፥ በራምሴ ከተማ አጠገብ ያለውን ቦታ በይዞታ ሰጣቸው።
እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው፥ ከተሞችን ከተመ፤ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ።
ንጉሥ ቤንሀዳድም አሳ ባቀረበለት ሐሳብ በመስማማት የጦር አዛዦቹንና ሠራዊቱን ልኮ በእስራኤል ከተሞች ላይ አደጋ እንዲጥሉ አደረገ፤ ሠራዊቱም ዒዮን፥ ዳን፥ አቤልቤትማዕካ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና በንፍታሌም ግዛት ስንቅና ትጥቅ የሚቀመጥባቸውን ከተሞች ሁሉ በድል አድራጊነት ያዙ፤
ሙሴ ባደገ ጊዜ ወገኖቹን ለመጐብኘት ሄደ፤ ከባድ ሥራ መሥራታቸውን ተመለከተ፤ እንዲያውም አንድ ግብጻዊ ከወገኖቹ አንዱ የሆነውን ዕብራዊ ሲደበድብ አየ።
ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጭንቀት አይቻለሁ፤ በአስጨናቂዎቻቸው ምክንያት የሚጮኹትን ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ ጭንቀታቸውንም ዐውቃለሁ።
ጨካኞች የሆኑት ግብጻውያን አሠሪዎችና የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆች ሄደው ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ አሉ፤ “ንጉሡ ከእንግዲህ ወዲህ ገለባ እንዳይሰጣችሁ አዞአል፤
ነገር ግን ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን ያኽል አንድ ጡብ እንኳ ሳይጐድል እንዲያስረክቡ አድርጉ፤ ‘ለአምላካችን መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ ልቀቀን!’ እያሉ የሚነዘንዙኝ ብዙ የሚሠሩት ነገር ስለሌለ ነው፤
የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት ወደ ግብጽ እንደ ወረዱና እኛም በግብጽ ለብዙ ዓመቶች እንዴት እንደ ኖርን ታውቃለህ፤ ግብጻውያን የቀድሞ አባቶቻችንም ሆነ እኛን በብርቱ አሠቃይተዋል፤