Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ነገር ግን ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን ያኽል አንድ ጡብ እንኳ ሳይጐድል እንዲያስረክቡ አድርጉ፤ ‘ለአምላካችን መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ ልቀቀን!’ እያሉ የሚነዘንዙኝ ብዙ የሚሠሩት ነገር ስለሌለ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ሆኖም ቀድሞ በሚያቀርቡት ሸክላ ልክ ሠርተው እንዲያቀርቡ አድርጓቸው። የሥራ ድርሻቸውን አትቀንሱ። ሰነፎች ናቸው፤ ‘ሄደን ለአምላካችን መሥዋዕት እንሠዋ’ የሚሉትም ለዚህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ቀድሞ ይሠሩት የነበረውን የጡብ ቍጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፦ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ መሄድ እንፈልጋለን’ እያሉ ይጮኸሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ቀድሞ ያደ​ር​ጉት የነ​በ​ረ​ውን የጡብ ቍጥር እን​ዲሁ በየ​ቀኑ በእ​ነ​ርሱ ላይ አድ​ር​ጉት፤ ምንም ከእ​ርሱ አታ​ጕ​ድሉ፤ ሥራ ሰል​ች​ተ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ፦ ‘ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እን​ድ​ን​ሠዋ እን​ሂድ’ እያሉ ይጮ​ሃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ቀድሞ ያደርጉት የነበረውን የጡብ ቁጥር በእነርሱ ላይ አድርጉት፤ ምንም ከእርሱ አታጉድሉ፤ ሥራ ሰልችተዋልና ስለዚህ፥ ‘ለአምላካችን እንድንሰዋ እንሂድ’ እያሉ ይጮኻሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 5:8
6 Referencias Cruzadas  

ለአሕዛብ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ጠላቶቻቸውም ገዥዎቻቸው ሆኑ።


ከዚህ በኋላ በብርቱ ሥራ ይጨቊኑአቸው ዘንድ ጨካኞች የሆኑ አሠሪዎችን ሾሙባቸው፤ በዚህም ሁኔታ ዕቃ ማከማቻ የሆኑትን ፊቶምና ራምሴ የተባሉትን ከተሞች ለፈርዖን ሠሩ።


ንጉሡም መልሶ “እናንተ ሥራ የማትወዱ ሰነፎች ናችሁ፤ በፍጹም ሰነፎች ናችሁ፤ ‘ሄደን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንድናቀርብ ልቀቀን’ እያላችሁ የምትጠይቁበትም ምክንያት ይኸው ነው፤


የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆች ቀድሞ የሚሠሩትን ያኽል ጡብ በየቀኑ መሥራት እንዳለባቸው በተረዱ ጊዜ በመከራ ላይ መውደቃቸውን ተገነዘቡ።


“ለጡብ ሥራ የሚሆን ገለባ ለሕዝቡ እንደ ወትሮው አትስጡ፤ እነርሱ ራሳቸው ገለባውን ፈልገው ያምጡ፤


ሐሰተኛ ወሬ የሚሰሙበት ጊዜ እንዳይኖራቸው፥ እነዚህ ሰዎች ከምንጊዜውም ይልቅ በሥራ እንዲጠመዱና በብርቱ እንዲሠሩ አድርጉአቸው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos