ይሁዳ ወደ ዮሴፍ ቀርቦ እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ አንድ ቃል እንድናገር ፍቀድልኝ፤ ምንም እንኳ የፈርዖንን ያኽል የተከበርክ ብትሆን እባክህ አትቈጣኝ።
1 ሳሙኤል 26:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሆይ! የምልህን አድምጠኝ! አንተን በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፥ መሥዋዕት በማቅረብ ቊጣውን እንዲመልስ ማድረግ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ ሄደህ ባዕዳን አማልክትን አምልክ ብለው እግዚአብሔር ከሰጠኝ ርስት ድርሻ ስላባረሩኝ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባሪያውን ቃል ያድምጥ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደ ሆነ፣ ቍርባን ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፣ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ፤ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳድደውኛልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ንጉሥ ጌታዬ የባርያውን ቃል ያድምጥ፤ ጌታ በእኔ ላይ አነሣሥቶህ እንደሆነ፥ መሥዋዕት ይቀበል፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ፥ በጌታ ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ ‘ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ’ ብለው በጌታ ርስት ድርሻ እንዳይኖረኝ ዛሬ አሳደውኛልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእኔን የአገልጋይህን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አስነሥቶህ እንደሆነ፥ ቍርባንህን ይቀበል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ላይ እንዳልቀመጥ ዛሬ ጥለውኛልና በእግዚአብሔር ፊት ርጉማን ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የእኔን የባሪያህን ቃል ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ፥ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አስነሥቶህ እንደ ሆነ፥ ቁርባንን ይቀበል፥ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ላይ እንዳልቀመጥ ዛሬ ጥለውኛልና በእግዚአብሔር ፊት ርጉማን ይሁኑ። |
ይሁዳ ወደ ዮሴፍ ቀርቦ እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ አንድ ቃል እንድናገር ፍቀድልኝ፤ ምንም እንኳ የፈርዖንን ያኽል የተከበርክ ብትሆን እባክህ አትቈጣኝ።
የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
ንጉሡም አቢሳንና ወንድሙን ኢዮአብን “ይህ እናንተን አይመለከታችሁም፤ እግዚአብሔር አዞት ቢረግመኝ ‘ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?’ ብሎ ለመጠየቅ መብት የሚኖረው ማን ነው?” አላቸው።
ቀጥሎም ዳዊት ለአቢሳና ለመኳንንቱ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “የራሴ ልጅ ሊገድለኝ ይፈልጋል፤ ታዲያ በዚህ ብንያማዊ ሰው ስለምን ትደነቃላችሁ? እኔን እንዲረግመኝ እግዚአብሔር ነግሮታል፤ ስለዚህ ተዉት፥ የአሰበውን ያድርግ፤
የእኔ ከተማ ግን ታላቅ ከተማ ናት፤ በእስራኤል ሰላም የሰፈነባትና ታማኝ ከተማ እርስዋ ናት፤ ታዲያ፥ አንተ ይህችን ከተማ ለመደምሰስ ለምን ታቅዳለህ? የእግዚአብሔር ርስት የሆነውን ነገር ለማፍረስ ትፈልጋለህን?”
ስለዚህም ዳዊት የገባዖንን ሰዎች በአንድነት ጠርቶ “የእግዚአብሔርን ሕዝብ ትመርቁ ዘንድ ቀድሞ በተፈጸመባችሁ ግፍ ፈንታ ካሣ የሚሆን አንድ ነገር ላደርግላችሁ እፈልጋለሁ፤ ታዲያ፥ ምን ላድርግላችሁ?” አላቸው።
እግዚአብሔር እንደገና በእስራኤል ላይ ስለ ተቈጣ በዳዊት አማካይነት መከራ እንዲመጣባቸው አደረገ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን “ሄደህ የእስራኤልንና የይሁዳን ሕዝብ ቊጠር!” አለው፤
እግዚአብሔርም ‘እንዴት አድርገህ ልታሳስተው ትችላለህ?’ አለው። መንፈሱም ‘ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ’ ሲል መለሰለት፤ እግዚአብሔርም ‘እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል አለው።’ ”
ይህንንም አይተሽ ፈገግታሽ በደስታ ይፈካል፤ ከባሕር የሚገኘው በረከትና፥ ከሕዝቦች የሚመጣው ሀብት የአንቺ ስለሚሆን፥ ከደስታሽ ብዛት የተነሣ ልብሽ ይፈነድቃል።
አንተ በምትበላው ምግብ ምክንያት ለወንድምህ እንቅፋት ከሆንክ በፍቅር የምትኖር አይደለህም፤ ስለዚህ ክርስቶስ የሞተለትን ሰው በምትበላው ምግብ ምክንያት እንዲጠፋ አታድርግ።
በማግስቱም በድንገት ከእግዚአብሔር የተላከ ክፉ መንፈስ ሳኦልን ተቈራኘው፤ በቤቱም ውስጥ እንደ እብድ ይለፈልፍ ነበር፤ ዳዊትም በየቀኑ ያደርግ በነበረው ዐይነት ለሳኦል በገና ይደረድርለት ነበር፤ ሳኦልም ጦሩን በእጁ ይዞ ነበር።
ዳዊት በልቡ እንዲህ ሲል አሰበ፤ “አንድ ቀን ሳኦል እኔን ይገድለኛል፤ እንግዲህ ለእኔ የሚበጀኝ ነገር አምልጬ ወደ ፍልስጥኤም መሄድ ነው፤ ከዚያም በኋላ ሳኦል በእስራኤል ምድር እኔን መፈለጉን ስለሚተው ከእጁ አመልጣለሁ።”