Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሆሴዕ 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እግዚአብሔርም ሆሴዕን “ከእንግዲህ ወዲህ የእስራኤል ሕዝብ ወገኖቼ አይደሉም፤ እኔም የእነርሱ አምላክ አይደለሁም፤ ስለዚህ የልጅህን ስም ‘ሎዓሚ’ ብለህ ጥራው አለው።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “ሎዓሚ ብለህ ጥራው፤ ምክንያቱም እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም፤ እኔም አምላካችሁ አይደለሁምና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታም፦ “ሕዝቤ አይደላችሁምና፥ እኔም አምላካችሁ አይደለሁምና ስሙን ሎዓሚ ብለህ ጥራው፥” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሕዝቤ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና፥ እኔም አም​ላክ አል​ሆ​ና​ች​ሁ​ምና ስሙን ኢሕ​ዝ​ብየ ብለህ ጥራው” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔርም፦ ሕዝቤ አይደላችሁምና፥ እኔም አምላክ አልሆናችሁምና ስሙን ሎዓሚ ብለህ ጥራው አለው።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 1:9
5 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ሙሴና ሳሙኤል እንኳ በፊቴ ቆመው ቢማልዱ ለዚህ ሕዝብ ምሕረት አላደርግም፤ ስለዚህ ከፊቴ ወዲያ እንዲሄዱ አድርግ።


በማግስቱም ከሰንሰለት እስራት ከፈታኝ በኋላ እንዲህ አልኩት፥ “ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔር ስምህን ፓሽሑር ብሎ አይጠራህም፤ ለአንተ ያወጣልህ ስም ‘ሽብር በየስፍራው’ የሚል ነው።


የእስራኤል ሕዝብ ብዛት ሊቈጠር ወይም ሊለካ እንደማይቻል የባሕር አሸዋ ይሆናል፤ አሁን እግዚአብሔር “ሕዝቤ አይደላችሁም” ቢላቸው በዚሁ ስፍራ “የሕያው እግዚአብሔር ልጆች!” ተብለው የሚጠሩበት ጊዜ ይመጣል፤


ጎሜር ሎሩሐማን ጡት ካስጣለች በኋላ እንደገና ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች።


ሕዝቤን በምድሪቱ ላይ እመሠርታለሁ፤ እንዲበለጽጉም አደርጋቸዋለሁ፤ ‘ምሕረት አይደረግላችሁም’ የተባሉትን ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ የተባሉትንም ‘ሕዝቤ ናችሁ’ እላቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘አንተ አምላካችን ነህ’ ይሉኛል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos