Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 68:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በጎቹን ለመጠበቅ ወደ ኋላ የቀሩት ክንፎቻቸው በብር የተለበዱ አንጸባራቂ የሆኑ ከወርቅ የተሠሩ ላባ ያላቸው ማዕድናዊ ርግቦችን አገኙ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በበጎች በረት መካከል ብትገኙ እንኳ፣ ከብር እንደ ተሠሩ የርግብ ክንፎች፣ በቅጠልያ ወርቅ እንደ ተለበጡ ላባዎች ናችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የሠራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፥ በቤትም የምትኖር ምርኮን ተካፈለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔስ በጸ​ሎቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው በጊ​ዜው ነው፤ ይቅ​ር​ታህ ብዙ ሲሆን መድ​ኃ​ኒቴ ሆይ፥ በእ​ው​ነት አድ​ነኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 68:13
22 Referencias Cruzadas  

“ይሳኮር በበጎች መካከል እንደሚተኛ ብርቱ አህያ ነው።


ሕዝቡም በፍጥነት እየተራወጠ ወጥቶ የሶርያን ሰፈር ዘረፈ፤ እግዚአብሔር አስቀድሞ በተናገረውም መሠረት ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ተሸመተ።


ከዚህ በኋላ እስራኤላውያንን መርቶ አወጣ፤ ሲወጡም ብርና ወርቅ ይዘው ነበር፤ ከነገዶቻቸውም መካከል ወደ ኋላ የቀረ ማንም አልነበረም።


እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ይለዋል፤ ድል በማቀዳጀት ትሑታንን ያከብራቸዋል።


አንተን የሚያምኑትን ነፍሶች ለአራዊት አሳልፈህ አትስጥ፤ የአገልጋዮችህንም ሥቃይ ለዘለዓለም አትርሳ!


“እኔ ከትከሻችሁ ሸክምን አወረድኩላችሁ፤ የጡቡን ሸክም ከላያችሁ እንድትጥሉት አደረግሁ፤


ጭቃ በማቡካት፥ ጡብ በማዘጋጀትና በእርሻ ውስጥ በጭካኔ ከባድ ሥራ በማሠራት ሕይወታቸው መራራ እንዲሆን አደረጉ።


ሕዝባችሁ ግን የምሰሶው ገመድ እንደ ላላ ምሰሶውም እንዳልጸና፥ ሸራውም እንዳልተዘረጋ መርከብ ነው፤ ከዚያ በኋላ የተትረፈረፈ ምርኮ ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ገብተው ይበዘብዛሉ።


በሁለት መድባችሁም አንደኛውን ክፍል ወደ ጦርነት ለሄዱ ወታደሮች፥ ሁለተኛውን ክፍል ለቀሩት የማኅበሩ አባላት ስጡ።


ዐሣማዎቹ ከሚመገቡት ብጣሪ ዐሠር ሆዱን ለመሙላት ይመኝ ነበር፤ ግን ይህንኑ እንኳ የሚሰጠው አልነበረም።


አባቱ ግን አገልጋዮቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ ‘ቶሎ ብላችሁ ከሁሉ የበለጠውን ልብስ አምጡና አልብሱት! በጣቱ ቀለበት፥ በእግሩም ጫማ አድርጉለት!


አሕዛብ በነበራችሁበት ጊዜ በማታውቁት ነገር ተመርታችሁ መናገር ወደማይችሉ ጣዖቶች ትወሰዱ እንደ ነበር ታውቃላችሁ።


እኛም ከዚህ በፊት ሞኞች፥ የማንታዘዝ እምቢተኞች፥ መንገዳችንን የሳትን ተላላዎች፥ ለልዩ ልዩ ፍትወትና ሥጋዊ ደስታ የተገዛን፥ በተንኰልና በምቀኝነት የምንኖር፥ የተጠላንና እርስ በርሳችንም የምንጣላ ነበርን።


አምስቱ አሞራውያን ነገሥታትም አምልጠው በማቄዳ ዋሻ ተደብቀው ነበር፤


ለምን በበጎች መካከል ዘገየህ? ለበጎች የሚደረገውን ፉጨት ለመስማት ነውን? ለመምጣት ወይም ላለመምጣት አመነታ።


በመጊዶ ውሃ አጠገብ በታዕናክ፥ ነገሥታቱ መጥተው ተዋጉ፤ ከዚያም የከነዓንን ነገሥታት ተዋጉ፤ የብር ምርኮ አላገኙም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos