Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ገላትያ 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እንግዲህ እነዚህ ግራ የሚያጋቡአችሁ ሰዎች ቢፈልጉ መገረዝ ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ጃንደረባ ቢያደርጉ እወድ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ግራ የሚያጋቧችሁ ሰዎች የራሳቸውን መግረዝ ብቻ ሳይሆን ይጐንድሉ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የሚያውኩአችሁ ራሳቸውን ይስለቡ!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የሚ​ያ​ው​ኩ​አ​ች​ሁም ሊለዩ ይገ​ባል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 5:12
18 Referencias Cruzadas  

በሥጋው ያልተገረዘ ወንድ ሁሉ ቃል ኪዳኔን ስላላከበረ ከሕዝቡ ይወገዳል።”


ላባም “እሺ አንተ ባልከው እስማማለሁ” አለ።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ሰባት ቀን ሙሉ እርሾ ያልነካውና ፈጽሞ ያልቦካ ቂጣ ብቻ ትበላላችሁ፤ በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ሁሉ ከየቤታችሁ ታስወግዳላችሁ፤ ማንም ሰው በነዚያ ሰባት ቀኖች እርሾ ያለበትን እንጀራ ቢበላ ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ይወገዳል።


ይህን የመሰለ ቅባት የሚሠራ ወይም ከዚህ ቅባት ወስዶ ካህን ያልሆነውን ሰው የሚቀባ ከሕዝቤ መካከል ይወገዳል።’ ”


ከልጅ ልጆቻችሁ መካከል የረከሰ ሆኖ ሳለ የእስራኤል ልጆች ለእኔ ለይተው ወዳቀረቡት ቅዱስ ስጦታ ደፍሮ ቢቀርብ ከፊቴ ተወግዶ ይጠፋል፤ ይህም ሥርዓት በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ተጠብቆ ይኖራል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


እነርሱም “ሁለንተናህ በኃጢአት ተወርሶ የተወለድክ! አንተ እኛን ልታስተምር ነውን?” አሉና ከምኲራብ አስወጡት።


ከእኛ መካከል አንዳንድ ሰዎች እኛ ሳናዛቸው ወደ እናንተ መጥተው በነገሩአችሁ ቃል እንዳስቸገሩአችሁና ግራ እንዳጋቡአችሁ ሰምተናል፤


ሐናንያ ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ወደቀና ሞተ፤ ይህን ነገር የሰሙ ሰዎች ሁሉ እጅግ ፈሩ።


በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ “የእግዚአብሔርን መንፈስ ለመፈታተን እንዴት ተስማማችሁ? እነሆ! ባልሽን ቀብረው የሚመለሱት ሰዎች በበር ናቸው፤ አንቺንም ወስደው ይቀብሩሻል” አላት።


በውጪ ስላሉት ሰዎች ጉዳይ የሚፈርድ እግዚአብሔር ነው፤ እንግዲህ መጽሐፍ እንደሚል “ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱ።”


ነገር ግን በመካከላችን ሾልከው በስውር የገቡ አንዳንድ ሐሰተኞች ወንድሞች እንዲገረዝ ፈልገው ነበር፤ እነዚህ ሰዎች ለስለላ በመካከላችን ሠርገው የገቡት በኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን ነጻነት ነጥቀው ወደ ባሪያነት ሊመልሱን አስበው ነው።


ነገር ግን ከዚህ የተለየ ሌላ ሐሳብ እንደማይኖራችሁ እርግጠኛ ሆኜ በጌታ እተማመናለሁ፤ ማንም ግራ የሚያጋባችሁ ቢኖር ቅጣቱን ይቀበላል።


“የተኰላሸ ወይም የተሰለበ ሰው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ አባል አይሁን።


መለያየትን የሚያመጣውን ሰው አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ከመከርከው በኋላ ከእርሱ ራቅ።


እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን መቋቋም ያልቻሉበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እነርሱ ራሳቸው እንዲጠፉ ስለ ተፈረደባቸው ከጠላቶች ፊት ወደ ኋላ ይሸሻሉ። እንዲደመሰስ የታዘዘውን ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ እኔ ከእናንተ ጋር አልሆንም።


ኢያሱም “ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ ያመጣህብን ስለምንድን ነው? እነሆ! በአንተም ላይ ዛሬ እግዚአብሔር መከራን ያመጣብሃል!” አለው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ ዓካንን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ ቤተሰቡንም በድንጋይ ወግረው ንብረቱን ሁሉ አቃጠሉ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos