Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 11:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የእግዚአብሔር ሊቀ ካህናት ሳይቀር እርሱን የሚቃወም ሠራዊት ሁሉ ከፊቱ ተጠራርጎ ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከፊቱ የሚቆመውን ታላቅ ሰራዊት፣ የቃል ኪዳኑንም አለቃ ሳይቀር ይደመስሳል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የሚጐርፍም ሠራዊት ከፊቱ ይወሰዳል፥ እርሱና የቃል ኪዳኑ አለቃ ይሰበራሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 11:22
11 Referencias Cruzadas  

“ከሞት ጋር ስምምነት አድርገናል፤ ከሙታንም ዓለም ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” እያላችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲሁም “ማታለልን እንደ መጠለያ፥ ሐሰትንም እንደ መጠጊያ አምባ ስላደረግን መቅሠፍት በሚመጣበት ጊዜ ሳይነካን ያልፋል” ብላችሁ ተስፋ ታደርጋላችሁ።


“የሶርያ ንጉሥ ወንዶች ልጆች ለጦርነት በመዘጋጀት ታላቅ ሠራዊት ያደራጃሉ፤ ከእነርሱ አንዱ ጠራርጎ እንደሚወስድ እንደ ኀይለኛ ጐርፍ ሆኖ በማለፍ በጠላት ምሽግ ላይ አደጋ ይጥላል።


በተንኰል የሰላም ውል በመደራደር ሌሎችን ያታልላል፤ የእርሱ ተከታዮች ጥቂቶች ቢሆኑም እየበረታ ይሄዳል።


እጅግም ተንኰለኛ ስለ ሆነ በማታለል ይበለጽጋል፤ ራሱንም ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ብዙ ሰዎችን ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ይገድላል፤ የልዑላንን ልዑል እንኳ ይፈታተናል፤ በመጨረሻም እርሱ ራሱ ይጠፋል፤ የሚጠፋውም በሰው ኀይል አይደለም።


ከስድሳ ሁለት ሳምንት በኋላ መሲሑ ያለ ፍትሕ ይገደላል፤ የሚገደለውም ለራሱ አይደለም፤ የሚመጣው መሪ ወታደሮች ቤተ መቅደሱንና ከተማይቱን ይደመስሳሉ፤ መጨረሻውም እንደ ጐርፍ ይመጣል፤ ውድመት ስለ ታወጀ ጦርነት እስከ መጨረሻ ይቀጥላል።


በዚህ ነገር ምድር ትናወጣለች፤ በአገሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የዓባይ ወንዝ ሞልቶ በመጒደል እንደሚናወጥ አገሪቱ በሞላ ትናወጣለች።”


መላዋ ምድር እንደ ግብጹ የዐባይ ወንዝ ከፍና ዝቅ በማለት ትናወጣለች፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድሪቱን ሲነካ ትቀልጣለች፤ በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።


ተቃዋሚዎቹን በኀይለኛ ጐርፍ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos