2 ሳሙኤል 21:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዳዊት ዘመነ መንግሥት ሦስት ዓመት ሙሉ ጽኑ ራብ ነበር፤ ዳዊትም ስለዚህ ጉዳይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጠየቀ ጊዜ እግዚአብሔር “ሳኦልና ቤተሰቡ ግድያ በመፈጸም በደል ሠርተዋል፤ ሳኦልም የገባዖንን ሰዎች ፈጅቶአል” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዳዊት ዘመነ መንግሥት፣ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊት እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፣ “ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፣ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዳዊት ዘመነ መንግሥት፥ በተከታታይ ለሦስት ዓመት ራብ ሆነ፤ ስለዚህ ዳዊት ጌታን ጠየቀ፤ ጌታም፥ “ሳኦል ገባዖናውያንን ስለ ገደለ፥ እርሱና ቤቱ የደም ዕዳ አለባቸው” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተከታታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ። እግዚአብሔርም አለ፥ “የገባዖንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት፥” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል ቀጥሎ ቀጥሎ ራብ ሆነ፥ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ፊት ጠየቀ። እግዚአብሔርም፦ የገባዖንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት አለ። |
በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ራብ ሌላ ዳግመኛ ራብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቤሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤
አንተ የሳኦልን መንግሥት ወሰድህ ቤተሰቡንም ሁሉ ገደልክ፤ እነሆ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር አንተን በመቅጣት ላይ ነው፤ እግዚአብሔር መንግሥትን ለልጅህ ለአቤሴሎም አሳልፎ ሰጥቶታል፤ አንተ ነፍሰ ገዳይ! እነሆ የአንተ መጥፊያ ደርሶአል።”
እግዚአብሔር እንደገና በእስራኤል ላይ ስለ ተቈጣ በዳዊት አማካይነት መከራ እንዲመጣባቸው አደረገ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን “ሄደህ የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ቊጠር!” አለው፤
ዳዊትም “በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ልጣልባቸውን? ድልንስ ትሰጠኛለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ በእነርሱ ላይ አደጋ ጣልባቸው! እኔ በእነርሱ ላይ ድልን እሰጥሃለሁ!” ሲል መለሰለት።
ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እርሱም እንዲህ ሲል መለሰለት “አሁን ካለህበት በኩል በእነርሱ ላይ አደጋ አትጣል፤ ነገር ግን ከወዲያ በኩል በስተ ኋላ በመዞር ከሾላ ዛፎች ፊት ለፊት ሆነህ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ።
በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ከበባውም የምግብን እጥረትና ብርቱ ራብ ከማስከተሉ የተነሣ፥ የአንድ አህያ ራስ ዋጋ እስከ ሰማኒያ ጥሬ ብር፥ ሁለት መቶ ግራም የሚያኽል የርግብ ኩስ ዋጋ ደግሞ አምስት ጥሬ ብር ማውጣት ጀመረ።
ልጅዋን ከሞት ያስነሣላትን፥ በሱነም ትኖር የነበረችውን ሴት እነሆ፥ ኤልሳዕ አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፥ “እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቈይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ።”
ምግብ እንድታጡ በማደርግበት ጊዜ እንጀራችሁን ዐሥር ሴቶች በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፤ ምግባችሁንም መጥነው ያቀርቡላችኋል፤ እናንተም በልታችሁ አትጠግቡም።
ካህኑ አልዓዛር በኡሪም አማካይነት ፈቃዴን የሚያውቅ ስለ ሆነ ኢያሱ በአልዓዛር ይደገፋል፤ በዚህም ዐይነት አልዓዛር ኢያሱንና መላውን የእስራኤል ማኅበር በተግባር አፈጻጸማቸው ሁሉ ይመራቸዋል።”
እስራኤላውያን ግን የተከለከሉ ነገሮችን በተመለከተ ታማኞች ሆነው አልተገኙም፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነው ዓካን፥ የከርሚ ልጅ፥ የዘብዲ የልጅ ልጅ፥ የዛራ ልጅ ከተከለከሉት ነገሮች በመውሰድ በእስራኤል ላይ የእግዚአብሔርን ቊጣ አስነሣ።
በእስራኤል አገር መሳፍንት ይገዙ በነበረበት ዘመን በሀገሩ ላይ ረሀብ ሆነ፤ ከዚህም የተነሣ በይሁዳ ክፍለ ሀገር ከቤተልሔም አንድ ሰው ከሚስቱና ከሁለት ወንዶች ልጆቹ ጋር ለመኖር ወደ ሞአብ አገር ሄደ።
ስለዚህም እነርሱ “ሌላ የቀረ ይኖር ይሆን?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም “ሳኦል እነሆ በዕቃ መካከል ተደብቆ ይገኛል” ሲል መለሰላቸው።
ታዲያ፥ የቀዒላ ከተማ ነዋሪዎች እኔን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? ሳኦልስ እኔ እንደ ሰማሁት ወደዚህ መምጣቱ እውነት ነውን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! መልስ እንድትሰጠኝ እለምንሃለሁ!” እግዚአብሔርም “አዎ፥ ሳኦል በእርግጥ ይመጣል” ሲል መለሰለት።
ስለዚህም ዳዊት “ሄጄ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ልጣልባቸውን?” ሲል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ! በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ በመጣል ቀዒላን ከጥፋት አድን” ሲል መለሰለት።
ከዚህም የተነሣ ዳዊት እንደገና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “እኔ በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን ስለማቀዳጅህ ሄደህ በቀዒላ ላይ አደጋ ጣል” አለው።