ዳንኤል 9:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከስድሳ ሁለት ሳምንት በኋላ መሲሑ ያለ ፍትሕ ይገደላል፤ የሚገደለውም ለራሱ አይደለም፤ የሚመጣው መሪ ወታደሮች ቤተ መቅደሱንና ከተማይቱን ይደመስሳሉ፤ መጨረሻውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ውድመት ስለ ታወጀ ጦርነት እስከ መጨረሻ ይቀጥላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከስድሳ ሁለቱ ሱባዔ በኋላ መሲሑ ይገደላል፤ ምንም አይቀረውም። የሚመጣው አለቃ ሰዎችም፣ ከተማውንና ቤተ መቅደሱን ይደመስሳሉ። ፍጻሜውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ጦርነት እስከ መጨረሻው ይቀጥላል፤ ጥፋትም ታውጇል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥ በእርሱም ዘንድ ምንም የለም፥ የሚመጣውም አለቃ ሕዝብ ከተማይቱንና መቅደሱን ያጠፋሉ፥ ፍጻሜውም በጐርፍ ይሆናል፥ እስከ መጨረሻም ድረስ ጦርነት ይሆናል፥ ጥፋትም ተቀጥሮአል። |
እነሆ፥ ጌታ እንደ በረዶ ወጨፎ፥ እንደሚያጠፋ ዐውሎ ነፋስና እንደሚያጥለቀልቅ ኀይለኛ የውሃ ጐርፍ የሆነ አንድ ጠንካራና ኀያል ሰው አለው። ይህም ሰው በሥልጣኑ ወደ ምድር አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል።
በእርሱ ላይ የተዛባ ፍርድ ተወስኖበት ተወሰደ፤ የወደፊትስ ሁኔታውን ማስተዋል የሚችል ማነው? ሆኖም ስለ ሕዝቤ መተላለፍ ተመታ፤ ከሕያዋንም ዓለም ተወገደ።
አሁን እኔ የአሦርን ንጉሥ ከኀይለኛ ሠራዊቱ ጋር በእነርሱ ላይ አስነሣዋለሁ፤ የሠራዊቱም አመጣጥ የኤፍራጥስን ወንዝ ሞልቶ እንደሚያጥለቀልቅ ማዕበል ይሆናል።
“የሶርያ ንጉሥ ወንዶች ልጆች ለጦርነት በመዘጋጀት ታላቅ ሠራዊት ያደራጃሉ፤ ከእነርሱ አንዱ ጠራርጎ እንደሚወስድ እንደ ኀይለኛ ጐርፍ ሆኖ በማለፍ በጠላት ምሽግ ላይ አደጋ ይጥላል።
“የሶርያ ንጉሥ መላ ሠራዊቱን ሰብስቦ ለመዝመት ያቅዳል፤ የጠላትን መንግሥት ለመደምሰስ ሴት ልጁን በመዳር ከጠላት ንጉሥ ጋር የትብብር ስምምነት ይዋዋላል፤ ይሁን እንጂ ዕቅዱ አይሳካለትም።
“የሶርያ ንጉሥ የፈለገውን ሁሉ ይፈጽማል፤ ራሱንም ከአማልክት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ከአማልክት ሁሉ በላይ ባለው አምላክ ላይ ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማይታወቅ የስድብ ቃል ይናገራል፤ የታቀደው ሁሉ መደረግ ስላለበት የእግዚአብሔር የቊጣው ቀን እስኪደርስ ድረስ ይሳካለታል።
ያም መሪ ለአንድ ሳምንት ከብዙ ሕዝቦች ጋር የጠበቀ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ በሳምንቱም እኩሌታ መሥዋዕቱንና ቊርባኑን ያስቀራል፤ በእነርሱም ፈንታ ጥፋት የሚያስከትለው ርኲሰት እንዲተካ ያደርጋል። ይህም የሚሆነው በዚያ አጥፊ መሪ ላይ የታወጀው ቅጣት እስኪፈጸም ድረስ ነው።”
እግዚአብሔርም ሆሴዕን “ከእንግዲህ ወዲህ የእስራኤል ሕዝብ ወገኖቼ አይደሉም፤ እኔም የእነርሱ አምላክ አይደለሁም፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ሎዓሚ’ ብለህ ጥራው አለው።”
መላዋ ምድር እንደ ግብጹ የዐባይ ወንዝ ከፍና ዝቅ በማለት ትናወጣለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድሪቱን ሲነካ ትቀልጣለች፤ በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።
ኢየሱስም “እነዚህን ትልልቅ ሕንጻዎች ታያለህን? እነዚህ ድንጋዮች ሁሉ ይፈርሳሉ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተነባብሮ የሚቀር የለም፤” ብሎ መለሰለት።
እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ “እርግጥ ነው፤ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል፤ ሁሉንም ያስተካክላል፤ ይሁን እንጂ፥ የሰው ልጅ ከባድ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚናቅ የተጻፈው እንዴት ነው?
ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”
ኢየሱስ ግን “ይህ የምታዩት ሁሉ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተነባብሮ የማይቀርበት ጊዜ ይመጣል፤ እነዚህ ድንጋዮች ሁሉ አንድ ቀን ይፈራርሳሉ።”
“በእንጨት ላይ ተሰቅሎ የሚሞት ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ ክርስቶስ ስለ እኛ እንደ ተረገመ ሰው ሆኖ ሕግ ከሚያስከትለው ርግማን ዋጀን።
ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።