Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 8:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በበረሓ የምትገኘውን የታጽሞርን ከተማና በሐማት ያለውን የስንቅና የትጥቅ ማኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ አጠናከረ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በምድረ በዳውም ውስጥ ተድሞርንና ቀድሞ በሐማት ሠርቷቸው የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በምድረ በዳም ያለውን ተድሞርን፥ በሐማትም የሠራቸውን ለግምጃ ቤት የሚያገለግሉትን ከተሞች ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በም​ድረ በዳም ያለ​ውን ተድ​ሞ​ርን፥ በኤ​ማ​ትም የጸኑ ከተ​ሞ​ችን ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በምድረ በዳም ያለውን ተድሞርን፥ በሐማትም የሠራቸውን የዕቃ ቤቱን ከተሞች ሁሉ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 8:4
6 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ በብርቱ ሥራ ይጨቊኑአቸው ዘንድ ጨካኞች የሆኑ አሠሪዎችን ሾሙባቸው፤ በዚህም ሁኔታ ዕቃ ማከማቻ የሆኑትን ፊቶምና ራምሴ የተባሉትን ከተሞች ለፈርዖን ሠሩ።


የሐማት ንጉሥ ቶዒ ዳዊት የሀዳድዔዜርን ሠራዊት በሙሉ ድል ማድረጉን ሰማ።


ሰሎሞን በሐማትና በጾባ ግዛቶች ላይ ዘምቶ በቊጥጥሩ ሥር አደረጋቸው፤


እንዲሁም ሰሎሞን በላይኛውና በታችኛው ቤትሖሮን በብረት መዝጊያ ሊዘጉ የሚችሉ ቅጽር በሮች ያሉአቸው የተመሸጉ ከተሞችን እንደገና ሠራ፤


ስለዚህ ኢዮሣፍጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ገናና እየሆነ ሄደ፤ በመላው ይሁዳ ምሽጎችንና፥ እጅግ የበዛ ስንቅና ትጥቅ የተከማቹባቸውን ከተማዎች ሠራ። በኢየሩሳሌምም የተለየ ችሎታ ያላቸውን ተዋጊዎች አኖረ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios